December 21, 2018
ለትግራይ ህዝብ
የህወሃት የጦር አበጋዞች ከኢዲዩ፣ኢህአፓ፣ ከደርግ፣ጦርነት ገጥሞ ኢትዩጵያን ተቆጣጠሩ፡፡ ህወሃት የጦር አበጋዞች ህዝቡን በዘር በመደራጀት (ትግሬ፣ኦሮሞ፣ አማራ፣ሱማሌ ወዘተ) ለሃያ ሰባት አመታት በአንድ ፓርቲ ገዛ፡፡

ፀጋዬ ገብረመድህን(ደብተራው)፣አበራሽ በርታ፣ ለማ ኃይሉ፣ ከበደ ተስፋ (ፎቶ ከአህአፓ ዌብ ሳይት)
የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን በትግራይ ወህኒ ቤቶች ውስጥ አስረው በድብደባ በማሰቃየት፣ ከወላጆቻቸው እንዳይጠየቁ በመሰወርና በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እንዳይጎበኙ በማድረግ ያለፍርድ እንደረሸኞቸው እንደገደሎቸው በአቶ ገብሩ አስራት መፅሃፍ ይፋ ወጥቶል፡፡ ከነዚህም ውስጥ {1}ጸጋዬ ገብረ መድህን(ደብተራው)፣{2} ይሳቅ ደብረፂዎን፣{3} ስጦታው ሁሴን፣{4} በለጠ አምኃ የኢህአፓ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩና ሌሎች አንጋፋ አባሎች ውስጥም {5} ደሳለኝ አምሳሉ፣ {6} ሃጎስ በዛብህ፣{7} ተክላይ ኃይለ ሥላሴና ከሱዳን ተላልፊ የተሠጠው {8} አዛነው ደምል፣ይገኙበታል፡፡ ከ1993 እኤአ ከአዲስ አበባ፣ባህር ዳር፣ ጎሞ ጎፋ በህወሓት የተሰወሩና የት እንዳደረሶቸው የማይታወቁት ውስጥ {9} አበራሽ በርታ፣ {10} ለማ መኮንን፣ {11}ተስፋዬ ከበደ፣ {12} ወንዱሲራክ ደስታ፣ {13} እዬብ ተካበ፣ {14}ሞት ባይኖር፣{15} አይነኩሉ፣ {16} ዬሴፍ፣ {17} ጋይም ገብረእግዚአብሄርና ጎደኞቹ በቅሎ ቤት አካባቢና {18} ጃታኒ አሊ በናይሮቢ በህወሓት የጦር አበጋዞች ሲገደሉ ሌሎች የደረሱበት አይታወቅም፡፡ ከኬንያ ታፍነው መጥተው የተገደሉ {19} ኢንጅነር ተስፍሁን {20}ኢንጁነር መስፍን ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዩጵያ የመጣው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ፣ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተቃዋሚ የህዝብ ልጆችን እያደኑ በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔዊ ተግባር ፈፅመዋል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት መሪ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ተወልደ ወልደ ብርሃን፣ በረከት ስምኦን፣ አባይ ፀሃይዬ፣ አለምሰገድና ኃያሎም አርዓያ ለግድያው ተጠያቂ ሲሆኑ ሌሎቹም ግልገል ፋሽስቶች አንድ ቀን ለፍርድ እንደሚቀርቡ ከደርግ መንግስት መማር ይገባቸዋል፡፡ በትግራይ ክልል በወያኔ ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የቶርቸር/ ግርፋት የስፈጸሙና የፈጸሙ ለህግ እንዲቀርቡ፣ መቐለ የመሸጉ ወንጀለኞችን የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡
የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንግድ ያሸጋግራሉ ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመተበቅ ይቆጠራል፡፡ ህወኃት በ43 ዓመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች ተቆጥረውና ተዘርዝረው አይዘለቁም፡-
{1} በትግራይ ክልል ብዙ የትግራይ ተወላጆችን፣ የኢዲና የኢህአፓ/አህአሠ ሰራዊትን ገድለው ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ ወያኔ የኢዲዩ አባላቶችን አስሮ ካሰቃያቸው በኃላ በነፍሰ ገዳይ ስኮዶቹ በነ ደብረጺዮንና ብስራት አማረ አማካኝነት ረሽነዋቸዋል፡፡ {2} የኢህአፓ አመራር አባሎችን እነ ፀጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው)ና ሎሎችን ከመቀሌ እስር ቤት አስረው ካስቃቸው በኃላ ረሽነዋቸዋል፡፡ ለዚህ ግድያ ተጠያቂዎቹ የህወኃት አመራሮች ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ አባይ ፀኃዬ ወዘተርፈዎች በደም የተጨማለቁ ነፍሰ ገዳዬች መሆናቸውን አንርሳ፡፡ ህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ በትረ ሥልጣን ከያዙ በኃላ በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የጅምላ ግዳያዎች በመፈፀም እጃቸውን በደም የታጠቡ ብድኖች ናቸው፡-{3} በኦሮሚያ በወለጋ፣ በበደኖ፣ በባሌ ከያዶት ወጣ ብሎ ብዙ ሰዎች ገብለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡{4} በሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት፣ ወያኔ ብዙ ሰዋች በኦብነግ ሥም ገድሎ በግሬደር ቆፍሮ የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች በሚዲያ ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶ፣ ለሰፊው ህዝብ እንዲቀርብ በሠማዕታቱ ሥም እንተይቃለን፡፡ {5} በአማራ ክልል ብዙ የወልቃት ተወላጆችን ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡{6} በጋምቤላ ክልል ብዙ የአኝዋክ ተወላጆችን እነ አባይ ፀሃዬና ገብርአብ በርናባስ ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ስላሉ ፍለጋው ቅድሚያ ይሠጠው እንላለን፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው!!! ለመጭው ትውልድ ወንጀለኞችን አናውርሰው እንላለን!!!
የወህኒ ቤቶች ሁኔታPrison and Detention Center Conditions
የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የወህኒ ቤቶች ሁኔታ በተመለከተ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ሦስት የፊዴራል እስር ቤቶችና 120 የክልል መንግስቶች እስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ብዙ ይፋ ያልሆኑ እስር ቤቶች በሃገሪቱ ውስጥ ሲገኙ ከነዚህ መኃከልም በዴዴሳ፣ በብር ሸለቆ፣ በጦላይ፣ ሆርማት፣ ብላቴ፣ ታጠቅ፣ ጅጅጋ፣ ሆለታና ሰንቀሌ የጦር ካንፖች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የወህኒ ቤቶች ሁኔታ ለእስረኛዎች ህይወት በጣም አስጊና ብዙ ሰዎች ተፋፍገው የታሰሩበትና ለመተኛት አመች ያልሆኑ ቦታዎች እንደነበሩና ብዙ ሰዎች በግፍ ተታስረ፣ተገርፈው ያለህግ ተገድለው በጅምላ መቃብር ሥፍራ ተቀብረዋል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ለእስረኞች በቀን ስምንት ብር ወይም ግማሽ ዶላር ለምግብ፣ ለውሃና ለጤና ጥበቃ ወጪ ያወጣል ነበር፡፡ ብዙዎቹ እስረኞች ተጨማሪ ምግብ ቤተሰቦቻቸው እየገዙ ያቀርቡላቸዋል ነበር፡፡ የእስረኞች ጤና ጥበቃ በተመለከተ በፊዴራል እስር ቤቶች ውስጥ አስተማማኝ ህክምና አያገኙም ነበር፡፡ በክልል እስር ቤቶች ውስጥም የህክምና አገልግሎት አልነበረም፡፡ በሃገሪቱ በሚገኙ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመኖሩ የተነሳ እስረኞች ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ባለመቻላቸው ብዙዎቹ በጤና ችግር ይሰቃያሉ ነበር፡፡ እስረኞች አነስተኛ የህክምና አገልግሎት ብቻ ያገኙ ነበር፡፡ በወርሃ የካቲት በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ አንድ የጣልያን ዜጋ በህክምና እጦት የተነሳ ህይወቱ አልፎል ነበር፡፡ በአመቱ መገባደጃ ላይ በአጠቃላይ በግምት 86,000 ሽህ እስረኞች ሲገኙ ከዚህ ውስጥ 2,474 ሴት እስረኞች ሲሆኑ፣ 546 ህፃናቶች ከእናታቸው ጋር ታስረው ይገኙ ነበር፡፡ የወጣት ጥፋተኞች አንዳንድ ግዜ ሞት ከተፈረደባቸው ጎልማሶች ጋር በአንድ ላይ ይታሰሩ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ወንድና ሴት እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች ታስረው ይገኛሉ፣ ቤተሰቦቻቸውም ይጠይቆቸው ነበር፡፡ በሌላ በኩል ቤተሰቦቻቸው የማይጠይቆቸው የተከለከሉ እስረኞች ነበሩ፡፡ The country has three federal and 120 regional prisons. There also are many unofficial detention centers throughout the country, including in Dedessa, Bir Sheleko, Tolay, Hormat, Blate, Tatek, Jijiga, Holeta, and Senkele. Most are located at military camps. Prison and pretrial detention center conditions remained harsh and in some cases life threatening. Severe overcrowding was common, especially in sleeping quarters. The government provided approximately eight birr ($0.50) per prisoner per day for food, water, and health care. Many prisoners supplemented this with daily food deliveries from family members or by purchasing food from local vendors. Medical care was unreliable in federal prisons and almost nonexistent in regional prisons. Water shortages caused unhygienic conditions, and most prisons lacked appropriate sanitary facilities. Many prisoners had serious health problems in detention but received little treatment. In April an Italian citizen died after receiving allegedly substandard medical treatment in Kality prison. At year’s end there were an estimated 86,000 persons in prison, of whom 2,474 were women and 546 were children incarcerated with their mothers. Juveniles were sometimes incarcerated with adults who were awaiting execution. Male and female prisoners generally were separated. Authorities generally permitted visitors. In some cases family visits to prisoners were restricted to a few per year.
በሁሉም ክልሎች ውስጥ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል፣ በሱማሌ፣ በሃረሪ፣ ደቡብ ክልሎችና በአዲስአበባና ድሬዳዋ አስተዳደር ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የቶርቸር/ ግርፋት የስፈጸሙና የፈጸሙ ህወሓት/ ኢህአዴግ ሹማምንቶች ለህግ እንዲቀርቡ፣ በየክልሎቹ ያሉ ያደፈጡ ስብኣዊ መብት የጣሱ ወንጀለኞችን ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጣቸውና ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረግ ሁሉም ክልሎች በትጋት እንዲሰሩ እንጠይቃለን፡፡ በሃገራችን መቼም የትም እንዳይደገም! NEVER EVER AGAIN!!!! ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል የሚሆነው ጥፋተኞቹን ለህግ በማቅረብ ነው፡፡ ኢሠመጉ አስፈላጊውን መረጃ ማቅረብ በአፋጣኝ ይጠበቅበታል፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው!!! ለመጭው ትውልድ ወንጀለኞችን አናውርሰው እንላለን!!!
ምንጭ በአቶ ገብሩ አስራት
