December 31, 2018

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
‹‹በምን አወቅሽበት በመመላለሱ፣ ሲታሰር ወደእኔ፣ ሲፈታ ወደእሱ፡፡›› ለህወሓትና ኦነግ
<<ሕይወት ማለት መብላትና መጠጣት፣ አዳዲስ ልብስ እያፈራረቁ መልበስ፣ ከባንክ ገንዘብ ማጠራቀም፣ አዲስ ‹‹ሞዴል›› መኪና ምንዳት፣… ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ በቀላሉ መንገድ ሊገኝ እንደሚችል አይተናል፡፡ ስብአዊ ክብር ግን በገንዘብ አይገዛም፡፡ ሐሪሶት (culture) የሌለው ሰብአዊ ክብር ምን እነደሆነ ማወቅ አይቻልም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጋጠመው ዋና ፕሮብሌም ነው፡፡>> 1 ብርሃኑ ድንቄ
ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የጦር አበጋዞች መንግስት ወደ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) የጦር አበጋዞች መንግስት በትረሥልጣኑን ለማራዘም ያሸጋገረበት የቅርብ ጊዜ ትዝታ በሽንፈት ተጠናቆል፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተስፋ ባለመቁረጥ አሁን ደግሞ ከመቐሌ ምሽጉ ስፖንስር በሚያደርገው ገንዘብና መሣሪያ ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የጦር አበጋዞች መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይ በወለጋ፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ወዘተ ትጥቅና ስንቅ በማቅረብ ሠላም በማደፍረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ህወሓት የዶክተር አብይ አህመድን አዲሱን ለውጥ ለማደናቀፍና በመላ ሃገሪቱ የሽብር ሴራ በመዘርጋት የዴሞክራሲውን መንገድና ነፃነት በመፈታተን ላይ ይገኛል፡፡ በሃገሪቱ የህግ የበላይነት ስለሌለ፣ ትላንት የፈፀሙትን ወንጀል ዛሬ ደግመውታል፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ ተጠያቂ ከሆኑ፣ የህዝብ ግጭቶችን በእንጭጩ መቅጨት ይቻላል እንላለን፡፡ ህወሓት የሶህዴፓ አብዲ ዒሊ የጦር አበጋዝ መንግሥት ሽንፈት በሆላ አዲስ ያገኘው መጋዣ የኦነግ ዳውድ ኢብሳ የሚመራ የፊንፊኔ የጦር አበጋዝ መንግሥት ጋሻ ጃግሬነት የተሰባሰቡት የሥልጣን ሱሰኞች በአሳዛኙ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ሃላፊ ጁሃር መሃመድ አንደበት የኦሮሞንና የኢትዮጵያን ደሃ ህዝብ ደም በማፋሰስ ላይ ናቸው፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች በዘር ግንድ ላይ የተመሠረተ የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም፣ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ስም፣ በዘር የተደራጀ ጦር በማሰልጠንና በመገንባት ሌላውን ዘር በማግለል የራሳቸውን ግዛትና መንግሥት በሌላው ላይ ለመጫን የተደራጀ ኃይል ያቆቁማሉ፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን ኦነግ በወለጋ መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠት ማዕከላዊውን መንግሥት በመፈታተን ላይ ይገኛል፣ በቃህ ሊባል ይገባል እንላለን፡፡የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግሥት ከወያኔ ጋር በመመሥረት በጊዜው በደኖ፣ አርባጉጉ፣ ወዘተ ህዝብ ላይ ያደረሰው የዘር ፍጅት ተጣርቶ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ አለመደረጉ ዛሬ ኦነግ በሃገሪቱ ውስጥ ወንጀል ለመስራት የተላላኪ ሚናውን በመወጣት ላይ ይገኛል ስለዚህ ከሁሉ በፊት የህግ የበላይነት መከበር ይኖርበታል እንላለን፡፡ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ሃላፊ ጁሃር መሃመድ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት በሥራ አስፈፃሚው መንግሥት የቀረበለትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቆቆሚያ ረቂቅ አዋጅን በመቃወም ከህወሓት ጋር ህብረት ፈጥሮል፡፡ ባለፈው ጁሃር መሃመድ በአዲስ አበባ ተገደሉ ያላቸው የ43 ኦሮሞ ሞቶች የስም ሊስት ውሽት በህግ ሳይጠየቅና በህግ ፊት በቃ ሊባል ሲገባ ዝም መባሉ ህግ ለእሱ እንደማይሰራ በእብሪት ያሰኘውን መናገር መቻሉ በቃህ ሊባል ይገባል እንላለን፡፡ ህግ በሌለበት ሃገር የማፍያ ሥርዓት የሚያራምዱ ህገ ወጥ ወንጀለኞች ይፈለፈላሉ፣ የህዝቡን ሠላምና ጸጥታ ማስከበርና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ካልተረጋገጠ ሃገሪቱ በዘር የተገነባ የጦር አበጋዞች መንግስት ሥር ዳግም ትወድቃለች እንላለን፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር አውሮፕላኖች፣ ታንኮች፣ የጦር ግምጃ ቤት ክምችት ወያኔን ለእብሪት ስራው ዳርጎታል በአፋጣኝ ወደነበረበት ቦታ መመለስ አለበት ፈርቶ ዝም ማለት ውሎ አድሮ ያስከፍላል፡፡
የህወሓትና የኦነግ የኢኮኖሚ አሻጥርን በህዝባዊ የራስ መተማመን (Selfe Reliance) ፖሊስ እንመክት
የዶክተር አብይ መንግሥት አዲስ ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) በመንደፍ የኢትዩጵያ መንግስት በግብርና ታክስ ልዩ ልዩ አሻጥሮች ያልተሰበሰበ ግብርን በልዩ ልዩ ገቢዎች ማጠናከር ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን የመቀነስ ፖሊሲን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ተመጣጣኝ እንዲሆን እርምጃ መውስድ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ መንግስት የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን ማጠናከር እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን መቀነስ አስፈላጊ እርምጃ መውስድ ይኖርበታል፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥትና በመላ ሃገሪቱ ሽብር ስፖንስር በማድረግ ህገወጥ ገንዘብና መሣሪያ በማሰራጨት ህዝቡን ሰላም በማሳጣት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሽመደመድ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ የወያኔን ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል የኢኮኖሚ አቅም ድባቅ ለመምታት የገንዘብ ገቢያቸውን ምንጮች ማድረቅ፣ የመሣሪያ ስርጭታቸውን መቆጣጠር በተከታታይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤ የግብርና ታክስ ስርዓት ገቢ እያሽቆለቆለ መሄድ አንዱ አሻጥር መሆኑን በመረዳት መንግሥት ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮችን መፈለግና የመንግሥት ወጪዎችን በመቀነስ ይሄን የኢኮኖሚ አሻጥር መግታት ይችላል እንላለን፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2009 ዓ.ም 50 ቢሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ግብር ጉድለት ነበረበት፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ2010ዓ/ም 213 ቢሊዮን ብር የታክስ ገቢ እንደሚያሰባስብ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹መብቴን እጠይቃለሁ፣ ግዴታን እወጣለሁ ››
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 10 ቢሊዮን ብር በአንደኛው ሩብ ዓመት መሰብስብ አልቻለም፡፡ የ2011 ዓ/ም መጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት፣ በ2010ዓ/ም በጀት አመት የፀደቀው 346.9 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 241.94 ቢሊዮን ብር ገቢ ከታክስና ሎሎች ገቢዎች በመሰብስብ ለመሸፈን የታቀደ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአገር ውስጥ ገቢ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲሰበሰብ የታቀደው ገቢ 28.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን አፈጻጸሙ 25.62 ቢሊዮን ብር በመሰብስብ በእቅድና በክንውኑ መካከል የ3.2 ቢሊዮን ብር ልዮነት ታይቶል፡፡ እንዲሁም ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ አልተቻለም፡፡ በአጠቃላይ ከአገር ውስጥ ገቢ (3.2) ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ከታቀደው የታክስ ገቢ ውስጥ 10 ቢሊዮን ብር መሰብስብ አልተቻለም፡፡ በመጪዎች ሩብ ዓመት የታክስ ገቢ መሰብስብና እንዳይቀንስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ፡፡
ህገወጥ የድንበርና የኮንትሮባንድ ንግድን፣ የምንዛሪ፣ የጥሬ ገንዘብና፣ የጦር መሣሪያ ዝውውርን መግታት ይኖርብናል፡፡
በየከተሞቹ ያሉ የህንፃ ግንባታዎች ሥራ መቀዛቀዝና የስራ አጥነት ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት በመሆኑ አዲስ የሥራ ፈጠራ ፕሮግራም መንደፍ ያስፈልጋል፡፡
የውጭ ንግድ ገቢ እንዲጨምር ማድረግና የገቢ ንግድ ወጪ እንዲቀንስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
መንግሥት በራስ የመተማመን (Selfe Reliance) ፖሊሲ መቅረስ ይኖርበታል
{1} የሼህ መሃመድ አላሙዲን ሜድሮክና የህወሓት ኢዛና የወርቅ ማዕድን አውጭ ኩባንያዎች ከብሄራዊ ባንክ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ስውር መመሪያና በቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አቶ ሶፍያን አህመድ ወርቅ በህገወጥ መንገድ በመሸጥ የወንጀል ተግባር ላይ በመገኘታቸው የወርቁን ማዕድን በመውረስ አዲሱ መንግስት እስከ 500 ሚሊዩን ዶላር በአመት የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላል እንላለን፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥሩን መንግሥት በዚህ መሰል እርምጃ መከላከል ይቻላል እንላለን፡፡
{2} ኦዴፓ/ ኢህአዴግ መንግሥት በራስ መተማመን (Selfe Reliance) አዲስ ፊሲካል ፖሊሲ፤ በመንደፍ የፌዴራልና የክልል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶችን የህዝብ ኃብትና ንብረት በማድረግ ገቢውን በትንሹ ከአምስት እስከ አስር ቢሊዮን ብር ገቢ በአመት መሰብሰብ ይችላል እንላለን፡፡ የህወሓት፣ብአዴን፣ ኦህደድ፣ ደኢህዴን የፖለቲካ ድርጅቶችና የንግድ ድርጅቶች የኢፈርት፣ ጥረት፣ ዲንሾና ወንዶ የከተማ ቤቶች ቅርምት፣ መንግሥት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶችን የህዝብ ኃብትና ንብረት በማስመለስና በአለው የቤት ገብያ ዋጋ ቢያከራይ ብዙ ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ይችላል፡፡ ‹‹የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከታኅሳስ ወር መጀመርያ ጀምሮ በ6,635 የንግድ ቤቶቹ ላይ የኪራይ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡›› የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ‹‹… የሚያስተዳድራቸው ቤቶች ላይ የክፍያ ተመን ማስተካከያ ሳያደርግ ለበርካታ ዓመታት በመዝለቁ፣ የኪራይ ዋጋው ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ ቆይቷል ሲል አስረድቷል፡፡ የክፍያ ዋጋውም ከግሉ ዘርፍ ጋር ከፍተኛ ልዩነት ያለው በመሆኑ የንግድ ውድድሩ እንዲዛባ አድርጓል በማለት የሚገልጸው ኮርፖሬሽኑ፣ የአሁኑን ጭማሪ በመቶኛ ማስላትም አግባብ ካለመሆኑም በላይ አሁንም ቢሆን ከግሉ ዘርፍ ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው ብሏል፡፡›› የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ‹‹… የንግድ ቤቶችና ድርጅቶች የክፍያ ተመን ለማሻሻል ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ጥናት ሲካሄድ ነበር ብሏል፡፡ የጥናቱ መነሻ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ሪፎርም በዜጎች መካከል የተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር መፈለጉ ነው ሲልም አክሏል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የንግድ ቤቶች መካከል የተለያየ የክፍያ ተመን እየተተገበረ በመሆኑ፣ በደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎች ለመፍታት ባልተመጣጠነና ገበያውን ባላማከለ የኮርፖሬሽኑ ተመን ምክንያት ያላግባብ በአቋራጭ የበለፀጉ ዜጎች በመፈጠራቸውና ለችግሩ ፍትሐዊ ምላሽ መስጠት አስፈልጓል ብሏል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች የክፍያ ተመን አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት የተለያዩ ሕገወጥነት ያላቸው ክስተቶች መፈጠራቸው በተለይም የሦስተኛ ወገን የአከራይ ተከራይና ቁልፍ ሽያጭ ለማስቀረት፣ የኮርፖሬሽኑ ቤቶች ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ስለሆነ ለጥገና፣ እንዲሁም አዳዲስ ሕንፃዎችን ለመገንባት ከዚህ የተሻለ አማራጭ ወቅት የለም ብሏል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እንደሚለው የሚያስተዳድራቸው ቤቶች የክፍያ ተመን ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ከግሉ ዘርፍ አንፃር ሲታይ ደግሞ አሁንም ከፍተኛ ልዩነት አለው፡፡ ለአብነት ኮርፖሬሽኑ እንደገለጸው ከ6,635 የንግድ ቤቶች ውስጥ 279 ያህሉ በካሬ ሜትር ከአንድ ብር በታች እንደሚከራዩ፣ 2,057 የሚሆኑት የንግድ ቤቶች ደግሞ በካሬ ሜትር ከአሥር ብር በታች እየተከራዩ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲሱ የኪራይ ጭማሪ መሠረት በካሬ ሜትር እያሰላ ማስከፈል የሚጀምር ሲሆን፣ በካሬ ሜትር እስከ 500 ብር መጠየቁ ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ በማድረግ የረጅም ጊዜ ደንበኞችን ማመሰቃቀል፣ ከበስተጀርባው የተደበቀ ሴራ አለው ሲሉ ተከራዮች ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ግን አሁን ካለው የገበያ ዋጋ አንፃር እንዲህ ያለ ብሶት ማቅረብ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት የካፒታል ሆቴል ስብሰባ ወቅት አንዳችም ተቃውሞ ሳይቀርብ ስምምነት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል፡፡››
{3} የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት፣ የቀድሞው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ በደርግ መንግስት በአዋጅ የተወረሱ ቤቶችን እንዲያስተዳድርና አዳዲስ ቤቶችን እንዲገነባ የተቆቆቀመ ድርጅት ነበር፡፡ከ1983 ዓ/ም ወዲህ አዳዲስ ቤቶች እንዳይገነባ ፣ ያሉትን ቤቶች ብቻ እንዲያስተዳድር ተወስኖበት ነበር፡፡ ከ26 ዓመታት በሆላ ደግሞ፣በየካቲት ወር 2009 ዓ/ም እንደ አዲስ በድጋሚ የተቆቆመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን፣ በማስተር ፕላኑ ዞን 3 እና 4 ውስጥ እስከ 10 ፎቅ የሆኑ በአጠቃላይ 16 ሽህ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ አውጥቶል፡፡ ቤቶቹ ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በኪራይ ለማስተላለፍ ነው፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ዜጋ በ10/ 90፣ በ20/ 80 እና በ40/60 ቤቶች ተደራጅተው ቤት ሊገነቡ ሲገባ በህዝብ ገንዘብ በግብር ከፋዩ ደም የኪራይ ቤቶች ሊያገኙ አይገባም፡፡ ከ37 ሽህ ህዝብ በላይ የቤቶች መስሪያ የቁጠባ ሂሳቡን ሲዘጋ የህዝብ የቁጠባ ባህል ተስፋ በመቁረጥ አብሮ እንደቀበራችሁት የሚረዳ ህሊና ቢኖራችሁ ዛሬ ቆጥቦ ቤት የሚሠራውን ወገን በመርዳት 33 ቢሊዮን ብር ግንባታችሁን፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ለሠራተኞች በየትኛው መልካም አስተዳደር ስነምግባራቸው፣ የሞራል ብቃታቸውና፣ ስብዕናቸው ነው በግብር ከፋዩ ገንዘብ ቤቶች የሚገነቡላቸው ይሄ አሠራር በመንግሥት በጀት፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ማድረግ የጥቅም ግጭት፣ መጠቃቀምና፣ የአድልኦ አስራርን በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ መንግሥት ቤት ለሌላቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎቹን ቤቶች ሠርቶ ሲያከራይ እንጂ መስራት ለሚችሉና ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ሲደጉም ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅ እንላለን፡፡ የፓርላማ አባላቶች ከመንግሥት ኪራይ ቤቶች ተሠጥቶቸው ይኖራሉ፡፡ ለመከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች በሲግናል ካንፕ፣ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት አካባቢ፣ገነት ሆቴል ምርጥ ኮንዶሚንየም ቤቶች ተሠርተው ለወያኔ ጀነራል መኮንኖች ተሠጥቶል፣ ብዙዎቹ መሬት በነፃ ተሰጥቶቸው ቤት ሠርተው ያከራያሉ፡፡ ለደህንነት ሠራተኞች ከመንግሥት ኪራይ ቤቶች ተሠጥቶቸው ይኖራሉ፣ብዙዎቹ መሬት በነፃ ተሰጥቶቸው ቤት ሠርተው ያከራያሉ፡፡ ከመንግስት ቤት ተከራይተው ቤት ሠርተው የሚያከራዩትን ወያኔ ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ቪላ ቤቶች አስለቅቆ በገበያ ዋጋ ማከራየት የመንግሥት ገቢን ይጨምራል እንላለን፡፡
{4} በፊዴራል ደረጃ ካሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል 77 ቢሮዎች፣ የራሳቸው ቢሮዎች/ህንፃ የሌላቸው ስለሆነ የግለሰብ ህንፃን እንደ ቢሮዎች ተከራይተው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡ አከራዬቹ የህወኃት/ ኢህአዴግ ሹማምንቶችና የጦር መኮንኖች እንደሆኑ መረጃውን የምታውቁ በማጋለጥ መተባብ ይኖርባችሆል፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት ከሹማምንጹ በአስለቀቃቸው ቪላ ቤቶችና መኖሪያ ቤቶች የራሱን ቢሮዎች በማዘዋወር በወር 31.6 ሚሊዮን ብር በዓመት 380 ሚሊዮን ብር የመንግሥት ወጪን መቀነስ ይችላል እንላለን፡፡ በኢኮኖሚ በራስ መተማመን እንዲህ ነው እንላለን፡፡
{5} ዲያስፖራው ወገናችን ቃል የገባውን እንዲፈፅም ቅስቀሳውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡
ምንጭ፡-
1- ብርሃኑ ድንቄ አልቦ ዘመድ መጽሃፍ የተወሰደ፡፡
2-ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ቤቶች ኮርፖሬሽን ባደረገው የንግድ ቤቶች የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ደንበኞች ቅሬታ አቀረቡ›› 23 December 2018
3- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ‹‹ለቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊዘጋጅ ነው ››16 December 2018
4- ሪፖርተር ጋዜጣ፣ በኢንሳ ሶፍትዌር ምክንያት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ቀን ተራዘመ 11 November 2018
