December 28, 2018 257
በስልጣን ላይ ያለው ‘የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር’ ተብሎ የሚታወቀው የአራት የፖለቲካ
ድርጅቶች ጥምር አካል ነው። ከነዚሁ መካክል ቀንድ የነበረው ‘የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር’ የተባለው አካሉን የፈጠረው አሁን ከሌሎቹ በመለየት አምጾ በሽፍተኝነት መቀሌ ከተማ ተመሽጎ ይገኛል። ከዚያ አካባቢ የሚነፍሰውን አሳፋሪ ወሬ የደሴ አዝማሪዎች በጠላ ቤት መዝናኛ አርገውታል። ከዚያ ባለፈ፣ አሁን የኢትዮጵያን ህልውና የሚከላከሉት ወጣቶች በብዙሃን መገናኛ ተቋማት የጊዜ ማሳለፊያ ዜና አርገውታል። በሌጣ አስተሳሰብ፣ በዚህ ወቅት ደስታን መርጨት ወደር የሌለው የአዕምሮ ህክምና ነው። ከዚህ ለየት ባለ መልክ ደግም ሰፊውን ጊዜ፣ ትልቅ ቁምነገር ባለው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪ ክቡር ጠ/ም ዶ/ር አቢይ የጀመሩትን መሰረታዊ ለውጥ ግንባታ ስራ ከግቡ እንዲደርስ ዜናውን በየደቂቃው ያስተጋባሉ። ኢትዮጵያ የተባረከች ሀገር በመሆኗ የተባረከ ትውልድ በየዘመኑ ይፈጠራሉ። ይህን የሚያረጋግጥ ያለንበት ወቅትና ጊዜ አንዱ ነው።
