“…..ኢትዮጵያ ምትላት የቷን ነው? አማራውን እስከ ነፍሱ አሰቦት ገዳም ገደል የጣለችውን እንቁፍቱ ላይ የአማራን ሴቶች ማህፀን የቀረደደችውን ነው ቤንች ማጅ ላይ ያፈናቀለችውን ኢትዮጵያ….!”

ለዚህ በእጅጉ የተሳሳተ ወያኔያዊ አስተያየት ቢጨንቀኝ እንዲህ ብየ መለስኩ፦

“”ኧረ ባክህ እውነትህን ነው??? ኢትዮጵያን እንዲህ ዓይነት ግፍ በአማራ ላይ ስትፈጽም አየሃት??? ምን ዓይነት ልብስ ነበር የለበሰችው ባክህ??? ጠይም ናት ወይስ ቀይ እስኪ ንገረን??? ወያኔ እንዲህ እያለ ነው የመረዘሽና ኢትዮጵያን እንድትጠይ ያደረገሽ??? ይሄውልህ ይሄንን ሁሉ ግፍ በአማራ ላይ የፈጸመውና ያስፈጸመው “ኢትዮጵያ ናት!” እያለ የመረዘህ ወያኔና መሰል የጥፋት ኃይሎች ናቸው እሽ ኢትዮጵያ አይደለችም!!! ወያኔ አደንቁሮህ ነው እንጅ ይሄንን ለመረዳት የሚከብድ አልነበረም!”” ብየ መለስኩ፡፡

በተለያየ ጊዜ ተመሳሳይ አስተሳሰቦችን የአብን አመራሮች ሲሰነዝሩ ተመልክታቹሃል፡፡ አሁን ታዲያ እነዚህ ለአቅመ ፖለቲካ ጨዋታና ኃላፊነት አይደለም ለመሸታ ቤት ጨዋታ እንኳ የሚበቁ ናቸው???

በሌለ እሳቤና የተሳሳተ ትርክት ሀገርን ኢትዮጵያን (የአማራን የእጅሥራ፣ የደም ብቃይ፣ የማንነት መሠረት) ጠላት አድርጎ ፈርጆ ከተነሣና “ጠላትህ ኢትዮጵያ ናት!” እያለ ትውልድን ከሚመርዝ፣ ከሚያደነቁር፣ አንድነትን ከሚያብጠለጥል ከሚኮንን የደነቆረ የጥፋት ቡድን ሰው እንዴት በጎ ውጤት ይጠብቃል??? እንዴት ተስፋ ያደርጋል??? ምን የሚሉት መደንቆር ነው ይሄ??? ያልዘሩት ይበቅላል እንዴ??? እንክርዳድ ተዘርግቶ ስንዴ ይታጨዳል እንዴ???

አማራን ለማንነቱ፣ አደጋ ላይ ላለው ህልውናው ለማታገል ኢትዮጵያን መርገም፣ ሀገርን ማስጠላት፣ አንድነትን ማብጠልጠል፣ ጠባብነትን ማስታጠቅ ግዴታ ስለሆነ ወይም ይሄ ካልተደረገ በስተቀር አማራ የማይነሣ ስለሆነ ይመስላቹሃል ጭንጋፎቹ ይሄንን የሚያደርጉት???

እርግጥ ነው ኢትዮጵያን እንደጠላት ሀገር የሚቆጥርን፣ ጠባብነትና ባንዳነት የተዋረሰውን ጎሳና ብሔረሰብን ፀረ ኢትዮጵያ ጠባብ ስብከትን ካልሰበኩት ላይነሣሣ ላይቀሰቀስ ይችላል አይችልምም፡፡ በዚህ ምክንያት እነወያኔ በዚህ መንገድ ተጉዘው ሕዝባቸውን ቀስቅሰው ማነሣሣትና ማታገል ችለዋል፡፡

አማራ ግን አማራ ነው ትግሬ ወይም ሌላ አይደለም!!! አማራ ጠባብ አይደለም!!! ባንዳ አይደለም!!! ሀገሩን እንደጠላት ሀገር የሚቆጥርና ፀረ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ የተጠናወተው አይደለም!!! ስለዚህም ትግሬ ላይ የሠራ ፀረ ኢትዮጵያና ጠባብ የማነሣሻ ስብከት አማራ ላይ አይሠራም!!! ደናቁርቱ መገንዘብ የተሳናቸው ይሄ ነው፡፡

አማራን በቁጭት ሊያነሣሣው፣ ሊቀሰቅሰው የሚችለው የጥፋት ኃይሎች ጠላቶቹ ጠላት ሀገሮችን ከጎን አሰልፈው ከትልቅነቱ እንዳወረዱት፣ ስንት የሆነላት ሀገሩን ቀምተው በገዛ ሀገሩ ተሳዳጅ ተፈናቃይ ተንከራታች እንዳደረጉት፣ ጭራሽም ዘሩን ከዚህች ሀገር አጥፍተው ሀገሩንና ያለውን ሁሉ ለመውረስ ተግተው እየሠሩ እንደሆነና የራሱንና የሀገሩን ህልውና ለመታደግ የግድ ቆርጦ ጨክኖ ያለመነሣት ምንም አማራጭ የሌለው መሆኑን መንገሩ ነው ከበቂ በላይ አነሣሽ፣ ቀስቃሽ፣ አሳማኝ፣ አስቆጭ፣ የሚያንገበግብ የሚሆነው፡፡

ጭንጋፎቹ (ቀደም ሲል ቤተ አማራ ነኝ የሚለው የጥፋት ቡድን አሁን ደግሞ የቤተ አማራ ውላጅ ነኝ የሚለው የጥፋት ቡድን አብን) ይሄ ጠፍቷቸው እንዳይመስላቹህ ከዚህ በተቃራኒ ወይም ወያኔያዊ በሆነ አቅጣጫ በመንጎድ አማራን ለመቀስቀስ ጥረት እያደረጉ የቆዩትና ያሉት??? አይደለም!!! የተሰጣቸውን የወያኔን የጥፋት ተልእኮን ለማሳካት እንጅ!!!

እኔ ምን ዓይነት ሰው ከዚህ እንጭጭ፣ ያልበሰለ፣ ያልበሰለ ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ ሊበስል ሊለወጥም ከማይችል (ተመርዞ የጥፋት ተልእኮ ተሰጥቶት የተሰማራ ቡድን ነውና) ከዚህ ቡድን እንዴት በጎ ውጤትና ሀገርንና ሕዝብን ሊጠቅም የሚችል ስኬት ሊጠብቅ እንደሚችል ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም!!!

የነሱ ቢጤ እንጭጭ የወያኔ የጥፋት ስብከት ሰለባ የሆነ ድኩም ዜጋ ካልሆነ በስተቀር መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ መናገር እችላለሁ ማሰብ ማሰላሰል የሚችል፣ የአባቶቻችን መንፈስ ያደረበት ኩሩ አማራ ከእነዚህ ዝጋጭና ጭንጋፎች ጋር ሊሰለፍ አይደለም ባለፉበት እንኳ አያልፍም!!!

በርካታ የአማራ ወጣት እነሱን ካለማወቅ የተነሣ፣ ለመደራጀት ካለ ከፍተኛ ፍላጎትና አስገዳጅ ሁኔታዎች የተነሣ አብሯቸው ተሰልፏል፡፡ ወያኔስ ይሄንን አውቆም አይደል እንዴ ለውጥ ባለው ጊዜ አማራ አጋጣሚውን በመጠቀም ትክክለኛው የአማራ ድርጅት በታማኝና ዋጋ በከፈሉለት ልጆቹ ከመመሥረቱ በፊት ተሽቀዳድሞ ይሄንን የቅጥረኛ ቡድን ያቋቋመው???

አብን ውስጥ ያለውን የአማራ ወጣት ይሄ የእንጭጮቹ የጭንጋፎቹ ቡድን በአማራነቱ ፈጽሞ እንደማይመጥነው እየነገርን ከዚህም በላይ በገዛ እራሱ ላይ ጠላት እየሆነ መሆኑን በማስረዳት ከእጃቸው የማስወጣት ግዴታ በእያንዳንዳችን ላይ አለብን!!!

ዋነኛ የቤት ሥራችን ግን እንደምንም ብለን አማራን የሚመጥን ማለትም ክብሩን፣ ኩራቱን፣ ማንነቱን፣ ታሪኩን፣ የሥነ ልቡና ልዕልናውን፣ ሥልጣኔውን፣ ቀዳሚነቱን፣ መሪነቱን፣ ገናናነቱን፣ ጀግንነቱን ወዘተርፈ. የሚመጥን ትክክለኛ የአማራ ድርጅትን በትክክለኛ፣ ታማኝ፣ አስተዋይ፣ የበቁና ቆራጥ አማሮች መመሥረት ይኖርብናልና እባካቹህ ወገኖች ሆይ ግድ የላቹህም ያለቀናቹህ አትሞቱም አትፍሩ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለን ይሄንን የአማራ ድርጅት ለመመሥረት እንረባረብ???

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com