በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ነቀርሳ የሆነብን አስተሳሰብንና ፍልስፍናን ሳይሆን የግለሰቦችና ቦድኖች ደጋፊ በመሆን ሰዎች በደቦ አመለካከት እንዲያስቡ መደረጋቸው ነው፡፡ በደቦ አመለካከት ግለሰቦች ሀሳባቸውን መናገር አይደፍሩም ቢናገሩም በደቦ የተሰበሰቡ ይወርዱባቸዋል፡፡ አሁን እያየን ያለንው ሰዎች መሠረታዊ ጥቅማቸውንና ሕልንውናቸውን ሳይቀር ለግለሰቦችና ቡድኖች መሥዋዕት እያደረጉ ነው፡፡ ከዛም በላይ በመሠሪነት እየነገዱበት አልፎም እየገደሉት ብዙ መከራ እያደረሱበት ያሉትን ማስተዋል እንዳይችል የሆነ ይመስላል፡፡ ሁሉም ጋር ይሄ ችግር አለ፡፡ ከቹሉም ግን የሚያሳዝነው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየሆነ ያለው ነው፡፡



December 27, 2018t

ዛሬ የኦሮሞን ፖለቲካ እየዘወሩ ያሉ ብዙዎች ሕዝቡን በኦሮሞነት መደለያ እሴቶቹን፣ ባሕሉህሉን አልፎም ሕልውናውን ሁሉ አውድመው የእነሱ የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ በማቆየት ለግል ጥቅማቸው ሲነግዱበት የሚታዩ ናቸው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ሁሉ ትልቁ ማነቆም ነው፡፡ ዛሬ ኦነግ በሚል የኦሮሞ ሕዝብ ደሜና አጥንቴ ነው የሚሊለትን ቡድን እንመራለን የሚሉ ግለሰቦች ኦሮሞን ለወያኔ ዋና መሳሪያ በማድረግ ሲነግዱበት መኖራቸው ሳያንስ ዛሬ ወያኔ ስትወገድ ከወያኔም በላይ እብድ አድርጓቸው ሲቅበዘበዙ እናያለን፡፡ ለዘመናት አንድም ቦታ ኮሽ ሲል ያልሰማንው ኦነግ ገና ወያኔ መንገዳግድ ስትጀምር ነበር በተለያዩ አቅጣጫ ለውጡን እያመጡ ያሉትን መፈታተን የጀመረው፡፡ ከሞያሌ እስከባቢሌ የነበረውን የሶማሌ ኦሮሞ ግጭት የአብዲ ኢሌ ሴራ ብቻ እንደሆነ ብዙዎች ሊሸፋፍኑት ይሞክራሉ፡፡ ይህን እውነት ሌላው ቀርቶ ግልጽ ከወጣ ችግር ይፈጥራል በሚል ይመስላል እነ አብይና ለማም ሊናገሩት አልፈለጉም፡፡ እውነቱን ግን አሳምረው ያውቁታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ አብዲ ኢሌ በጥምሩ ቡድኑ ቢሳተፍም በዋናነት ወያኔና-ኦነግ በጥምረት የሰሩት እንደሆነ ሁሉም ማስተዋል ቢችል ጥሩ ነበር፡፡
ኦነጋውያን ወያኔ በተለይ የአማራና ኦሮሞ ሕዝብ እንድ እየሆኑና ጉልበት እያገኙ መጥተው ወያኔን ከፍተኛ ስጋት ላይ በጣሉበት ወቅት ለወያኔ የሕዝቡን ትግል በውጭ ኃይሎች ግፊት እንደሆነ ለማስመሰል ግብዓት እንዲሆናት ኦነጋውያን ለንደን ላይ ተሰብስበው ኢትዮጵያ እንበታትናለን አሉ፡፡ በዛው ቀን ነበር ወያኔ ድሮም ትደሰኩር የነበረውን አገርን የሕዝቡን ትግል አገርን ከመተታተን ጋር እንደምስክርነት ስታሳየን የነበረው፡፡ የዛ ስብሰባ ንግግር አላማውም ይሄው ነበር፡፡ ለወያኔ ግብዓት እንዲሆና የተቀነባበረና የሕዝብን ትግል ትግል በሚጣልላቸው ዳረጎት የሸጡ ሴረኞች ያሴሩት፡፡

በዛው ወቅት ነበር ሌላ የኦሮሚያ ቻርተር በሚል የሕዝቡ አንድነትን (የኦሮሞና አማራን) ለመከፋፈል አትላንታ ላይ ተሰብስበው ሲየሴሩ የነበሩት፡፡ የሕዝብ አንድነት (በተለይ የኦሮሞና-አማራ) ወያኔን እንደሚያጠፋት ግልጽ ነበር፡፡ ከወያኔ ባልተናነሰ ግን የኦሮሞና አማራ ሕዝብ አንድነት ትልቅ ስጋት የነበረበት የኦሮሞን ሕዝብ በወያኔ ዳረጎት እየነገደበት የነበረው ቡደን ነበር፡፡

ኋላም ቆይቶ አይቀሬው ለውጥ በመጣ ጊዜ ኦነጋውያንንና በተለይም ጀዋር የተባለ ግለሰብ የሚቆምረው ቡድን እብድ ሲያደርጋቸው አይናችን አይቷል፡፡ ችግሩ ገብቶናል ለዘመናት ሲቆምሩት የነበረው ሴራ ሊጋለጥ መሆኑ እውን ስለሆነ ከፍተኛ ስጋት ስለተፈጠረባቸው በአብይና ለማ ላይ በየትኛውም አመክንዮ ሊታሰብ የማይችልና ያልታይ ወሬ መንዛት ጀመሩ፡፡ እርግጥም ሰሚ አላጡም ምክነያቱም ቀድመው በጭፍን ደጋፊነት በደቦ የሚከተላቸው ብዙ ተከታይ አፍርተዋልና ነው፡፡

እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ብዙ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ከመናቃቸው የተነሳና እኔን የሚከተል ብዙ ደጋፊ አለኝ በሚል በእብሪት ተወጥረው እንደፈለጋቸው ያወራሉ፡፡ እርግጥ ነው ደጋፊያቸው ብዙ ነው፡፡ ዛሬ ወለጋ ከኦሮሞም ተነጥሎ ዋና መጠቀሚያ መሳሪያ እየሆነ ነው፡፡ አእምሮ ላለው የወለጋ ከሌላው ተለይቶ አሁን እያየን ያለንውን እየሆነ ያለው በእነዚህ የሕዝብና አገር ጠላቶች መርዘኛ አመለካከት አዚም ተደርጎበት እንጂ ታግሎ ከማን ነጻ ሊወጣ እንደሆነ እንኳን እንደፈለገ ሊያስተውል በተገባው ነበር፡፡ በቀለ ገርባና ጀዋር ወለጋ ሄደው ሕዝቡን እንዴት በስሜት ሲያፈዙትና ለንግዳቸው ሲያመቻቹት እንደነበር አይተናል፡፡ ሲዘመርለት የነበረው በቀለ ገርባ በዘረኛና በጥላቻ የመረቀዘ አስተሳሰቡን በራሱ አንደበት ነው የሰማነው፡፡ ያሳዝናል! እንዲህ ደፍሮ የሚናገረው ቢያገኝ ከጅምሩ ሊያርመው በቻለ ነበር፡፡ አሁን ራሱ አደባባይ በአወጣው የዘረኛ አመለካከቱ የሌለውን ክብር ብንጭንለት አይሆንም፡፡ በቀለ ከጅምሩ እንደሌሎቹ የወያኔ ዳረጎት ተቀባይ እንደነበር ባናውቀውም አሁን ላይ ግን ወያኔ ኦሮሞን እንዲያፈዝላት ከተከፈላቸው ሊሆን እንደሚችል እያሰብን ነው፡፡ ሌሎቹ ግን በውጭ በአክቲቪስትነት የኦሮሞ ሕዝብ ዋና ወካይ ሆነው የምናውቃቸው ከወያኔ ጋር የቆየ የጥቅም ወዳጅነት የነበራቸው ናቸው፡፡ ኦነግ የተባለውን የሚመሩት ደግሞ ከጅምሩ ጀምሮ የወያኔ ልዩ ሚስጢራዊ ወዳጅ እንደሆኑ አለማስተዋል ያሳዝናል፡፡ ያም ሆኖ ዛሬ ላይ ግልጽ ሆኖ የኦሮሞን ሕዝብ አሁንም ለወያኔ መሳሪያነት በግልጽ እንዲውል በማድረግ እየነገዱበት እያየን የተለያየ ማስተባበያ ሊሰጥ ሲሞከር እናስተውላለን፡፡ አሊያማ በምን መስፈርት ነው ኦሮሞ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትንና ትግሉን ወደነጻነት የመሩለትን መሪዎቹን የሚጠላበት ምክነያት፡፡ ከዚህስ በላይ ምን ይፈልጋል፡፡

የኦሮሞን ሕዝብ ስነልቦና በተራ ምናምቴዎች ሳይቀር ተገዥ እንዲሆን አድርገው ሲነግዱበት የቆዩት እነጀዋር ዛሬም የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ ያስገቡት በራሱ ሎጂክ የማያስብ በብዛት ደጋፊ ተጠቅመው በየቀኑ እየተገለባበጡ ይጫወቱበታል፡፡ እነጀዋር ከወያኔ ጋር አጋር ለመሆን ሕዝብ ምን ይለናል ሳይሉ ሰርተዋል፡፡ የሚገርመኝ አዚም አላቸው መሰለኝ እስከዛሬ ብዙ ኦሮሞ የአምልኮት ያሕል ነበር የሚከተላቸው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ በጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ከተሰበከ በቂ ነው ብላ የምታምነው ወያኔ ያሰማራቻቸውን እንደነ ጂጂ የተባለች ሴት ያሉ እጅግ አሳፋሪ የሆኑ ግለሰቦች ሳይቀር ነበር በኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ ይነገርበታል በተበለው የትላንታው ስብሰባ ያየናቸው ከዛም በላይ ልዩ እንግዳ ሆነው የነበሩት፡፡ ኦኤም ኤን ልክ እንደ ልዩ ተንታኝ ኢንተርቪው ሲያደርጋት ነበር፡፡ ዛሬ ሌላው ኦኤንኤን የተባለው ኦነግ ይመራዋል የሚባለው ሚዲያ ምን እየሰራ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ከጅምሩ ተናግሬ ነበር ኦሮሞ ሁሉ ራሱን ከእነዚህ አዚም ከሆኑበት ነጻ ከአላወጣ መከራው ይቀጥላል፡፡ ለሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝብም ችግር ይሆናል፡፡

ሰላምን ራሳቸው እያደፈረሱ መንግስት ሕግና ስርዓት አላስከበረም ይሉኃል፡፡ ሕግና ሥርዓት ለማስከበር ሲሞክር ኦሮሞን አጠቃ ይሉሃል፡፡ አብብ ሞኝን ሁለቴ ነደፈው! እኛን ግን ብዙ ጊዜ ነደፈን፡፡ ሰሞኑን እነ ጀዋር የተነቃባቸው ስለመሰላቸው ተንከረባብተው የመንግስት ደጋፊ ለመምሰል ሲቀበጣጠሩ እናያለን፡፡ በቀለ ግን እዛው የተጠመቀበት የዘረኝነት አባዜው ውስጥ ነው፡፡ ዳውድ 40 ምናምን አመት ኦሮሞን በነጻነት ስም እያስፈጀ ሲነግድበት እንደነበረ ተዘንግቶለት በሰላም ቢጠራም ዛሬም ኦሮሞን አለቀቀውም፡፡ ሰሞኑን ዳውድ ኦሮሞ አደለም የሚሉ ብዙዎች መጥተዋል፡፡ ማንም ይሁን ኦሮሞም ይሁን፡፡ ቁም ነገሩ በመጀመሪያ ከዘር ማንነቱ ሳይሆን የኦሮሞን ሕዝብ እንዴት እየነገደበት እንዳለ ሴራውን ማስተዋል ነው፡፡ ወያኔ ኦሮሞንና (በአብዛኛው በኦነግ ሥም) ሌሎችንም ስታርድ ኮሽ ያላለው ሰውዬ ነው ወያኔ አደጋ ላይ ስትወድቅ በያለበት ችግር መፍጠር የጀመረው፡፡ ትልቁ ሌላው ችግር በኦሮሞነት ወለጋና ባሌም እኩል መታመሱ ነው፡፡ ኦነግን እንመራነልን የሚሉትና ተባባሪዎቹ ደግሞ ከዛው ከወለጋ የተጠራቀሙ ናቸው፡፡ ይህንም እንዳያስተውል አዚም አላቸው መሰለኝ፡፡ በኦሮሞነት አጭቀው ሁሉንም መሳሪያ እያደረጉት ነው፡፡
ኦሮሞ ሆነ ሌላው በደቦ አመለካከት የሚነዱህን አምቢ በል! ነጻነትህን ማስከበር የራስህ ድርሻ ነው! በዚህ አጋጣሚ ምሁር ነን በሚሉ በብዙ ኦሮሞዎች አዝኛለሁ፡፡ ማንም ምንም እንደማያመጣ አውቃለሁ! ጉዳዩ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰውም እንዳልሆን ከጅምሩ ስለማውቅ፡፡ ግን ከዛ ሁሉ ችግር ወጥተን ዛሬ ተስፋ በሆነልን ሁኔታ ተመስግን ከማለት ይልቅ በገዛ ፍቃዳችን ለምናመጣው ችግር እርግማን እንዳይሆን አሰጋለሁ፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!