አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአቶ ገለሣ ዲልቦ የሚመራ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አመራርና አባላት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በአቶ ገለሣ ዲልቦ የሚመራው አመራርና አባላት አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት አመራሮችና አባላት 22 ሲሆኑ መንግስት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር መመለሳቸወን አስታውቀዋል፡፡
በለይኩን አለም
