January 6, 2019 t

ለትግራዋይ ዲጂታል ዘመን ወጣቶች የምታጡት የታሰራችሁበትን የህወሓት የባርነት ሠንሠለት ብቻ ነው!!! ትግራይ ነፃ ሳትወጣ ኢትዮጵያ ነፃ አትወጣም!!! ጥንትም ዛሬም ታሪካችን አንድ ነውና!!! በፎቶግራፍ የኢትዮጵያ ዜጎች ታሪክ ዛሬም ይናገራል!!!

(ክፍል አንድ) ፀት ፂዮን ዘማርያም

ልጅህንም፣ አባትህንም ስታጎርስ
ላንዱ ታበድራለህ፣ላንዱ ትከፍላለህ
ደግ አባት ርስት ያቆያል፤
መጥፎ አባት ዕዳ ያቆያል፡፡››

የአባቶች ብሂል ከ1928 አስከ 1933ዓ/ም በተደረገው የኢትዮጵያና የጣሊያን ቀኝ ገዥ ጦርነት በተደረገ የነፃነት ትግል አባቶቻችን ‹‹ያለጥርጥር ዛሬ (Guerrilla warfare/ ሽምቅ ውጊያ) እየተባለ የሚጠራው ውጊያ የተጀመረው በኢትዮጵያ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ታላቅ መንግስት ወታደራዊ ድርጅቱንና የጦር መሣሪያ ብልጫውን በመተማመን፣ ፈቃድ የሌለውን አነስተኛ አገር በኃይል ለመግዛት እንደማይችል በአምስቱ ዓመታት የኢጣሊያ ይዞታ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ አርበኛች ሚበቃ ማስረጃና ማሳሌነትን ሰጥተዋል፡፡ በሸዋ እነ አበበ አረጋይ፣መሥፍን ስለሺ፣ ኃይለማሪያም ማሞ፣ በጎጃም እነ መንገሻ ጀምበሬና እነ በላይ ዘለቀ፣ በትግሬ እ ገብረ ሕይወትና ዓባይ ፣ በደቡብ እነ ገረሱ ዱኪና እነ በቀለ ወያ….ያሳዮት ጀግንነት የሚያስገርም ነው፡፡ ግን የቤተ ማኅ ተም (Press) አገልግሎት እንደዛሬው ሁሉ ክፍት ሳላልነበር፣ የቀረው ዓለም ስለነዚህ ሰዎችና ስለሥራቸው የሚያውቀው ነገር የለም፡፡›› ብርሃኑ ድንቄ

የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)

በኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዬታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አባሎች የነበሩ ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራሮችና አባላቶች በመላ ኢትዮጵያ ከሚኖሩ ዜጎችን ያቀፈ ህብረ ብሄር ፓርቲ ሲሆን የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የሲዳማ፣ የሀረሪ፣ የሶማሌ፣ የአፋር ወዘተ ልጆችን አቅፎ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የህዝብ መንግስት እንዲቆቆም ታግሎ በማታገል፣ ውድ ህይወታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በደርግ የጅምላ መቃብር አባሎቻቸው ተገለው በአንድ ጉድጎድ ውስጥ ተቀብረዋል፡፡ ክብር ለወደቁ ሠማዕታት!

አርቆ አሳቢ፣ ቅርብ አዳሪ!!! ትውልድ እና የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ትውልድ ወያኔን በመፋለም የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በዘር ያማያምነው ትውልድ የተደራጀው በርዕዮተ ዓለም ሶሻሊስት ትግል እንጂ በቆንቆና በወንዜ ልጅነታና በዘር ሃረግ አልነበረም፡፡ የመኢሶኑ ዶክተር መረራ ጉዲና የመኢሶን አበራ የማነአብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ10 ዓመታት በላይ በወህኒ ቤት ያሳለፈ ጣሪክ የማይረሳው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ዶክተር ነገደ ጎበዜ የወያኔን ቤተመንግሥት በብዕሩ የናደ በረከት ስምዖንንና መለስ ዜናዊን ያስነጠሰ

ኃይሌ ፊዳ የመኢሶን መሪ (ኦሮሞ)፣ ዶክተር ነገደ ጎበዜ (አማራ)፣ ዶክተር ንግሥት አዳነ(ትግራይ)፣ ዩሃንስ ህሩይ(አማራ)፣ አበራ የማነአብ(ኤርትራ)፣ ዶክተር የራስ ወርቅ አድማሴ (አማራ)፣አንዳርጋቸው አሰግድ (አማራ)፣ ደስታ ታደሰ(ጉራጌ)፣ ዶክተር መረራ ጉዲና(ኦሮሞ)The organ of the All-Ethiopian Socialist Movement, Voice of the Masses, which was distributed clandestinely contributed immensely to strengthen the struggle and to spread consciousness.

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዬታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)

ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ (ትግራይ)፣ ብርሃነመስቀል ረዳ (ትግራይ)፣ ዬሴፍ አዳነ (ትግራይ)፣ ዮሐንስ ብርሃነ (አማራ)፣ጌታቸው ማሩ (አማራ) ፣ ብርሃኑ እጅጉ (አማራ)፣ ፍቅሬ ዘርጋው (ጉራጌ)፣ አብዲሳ አያና ሮባ (ኦሮሞ) ክፍሉ ተፈራ፣ፀሎተ ህፅቅኤል(ትግራይ)፣መላኩ ማርቆስ፣ ተካልኝ ወልደአማኑኤል፣ውብሸት ረታ፣ሙሉጌታ ሱልጣን፣ግርማቸው ለማ፣(EPRP Leaders Dr. Tesfay Debessay-Chaireman of EPRP/’IHAPA’ with some of a CC and Polite Bureau members)የህወሃት የጦር አበጋዞች ከኢዲዩ፣ኢህአፓ፣ ከደርግ፣ጦርነት ገጥሞ ኢትዩጵያን ተቆጣጠሩ፡፡ ህወሃት የጦር አበጋዞች ህዝቡን በዘር በመደራጀት (ትግሬ፣ኦሮሞ፣ አማራ፣ሱማሌ ወዘተ) ብሎ በዘር የተመሠረተ ፌዴራሊዝም በመከፋፈል ለሃያ ሰባት አመታት በአንድ ፓርቲ ገዛ፡፡ በአንድ ጉድጎድ በአንድነት እንደተቀበሩ ተረሳና!!!

ቢኒያም አዳነ(ትግራይ)፣ሳሙኤል አለማየሁ(አማራ)፣ዘሩኡ ክህሽን(ትግራይ)፣ገብሩ መርሻ(ጉራጌ)፣(በህመም የሞቱ)፣መዝገብነሽ አቦዬ፣(በሰው የተገደለች)

(በህይወት ያሉ) ኢያሱ አለማየሁ(አማራ)፣ገነት ግርማ(ኦሮሞ)፣ ክፍሉ ታደሰ (አማራ)፣አዳነች ፍስሃዬ(ትግራይ)፣መላኩ ተገኝ፣ አብዱል መጅድ ሁሴን (ሱማሌ)ወዘተ                     

Many of its central committee and senior members (Dr.Tesfye Debessay, Kiflu Kebede, Yohannes Berhane, Yosefe Adane, Geremachew Lema, Melaku Markos, Mulugeta Sultan, Mulugeta Zena, Berehanu Egegu, Fekere Zeregawe Engineer Osman, mohamude mafuse etc) paid the ultimate sacrifice. Faced with a ruthless dictatorship there is no choice but to wage the bitter and costly struggle.

ፀጋዬ ገብረመድህን(ደብተራውአማራ)፣አበራሽ በርታ(ኦሮሞ)፣ ለማ ኃይሉ(ትግራይ)፣ከበደ ተስፋ
ኮሌኔል አለማየሁ አስፋው(አማራ)፣ገብረእግዚአብሄር ወልደሚካኤል(ትግራይ)የወያኔን ጠባብ ብሄርተኛነት ገና በጠዋቱ የተዋጉ የቁርጥ ቀን ልጆች በታሪክ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡ በወያኔ በተግራይ ውስጥ በጅምላ መቃብር ተገለው የተቀበሩ የኢህአፓ ሠማዕታቶች አስክሬን በክብር የሚያርፍበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡ ገዳዬቻቸው የህወሓትና ብአዴን ሹንባሾች በታሪክ አተላነት የሚጠየቁበት ቀን ቀርቦል፡፡ እነሱም እንደእናት እናትና አባት፣ እህትና ወንድም እንዳላቸው አትዘንጉ እኛ አልረሳናቸውም፣ ለዘላለም አንረሳቸውም! የወያኔን መሰሪነት ያስተማሩን እነሱ ናቸውና፡፡ የዛሬ አርባ አመት ወያኔን በእንጭጩ ለመቅቸት የተፋለሙ ጀግኖቻችን እንዘክራቸዋለን፡፡በኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዬታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባሎች የነበሩ ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራሮችና አባላቶች በመላ ኢትዮጵያ ከሚኖሩ ዜጎችን ያቀፈ ህብረ ብሄር ፓርቲ ሲሆን የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የሲዳማ፣ የሀረሪ፣ የሶማሌ፣ የአፋር ወዘተ ልጆችን አቅፎ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የህዝብ መንግስት እንዲቆቆም ታግሎ በማታገል፣ ውድ ህይወታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በደርግ የጅምላ መቃብር የኢህአፓና መኢሶን አባሎቻቸው ተገለው በአንድ ጉድጎድ ውስጥ ተቀብረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጭቁኞች አብዬታዊ (ኢጭአት)ICHAAT or Revolutionary Organization of Oppressed Ethiopians,

ባሩ ቱምሳ(ኦሮሞ)፣ዘገየ አስፋው(ኦሮሞና አማራ)፣ አሰፋ ጫቦ (ደቡብ)

የኢትዮጵያ ጭቁኞች አብዬታዊ፣ ወዝ ሊግና ሰደድ በዘርሃረግ ላይ ያልተመሠረቱ ህብረ ብሄር ድርጅቶች ሲሆኑ በኢትዮጵያ የዘር ድርጅትን የፈበረኩት ሻብያ፣ ህወሓት፣ ኦነግ ወዘተርፈ ጊዜ ሰጣቸው ቅሎች መሆናቸውን አዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወታቶች ታሪኩን አመሳክረው ማወቅ ጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡