December 23, 2018

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

በኢትጵያ የታሪክ እስረኞች ወታደራዊው ደርግ ከ1967 እስከ 1983 ለ17 ዓመታት፣ ህወሓትከ 1983 እስከ 2010ዓ/ም ሃገራችንን የታሪክ እስርቤት ያደረጉ በታሪክ ወራዳ መሪዎች ያፈራችበት ህዝብ የታሰረበት፣ የተገረፈበት፣ የተረሸነበት፣ የተሰደደበት ታሪካችን ሲሆን እነዚህ የታሪክ እስረኞች ንሰሃ ሳይገቡ፣ በስመ ዴሞክራሲ፣በስመ የህዝብ መንግስት፣ የህዝብ ስብዓዊ መብቶች የጣሱ ፋስስቶችና ግልገል ፋስሽቶች የኢትዮጵያን እናቶች ሲያስለቅሱ የኖሩ የእንግዴ ልጆች ናቸው፡፡

ወታደራዊው ደርግ ከ1967 እስከ 1983 ለ17 ዓመታት የግፍ አገዛዙ ህዳር 13 ቀን 1967 ዓም የቀ.ኃ.ሥ ሚንስትሮችና የጦር ጀነራሎች በመረሸን በከርቸሌ የጅምላ መቃብር አማራ፣ኦሮሞው፣ ጉራጌው፣ ትግሬው፣ ኤርትራዊው ወዘተ በአንድ ጉድጎድ ተቀበሩ፡፡ ያለ ፍርድ ግድያ ዓለምን ያስገረመ ጭካኔ በታሪካችን አፃፈ፣ ብሎም በነፃ እርምጃና በቀይ ሽብር አንድ ትውልድ ፈጀ፡፡

November 23, 1974 was “Bloody Saturday” in Ethiopia for that day’s* surprise purge of some threescore politicians and soldiers by the ruling Derg. It was barely ten weeks since the Derg — an Amharic word meaning “committee”, in this case a leftist military junta — had formally overthrown Emperor Haile Selassie.
በኢትዮጵያ የሰው ልጆች ያለ ህግና ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ገሎ መንገድ በመጣል አዲስ ባህል እንደ ተስቦ ተስፋፋ፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ከ 1983 እስከ 2010ዓ/ም ሃገራችንን የታሪክ ጎማ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን በከፋ በመመረሽ ዜጎቹን በድብቅ እስር ቤቶች በማሰር፣ በኢሰብዓዊ ግርፋት፣ ሴቶችን በመድፈር፣ ወንዶችን በግብረሶዶማዊነት በመድፈር፣ ዜጎችን በመሰወርና በመግደል፣ ታሪክ የማይረሳው ሥራ ሰርተዋል፡፡ ወያቤ በበደኖ፣ አርባጉጉ፣በአረካ፣ ሃዋሳ፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በሱማሌ፣ በጅግጂጋ፣ ቦረና፣ በአዲስ አበባ ያደረሰው የህዝብ ጭፍጨፋ የታሪካችን ጥቀርሻ ሆኖ ተመዝግቦል፡፡ የሀገራችን መሪዎች ህዝቡን እንዲህ የሚያደርጉት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው፡፡ የመሪዎቻችን ያልተማሩና ደንቆሮ በመሆናቸው ምክንያት በጭካኔ በትረ መንግሥታቸውን ሲገዙ ተስተውለዋል፡፡ የራሱን ቤተሰብ ማስተዳደር የማይችል ቀማኛ ሚኒስቴር፣ አንባሳደርና የጦር ጀነራል አድርጋ የሾመች አገር፣ አስራአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የነበሩ የህወሓት ሚኒስትሮች (ታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሠ፣ ተፈራ ዋልዋ፣በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዬሴፍ፣ ወዘተርፈ) ዮኒቨርሲቲ ሳይጨርሱ (መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ዳዊት ዮሃንስ ወዘተርፈ )የመከላከያ ሠራዊት የውትድርና ሳይንስ ትምህርትና ክህሎት ሳይኖራቸው የጦር ጀነራሎች የተባሉ (ስዬ አብርሃ፣ ሳሞራ ዩኑስ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ ጻድቃን ገ/ትንሳይ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ወዘተርፈ) አንዴ አንባሳደር፣ አንዴ ሚኒስቴር፣ አንዴ የክልል አሰታዳደሪ፣ አንዴ ሲቪል አንዴ ወታደር በአገር የቀለዱ ዋልጌዎች ሃገራችን በታሪኮ አስተናግዳ አታውቅም፡፡ የሃገሪቱን ሃብት የዘረፉ መሠረተ ደሃዎች መሬት ዘረፎ፣ ፎቅ ገነቡ፣ ገንዘብ ዘረፉ፣ ሴት ደፈሩ፣ ህዝቡን በዘር አፋጁ፣ አሰሩ ፣ገረፉ፣አሰደዱ ታሪካቸው ሳይጨምር ሳይቀንስ ይሄው ነው፡፡ የዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች ታሪካችሁን ጎልጉለው ያወጡታል፣ የግድያ ሴራችሁን ብዛት፣ የስካራችሁን ሱሰኛነት፣ የሰረቃችሁትን መሬትና ገንዘብ፣ የመንግሥት ቤት በስማችሁ ያዞራችሁትን፣ በመንግስት ቤት እየኖራችሁ ቤታችሁን ለሃያ አመታት ማከራየታችሁን፣ አፍቅሮተ ነዋይና ሥልጣን የእናንተ የገማ ታሪክ ዜና መዋዕል አያሻውም፡፡ ትምህርትና እውቀትን ወደ ነበረበት ማማ ሠገነት ላይ መልሰን ካላስቀመጥናት ሕግ አውጪው፣ህግ ተርጎሚውና ህግ አስፈፃሚው ነጻነት እስካልሰሩ ድረስ፣ ፖለቲካና ሙያተኛ ቴክኖክራቶች ያለጣልቃ ገብነት እስካልሰሩ ድረስ፣ የአካዳሚክ ነፃነት እስካልተጠበቀ ድረስ፣ የሲቪል ሶስይቲና የሙያ ማህበራት ተደራጅተው አስካልተንቀሳቀሱ ድረስ፣ ዴሞክራሲያዊና ስብኣዊ መብቶች፣ የህግ ሉዓላዊነት እስካላስከበርን ድረስ ወደ ትፋታችን እንመለሰለን፡፡ የደርግ ፋሽስቶች የነፃ እርምጃና የቀይ ሽብር ሠማዕታት በፎቶ በትንሹ አስተውሉት

የደርግና የህወሓት ፋሽስቶች የህሊና ፀፀት የሚባል ህሊና ያልፈጠረባቸው በሰሩት ስራ የሚኩራሩ የታሪክ እስረኞች ናቸው፡፡ ለሃገርና ለወገን ሳይሆን የሠሩት ሆዳቸውን ለመሙላት የራሳቸውን ድህነት ለመቅረፍ በፖለቲካ ሽርሙጥና የተካኑ አድርባይ መሪዎች በመሆናቸው ነው፡፡
Ethiopia: Remembering the Meles Massacres of November 2005, የ1998ዓ/ም ምርጫ የመለስ ግድያ በአዲአበባ

የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት የረከሰው በዚህ ዘመን ነው፣ ማንም ተነስቶ ሚኒስቴር፣ አንባሳደር፣ የጦር ጀነራል፣ የክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ፣ የክልል አስተዳዳሪ የተሆነበት ዘመን በደርግና ወያኔ ሥርዓት ተከተለ፡፡ የፖለቲካ ካድሬነትና ኮሚሳርነት የሽሮ መብያ የሥልጣን እርከን መውጫ የፖለቲካ ፓርቲና ድርጅቶች ዘመናዊ የሥልጣን የካዚኖ ቁማር ቤቶች ሆኑ፡፡ የተማረ ሰው፣ እውቀት ያለው ሰው ተጠላ መለስ ዜናዊ 42 የዩኒቨርሲቲ መምህራን ዶክተሮችና ፕሮፊሰሮች አባረረ፣ እውቀት በአፍጢሙ ተደፋ፡፡ አድርባይ የፖለቲካ ምሁራን በየዘራቸው አዶከብሬ እየመቱ፣ ያለ እውቀት መለመላቸውን የዘር ፖለቲካ በማራመድ የዘራቸው ሚኒስቴር፣ አንባሳደር፣ ወዘተርፈ ሆኑ፣ ፖለቲካ ሽሮ መብያ፣ ደሞዝ ማግኛ ቀለብ መሸመቻ ሆነ፡፡ የኢትጵያ ባንክና ፋይናንሻል ተቆማት በዘር ግንዳቸው ተዋቀሩ ወጋገን(የትግሬ)፣ አዋሽ(ኦሮሞ)፣ አባይ(አማራ)፣ ደቡብ(ደቡብ) ወዘተ ባንክና ኢንሹራንሱም በዘር የተደራጀባት ሃገር በመሆኖ ምሁሩ ይህን ዘረኛ አደረጃጀት ከስር መሠረቱ እስካልነቀለ ድረስ ሃገር አያድግም ህዝብ አይበለፅግም፡፡ የነቀዘው ፖለቲከኛ ምሁር ዩኒቨርሲቲዎችንም በየዘራቸው በማደራጀት ወጣቱን ትውልድ በጎሳ ልክፍት መርዞታል በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ በዘር ተከፋፍሎ መጋደል ያመጣው የዘር ፖለቲካ ከነሰንኮፉ ተነቅሎ እስካልወጣ እነዚህ ወጣቶች የሃገር መሪ ሆነው የስልጣን መንበሩን በጨበጡ ዘመን ምን ሊሆን እንደሚችል መተንበይ አያዳግትም፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ንግድ ድርጅቶች ፈልፍለው ኢፈርት፣ ጥረት፣ ወንዶና ዲንሾ በአክሲዩን ለህዝብና ለባለሃብቶች እስካልተሸጡ ድረስ ሙስና ሌብነት ከዚች ምድር አይጠፋም፡፡ በሃገራችን የስፖርት ብዱኖች በዘር ተደጋጁ ተዋቀሩ፣ የሃገሪቱ መኪኖች ታርጋና ታፔላ በዘር ተሸነሸኑ፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ካርዶች በዘር ተሰጡ፡፡ ወያኔ በ27 አገዛዙ ዘመን በዘር ፖለቲካ አንዱን ዘር ከሌላው እያጣላ ገዛ፡፡ የህዝባዊው አመፅና ተጋድሎ የወያኔን ሴራ በማክሸፍ አሁን የተጀመረው አዲስ ለውጥ ተከተለ፡፡ የህወሓት የፖለቲካ ፓርቲፖች ከንግድ ስራ እንዲወጡ በህገመንግሥቱ ያለው በተግባር እስካልዋለና እነዚህ የንግድ ድርጅቶችን ኢፈርት፣ ጥረት፣ ወንዶና ዲንሾ ለግሉ ዘርፍ በአክሲዩን ተሸጠው ከንግድዘርፍ እስካልወቱ እነሱን ማሽሞንሞን አሳማን ሊፒስቲክ ቀብቶ ቆንጆ ማድረግ ያህል ይሆናል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቆም መግለፅና መቃወም ከወዲሁ ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡
የህወሓት ፋሽስቶች መንግስታዊ ሽብርና በአዲስ አበባ በቢሸፍቱ እሬቻ፣ በሞያሌ ወዘተ የተደረገ የግፍ ግድያ ሠማዕታት በፎቶ በትንሹ አስተውሉት፡፡

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህወሓት/ኢህአዴግ ነው፡፡

መንግሥትና ዘመን ተቀየረ እንጂ ግድያው አልቀረም!!! የህግ የበላይነት በሃገራችን ይከበር!!! ለመጪው ትውልድ ነፃነት እናውርሰው!!!

የህወሓት ፋሽስቶች መንግስታዊ ሽብርና በአዲስ አበባ በቢሸፍቱ እሬቻ፣ በሞያሌ ወዘተ የተደረገ የግፍ ግድያ ሠማዕታት በፎቶ በትንሹ አስተውሉት፡፡ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህወሓት/ኢህአዴግ ነው፡፡