December 23 2018

በሕገ መንግሥቱ የተከበሩ መብቶች በማንኛውም ሁኔታ ሲጣሱ፣ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ አኳያ ለመተርጎምና ለማስከበር የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት መቋቋም እንዳበት ምሁራን ሐሳብ አቀረቡ፡፡ ሐሳቡን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሁራን፣ በጥብቅናና በተለያዩ ቦታዎች የሕግ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
ሐሳቡን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሁራን፣ በጥብቅናና በተለያዩ ቦታዎች የሕግ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አተረጓጎም ሥርዓት መሻሻል ያስፈልገዋል?›› በሚል ርዕስ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ታኅሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው የግማሽ ቀን ዓውደ ጥናት ላይ የተገኙ ምሁራን እንደገለጹት፣ በሕገ መንግሥቱ የተከበረ መብት በማንኛውም ሁኔታ መከበር አለበት፡፡ ነገር ግን ሕገ መንግሥትን የሚጥሱና ኢሕገ መንግሥት የሆኑ አዋጆችና ውሳኔዎች ሲወጡና ሲሰጡ መቆየታቸውንና እስካሁንም እንዳልታረሙ አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር) በዓውደ ጥናቱ ላይ እንደተናገሩት፣ በእሳቸው እምነት የሕገ መንግሥት ትርጉም ሥርዓት መሻሻል አለበት፡፡ የሕገ መንግሥት ትርጉሞችም ሦስት ዓይነት መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የመጀመርያው በሕገ መንግሥቱ ሰነድ ላይ የሚነሱ ክርክሮች ሲያጋጥሙ ሲሆን፣ ይኼም ውሳኔዎች ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጩ ሆነው ሲገኙ ፈራሽ በማድረግ፣ የሕገ መንግሥት የበላይነትን ማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሦስተኛው የባለሥልጣናት ውሳኔ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን ሲጥስ ፈራሽ መሆን እንዳበት በመግለጽ፣ ይኼም የሚፈጸመው የሕገ መንግሥቱን የበላይነት ሳይጠብቁ በፓርላማ በሚፀድቁና ለአስፈጻሚ ተቋማት በሚወጡ አዋጆች አማካይነት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ውሳኔዎች ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጩ ሆነው ሲገኙ ፈራሽ በማድረግ፣ የሕገ መንግሥት የበላይነትን ማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሦስተኛው የባለሥልጣናት ውሳኔ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን ሲጥስ ፈራሽ መሆን እንዳበት በመግለጽ፣ ይኼም የሚፈጸመው የሕገ መንግሥቱን የበላይነት ሳይጠብቁ በፓርላማ በሚፀድቁና ለአስፈጻሚ ተቋማት በሚወጡ አዋጆች አማካይነት መሆኑን አስረድተዋል፡፡  መንግሥት ሲከሰስ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለማስተላለፍ ግዴለሽነት እንደሚታይና ለዚህ ማሳያ ቅንጅት ስብሰባ እንዳያደርግ ሲከላከል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የከሰሰበትን የክስ ሒደት በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፖለቲካ ተቋም ከመሆኑ አንፃር ተቃራኒ ውሳኔ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ስለሚሆን፣ ከየክልሎቹ የተውጣጡና ብቃት ያላቸው ዳኞች በሕዝቡ ተመርጠው የሚዳኙበት የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት በማቋቋም ለችግሮች መፍትሔ መስጠት እንዳለበት የሕግ ባለሙያዎቹ አስተያየት አቅርበዋል፡፡ ሕገ መንግሥቱም ተሻሽሎ የትርጉም አሰጣጥ ሥርዓቱም መስተካከል እንዳለበትም አክለዋል፡፡