ብዙዎቻቹህ እኒህን አቡነ አብርሃም የተባሉትን ሰውየ ከሁለት ዓመት በፊት ባሕርዳር መስቀል አደባባይ ላይ ለሕዝብ አሳቢ ተቆርቋሪ እረኛ መስለው የተናገሩትን ሸንጋይ ቃል በመያዝ ትክክለኛ ወይም ታማኝ አባት እንደሚመስሏቹህ እገምታለሁ፡፡
ያንጊዜ እኒህ ሰውየ ድንገት ወደተቆርቋሪነት ተለውጠው ያንን ንግግር ሊናገሩ የቻሉት በእርግጥም ለሐዋርያዊ ተልእኮ ለመታመንና የእረኝነትን ግዴታ ለመወጣት አስበው ለሕዝብ ተቆርቋሪ ወደ መሆን መጥተው ወይም ተለውጠው ሳይሆን ያንን ቃል የተናገሩት በወቅቱ የባሕር ዳር ሕዝብ አስፈሪ በሆነ ደረጃ በትኩስ ዐመፅ ላይ ስለነበረ በዐመፁ ገፍቶበት ከፍተኛ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አርበኛ መስለው ሕዝቡን እንዲቀርቡ በተደረጉት በእኒህ ሰውየ በኩል ሕዝቡን ለመያዝ ለመቆጣጠር ታስቦ ስለነበረ ነበር ሰውየው ድንገት ወደተቆርቋሪነት እንዲለወጡ ተደርጎ ያንን ንግግር በበዓሉ ላይ እንዲናገሩና የሕዝብን አመኔታ እንዲያገኙ ተደርጎ የነበረው፡፡
እኒህ ሰውየ በወቅቱ ያንን ንግግር ካደረጉ በኋላ ሕዝቡን ማታለልና እንደጀግና ተቆጥረው ውዳሴና አድናቆት እንዲዘንብላቸው ማድረግ ቢችሉም ንግግሩን ከማድረጋቸው ቀደም ባሉ ጊዜያት ማታ ማታ ወደ ብአዴን ጽሕፈት ቤቶች እየሔዱ ከብአዴን ባለሥልጣናት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው እንደሚዶልቱ የሚያውቁ ሰዎችን ግን ማታለል አልቻሉም ነበር፡፡
እኒህ ሰውየ ሰሞኑን ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ኢሳት ትናንትና ማታ ክፍል አንዱን አቅርቦት ተመልክቸ ነበረ፡፡ ሰውየው እውነትን ፈጽሞ የማያውቋትና ለእውነትም የማይታመኑ አደገኛ ካድሬ (ወስዋሽ) በመሆናቸው ቅሰጣቸው እንዳይታወቅባቸው ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች በሚሰጡት መልስ “ወደዚያ ውስጥ መግባት አልፈልግም!” የሚለው ቃል ጋዜጠኛውን አሰልችቶት ነበር፡፡
ሕዝቡ አንድ የሚያውቀውን ወያኔ በቤተክርስቲያን ላይ የፈጸመውን ግፍ ለማስተባበል ለመደበቅ የተናገሩት ነገር ግን በጣም ገረመኝና ይህችን አጭር ጽሑፍ ለመጻፍ ፈለኩ፡፡
እኒህ የመርካቶ አጭሉግ ካድሬ የውሸት ጳጳስ በእርቁ ጉዳይ የዐቢይ አስተዋጽኦ የቱን ያህል እንደነበረ ተጠይቀው ሲመልሱ የዐቢይን አስተዋጽኦ ከገለጹ በኋላ ምን አሉ መሰላቹህ “……ከዚህ በፊትም ቢሆን እርቁን ግፉበት በርቱ ያለን አልነበረም እንጅ አትታረቁም ብሎ የከለከለን እኮ የለም!” በማለት በተደጋጋሚ እርቁን እያሰናከለ ያስቀረውን ሲጀመርም ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበራቸው በኃይል አፈናቅሎ ያሰደዳቸውን ወያኔን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ ጥረት አደረጉ፡፡
የሚያሳዝነው ነገር ግን አቦይ ስብሐት በወቅቱ ስለ እርቁ ተጠይቆ ለግል ጋዜጣ በሰጠው ቃለ ምልልስ “እናስታርቃለን የሚሉ ቄሶችን እንሰቅላለን!” ብሎ በማስፈራራትና ስለ እርቁ ጉዳይ ለመነጋገር ከቅዱስ ሲኖዶስ መልእክት ይዘው ከአሜሪካ የመጡትን ካህን መንበረ ፓትርያርክ ግቢ በር ላይ አፍነው ወስደው በዚያኑ ዕለት ወደ አሜሪካ ዲፖርት እንደተደረጉ ወይም እንደተባረሩ እርቁም በዚያው ተሰናክሎ መቅረቱን በወቅቱ የግፍ ሰለባው ካህን ራሳቸው በአሜሪካ ድምፅ ቀርበው የደረሰባቸውን እንግልትና ግፍ ተናግረውት እርቁን ለማሰናከል ወያኔ በቤተክርስቲያን ላይ የፈጸመውን ግፍ ሕዝብ ሰምቶት በሚገባ የሚያውቀው መሆኑ ነው፡፡
እንግዲህ ይታያቹህ! ይሄ እውነትን ፈጽሞ የማያውቃትና ለእውነት የማይገዛ እፍረተቢስ ምን ይሉኝ የማይል አጭበርባሪ ካድሬና ሐሰተኛ ጳጳስ ይሄንን ያህል በሕዝብ የሚታወቀውን እውነት ነው ለመደበቅ ጥረት ያደረገው፡፡
ግን ምን ያህል እፍረተቢስ ዓይን አውጣ አጭበርባሪ ቢሆን ነው ይሄ ሰውየ ሕዝብ በዚህ ደረጃ የሚያውቀውን እውነት ለመደበቅ ጥረት ያደረገው??? አይገርምም??? አያሳፍርም??? አያሳዝንም???
እንዲህ ዓይነት ሰው የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ እያለ ሲመጻደቅና ቃለ እግዚአብሔርን እየጠቀሰ እየተናገረ ለማታለል፣ ለማወናበድ፣ ለማጭበርበር ሲጥር እንደማየት ምን የሚያበሳጭ፣ ምን የሚያናድድ፣ ምን የሚያበግን ነገር አለ ወገኖቸ???
“አየ አንች ቤተክርስቲያን ሰው ይቀበርብሻል???” አለ ያገሬ ሰው!!! ግድ የለም እግዚአብሔር ሁሉንም የሚገልጥበት ቀን አለውና እምብዛም አያሳስብም!!!
ለማንኛውም ግን ሰውየውን እወቁት ምእመናን!!! እባብ የወያኔ ካድሬ ነው!!! መድኃኔዓለም ክርስቶስ ማንነቱን ገልጦ እርቃኑን ያስቀረውና!!!
ድል ለቤተክርስቲያን!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
