“….ነገር ግን እኔ ወለጋ ሔጄ ብገደል ግን ከዚህ በኋላ ወለጋ እና ጂማ፣ ወለጋ እና ባሌ፣ ወለጋ እና አርሲ አንድ ሁነው በኦሮሞነት መቀጠል አይችሉም….!”

አለ አሉ ዐቢይ በኦሮምኛ ወገኖቹን ሰብስቦ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ….!!!

በይፋ በቀረበበት መድረክ ይሄንን ያለ በጓዳማ ምን ይል ምን ያሴር ይሆን ወገኖቸ???

አየ የኛ የዘር ፖለቲካ ጠይው ድንቅ መሪ ዐቢይiiii…

የሚገርማቹህ ነገር ሰዉ ይሄንን ሰምቶም ከዚህ በኋላም ዐቢይ በአማርኛ ሕዝብን ለማጭበርበር፣ ለመሸንገል፣ ለማጃጃል፣ ለማታለል “እምየ ኢትዮጵያ፣ አንድነት!” ምንንትስ እትትት እያለ በሚያወራው የሚጃጃል መሆኑ ነው በጣም የሚገርመኝ!!!…

አሁን ይሄ ሰው ነው ኢትዮጵያን የሚያስቀድመው???

አሁን ይሄ ሰው ነው የዘር ፖለቲካ ቀውስ ከከተተን ማጥ ውስጥ የሚያወጣን???

አሁን ይሄ ነው ታዲያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር???

ይሄ ንግግር አቶ መለስ “ጨርቅ ከሆነው ከሌላው ሕዝብ ሳይሆን ወርቅ ከሆነው ከትግሬ ሕዝብ በመወለዴ እኮራለሁ!” ካለው ጠባብ፣ ደንቆሮና ዘረኛ ንግግር በምን ይለያል???

አንድ ሰው “ሁሉንም ዜጋ እንደ አባት በዕኩል ዓይን እያየሁ አሥተዳድራለሁ!” ብሎ ቃለ መሐላ ፈጽሞ በሀገር መሪነት ከተሾመ በኋላ እንዴት እንደዚህ ወደኋላ ተመልሶ ይወርዳል??? እንዴት እንደዚህ ይጠባል???

ዐቢይ እና ለማ ለእኛ በአማርኛ ተራውን ዜጋ ሳይቀር “ከዘር ፖለቲካ ውጡ!” እያሉ እየሰበኩ፣ እያዘናጉና በተመሳሳይ ንግግር እየከለሉ እነሱ ግን በኦሮምኛ ሕዝባቸውን የዘረኝነትን፣ የጠባብነትን፣ የጽንፈኛ ብሔርተኝነትን መርፌ እየወጉ ይመርዛኑ፣ ያነሣሣሉ፣ ይቀሰቅሳሉ ወደ ኦነግ ካምፕ ይልካሉ፣ ጽንፈኛ ኃይላቸውን ያደራጃሉ፡፡ አያሳዝንም???

እንዲያው ዝም ብላቹህ ትደክማላቹህ እንጅ የወያኔ/ኢሕአዴግ ማሕፀን በምንም ተአምር ቢሆን ከጠባብነት ወጥቶ ኢትዮጵያን የሚያስብ፣ ኢትዮጵያን የሚያስቀድም፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በእኩል የሚያይ መሪ ሊያፈራ አይችልም!!!…

አሃ ይቅርታ! የኞቹ በድኖች ማለቴ ብአዴኖች አሉ ለካ፡፡ “እንወክለዋለን!” ከሚሉት ከአማራ ሕዝብ ይልቅ ለሌላው የሚንገበገቡት፣ አማራን አዋርደው ሌላውን የሚያከብሩ፣ አማራን በድለው ሌላውን ተጠቃሚ የሚያደርጉ፣ አማራን ገለው ሌላውን ለማኖር የሚጥሩት የኞቹ በድኖች አሉ ለካ!

ግን እነሱም ቢሆኑኮ ሀገርን በማስቀደማቸው፣ ጠባብ ስላልሆኑ ሳይሆን አማራ ጠል ሆነው ስለተቀረጹ፣ የተሠራላቸው የጭንቅላት አወቃቀር (mind setup) በባርነት እንዲያገለግሉ ሆነው ብቻ ስለተተለሙ ነውኮ!!!

እባክህን ወገኔ ንቃ!!!… ተው ንቃ ተበላህ ኋላ ተናግሬያለሁ አለቀልህ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com