ከሰሞኑ ጠቋሚ ነጥቦችን በማንሣት አብኖች በወያኔ/ብአዴን መመሥረታቸውን ለመመልከት ሞክረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሰዎቹን በዚህ ደረጃ የወያኔ/ብአዴን መጠቀሚያ እንዲሆኑ ምን እንዳበቃቸው እንይ፦
እንደምታውቁት የሚበዙትማ ጭራሽ የብአዴን ካድሬ ሆነው ወገናችንን ሲያርዱና ሲያሳርዱ የኖሩ ናቸው፡፡ እንደ ጋሻው መርሻ ያሉትም “አማራ የሚባል ነገድ ወይም ብሔረሰብ የለም!” የሚለውንና “አማራ የለም!” በሚለው አቋሙም በአማራ ላይ የተፈጸሙት የዘር ማጥፋት አረመኔያዊ ጥቃቶች “በአማሮች ላይ ተፈጸመ!” ተብሎ በኢሰመጉም ሆነ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳይዘገብ እንዳይመዘገብና የአማራ ግፍ በደል እንዳይታወቅለት ከፍተኛ ሸፍጥና ደባ የፈጸመብንን የአማራን ቀንደኛ ጠላት አቦይ መስፍን ወልደማርያምን አምላኪና አብረውም “አማራ የለም!” ባይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከአምላኪነታቸው የተነሣ ለአጠራራቸው እንኳ ቋንቋ አላቸው፡፡ ረቢ በማለት ነው አቦይ መስፍንን የሚጠሩት፡፡ ሐዋርያት ጌታን በሚጠሩበት ቃል ማለት ነው ይሄንን የአማራ ጠላት የሚጠሩት፡፡
ይሄንን ቃል ጋሻው መርሻ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰውየው 86ኛ ዓመት ልደታቸውን ሲያከብሩላቸው ከለጠፈው እዚሁ ካያያዝኩላቹህ ፎቶ ላይ ታገኙታላቹህ፡፡ ሰውየውን ምን ብሎ እንደገለጻቸውም ተመልከቱት፡፡
ከዚህ ቀደም ስለእሳቸው የጻፈው “ዓለም ውስጥ ካሉ ብርቅና ድንቅ ምሁራን አንዱ!” እያለ አይደለም ፕሮፌሰርነት (ሊቀጠበብትነት) ዶክትሬት (ሊቀማእምራንነት) እንኳን የሌላቸውን ሰው እዚያ ላይ ሰቅሎ ውዳሴና የአድናቆት ቃላት ብቻ የታጨቀበት እያረፋቹህ ካልሆነ አንዴ የማትጨርሱት እረጅም ጽሑፍ ነበረው፡፡ እዚህ ላያይዝላቹህ ፈልጌ የፌስቡክ አካውንቱ (የመጽሐፈገጽ መዝገቡ) ውስጥ ብፈልገው አጣሁት አጥፍቶታል፡፡ ጥቂት የማትባሉ ሰዎች ግን ይሄንን ጽሑፉን እንደምታውቁት አልጠራጠርም፡፡ በርካታ የሰውየውን ፎቶ (ምሥለ አካል) ግን ከተለያዩ የማድነቂያ ቃላቶቹ ጋር አሁንም ብትገቡ ታገኛላቹህ፡፡ ይሄ ሰው ነው እንግዲህ ዛሬ እውነት አስመስሎ በስሜት ትናንትና የለም ሲለው የነበረውን አማራ እየጠራ ሲወሸክት የምታዩት፡፡
እናም እንግዲህ እነዚህ ከፊሉ የብአዴን ካድሬ (ወስዋሽ) ከፊሉ ደግሞ “አማራ የሚባል ነገድ ወይም ብሔረሰብ የለም!” የሚሉ አማራን ጨርሶ የማያውቁና ህልውናውን የካዱ፣ ሕመሙ የማያማቸው፣ ሰቆቃው የማይታያቸው፣ ለቅሶው ጩኸቱ የማይሰማቸው ናቸው እንግዲህ ዛሬ “የአማራን የሰቆቃ እንባ አባሽ ነን!” ብለው በስሙ እያወናበዱ የሚገኙት፡፡
እንዲህ ዓይነት ሰዎች ከሆኑ ምን አስበው ምን ፈልገው በወያኔ/ብአዴን ለመደራጀት ፈቀዱ ታዲያ? ተብሎ መጠየቁ አይቀርም፦
አብኖች ማለት ወቅት እያየ ወቅቱ የሚፈልገውን አገለግሎት ይዞ እንደሚቀርብ ብልጥ ነጋዴ ማለት ናቸው፡፡ ሁሉም አጋጣሚውን ተጠቅመው በሚተዋወቁበት ተጠራርተው በመቧደን ተጠቃሚ ለመሆን የተደራጁ ብልጣብልጥ ነጋዴዎች ወይም ጥቅም አሳዳጆች ናቸው፡፡ ለጥቅም ለሆድ ነው ሌላ ነገር አይደለም ማለቴ ነው፡፡ በአንዳቸውም ጭንቅላት የአማራ የግፍ፣ የበደል፣ የሰቆቃ ድምፅ የለም!!! የአማራ ሕዝብ ለነሱ ቢዝነስ ነው፣ ሸቀጥ ነው፡፡ ስሙን እየቸበቸቡ የሚከብሩበት፣ እንደመሰላል ተጠቅመው ለሥልጣን የሚበቁበት አዋጭ ቢዝነስ (ንግድ)፡፡
ከመሃላቸው ከአንድና ሁለት ዓመት በፊት ስለአማራ ሲል ሲጮህ፣ ሲታገል፣ ዋጋ ሲከፍል የነበረ አንድም ሰው እንኳ አታገኙም!!! ከላይ እንዳልኩት ሁሉም ወቅት አይቶ ለመጠቀም አሰፍስፎ የተሰለፈ ብልጣብልጥ ነጋዴ ወይም ጥቅም አሳዳጅ ነው፡፡
ነጋዴ ደግሞ ቢዝነሱን (ንግዱን) ይከታተላል እንጅ የወገንን ግፍና በደል አይከታተልም፡፡ ለዚህም ነው “አለን!” ለማለት ያህል ብቻ ቀለል ቀለል ባለው ጉዳይ ላይ ካልሆነ በስተቀር ከበድ ከበድ ባለው ወይም በከፋው የአማራ ግፍ፣ የአማራ በደልና የአማራ ጥቅም ላይ አብንን የማታዩት የማታገኙት፡፡ ይሄንን አልታዘባቹህም???
ምሳሌ ልጥቀስላቹህ፦ ዐቢይ ወያኔ በማኒፌስቶው ቀርጾ በአማራ ላይ ሲፈጽመው የኖረውን የዘር ማጥፋት አረመኔያዊ ጥቃት በሕዝብ ፊት በአደባባይ ቀርቦ ሸምጥጦ በመካድ “በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት አልተፈጸመም!” ብሎ ሲለፍፍ መግለጫ አውጥተው በተገቢው መንገድ ተቃውሟቸውን አላሰሙም፣ የአማራ እናቶችን ለማምከን ተሲሮ እየተፈጸመ ያለውን ክትባት አልተቃወሙም አላወገዙም ወይም ደግሞ ሕዝቡ ከሥጋት ነጻ ሆኖ መተማመን የሚፈጠርበትን ሥራ አልሠሩም ዓይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ ነው የሆኑት፣ የዐቢይ/ታከለ አሥተዳደር የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ (ነባራዊ ምኅዳር) በመቀየር ወደፊት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን በርካታ መሠረታዊ ሕገወጥ ሥራዎችን ሲሠራ ይሄንን የአማራን ታሪካዊ ጥቅም የሚያሳጣን ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታት አንድም ዓይነት ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም ወዘተረፈ.
አብኖች አማራ ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል የቀሰቀሳቸው፣ ያሥነሣቸው፣ የወለዳቸው ቢሆኑ ኖሮ ዛሬ የሚፈሩት ነገር ሳይኖር በድፍረትና በጽናት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ሲታትሩ ታዩዋቸው ነበረ፡፡
ዛሬ ብቻ ሳይሆን ትናንትናም በአስፈሪው የአፈናና የመታረድ ዘመን ከእኛ ጋር ሆነው ለአማራ ሲጮሁ፣ ለአማራ ሲሟገቱ፣ ለአማራ ሲታገሉ፣ ለአማራ ዋጋ ሲከፍሉ ታዩዋቸው ነበር፡፡
ነጋዴዎች እንጅ ታጋዮች አይደሉምና ብልጣብልጥ ጥቅም አሳዳጆች እንጅ ለወገን ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ምጥዋን አይደሉምና ትናንት ከእኛ ጋራ ቆመው ስለ አማራ አልጮሁም፣ አልተሟገቱም፣ አልታገሉም፣ ዋጋ አልከፈሉም ወገን ጨርሶ አያውቃቸውም!!!
ነጋዴዎች እንጅ ታጋዮች አይደሉምና ብልጣብልጥ እፍረተቢስ ጥቅም አሳዳጆች እንጅ እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ፋኖዎች አይደሉምና ወደፊት አንድ ነገር ቢመጣ ሸጠውህ ይሄዳሉ እንጅ አንዳቸውንም ከጎንህ አታገኛቸውም፡፡ ዳሩ ቅጥረኞች ናቸውና ችግር እንኳ ቢመጣ ችግሩ የሚያጠቃው አንተን እንጅ እነሱን አይነካም ለማስመሰል አንዳንድ ነገር ካልተደረገ በስተቀር፡፡ እናም እነሱ ማለት ለአማራ ሕዝብ የሰንበሌጥ ምርኩዝ ማለት ናቸው፡፡
ለአሁኑ ግን ቀደም ሲል ከዓመታት በፊት ወገኔን ለመቀስቀስ፣ ለማነሣሣት፣ ለማታገል ከጻፍኳቸው ጽሑፎች ላይ ወኔ ቀስቃሽ፣ አነቃቂና አስቆጭ የሆኑ ቃላቶችንና ሐሳቦችን እየለቃቀሙ ሸምድደው በመያዝ በየቀረቡበት መድረክ እንደጸሎት መጽሐፍ በመድገም እልህ፣ ቁጭት፣ መደፈር፣ ብሶት፣ መጠቃት፣ መዋረድ፣ መገፋት የወለዳቸው ፋኖዎች መስለው መታየትን ችለውበታል፡፡
ከበፊት ጀምሮ ጽሑፎቸን የሚከታተሉ ሰዎች ብዙ ነገር ይነግሩኛል “እከሌ የተባለው የአብን አመራር እንደዚህ ከሚለው ጽሑፍህ ውስጥ እንደዚህ ያልከውን ቃል፣ ሐሳብ ወስዶ የራሱ በማስመሰል እንደዚህ ብሎ ተናገረ!” ይሉኛል፡፡ እኔም እንዲሁ ሲያደርጉ አያቸዋለሁ፡፡ እንኳን አዲስ ሐሳብ ሊያመጡ ከእኔ የለቃቀሙትን እንኳ በደንብ አስተካክለው አይናገሩትም፡፡
አብኖች ለአማራ የሚታገሉ ቢሆኑ ኖሮ በጽሑፎቸ ላይ ያነሣኋቸውን ሐሳቦች እየወሰዱ መጠቀማቸው ባላስከፋኝ እንዲያውም ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ይሄ ቀርቶ ቅጥረኞች ሆነው እያለ ሐሳቦቸ ወገኔን ለማታለያነት፣ ለመደለያነት መጠቀሚያ በመዋላቸው እንዴት ያንገበግበኛል መሰላቹህ!!!
ሲጠቃለል ወገኔ ሆይ! ከቅጥረኝነታቸው በተጨማሪ ስምህን ቸብችበው ለመክበር በፈለጉ፣ አንተን መወጣጫ መሰላል አድርገው ሥልጣን መያዝ በፈለጉ ዓይንአውጣ ብልጣብልጥ ጥቅም አሳዳጆችና ነጋዴዎች እየተታለልክ ነውና ቶሎ ንቃ!!!
አብን አሻንጉሊት ጭፍሮቹን የኔን ጽሑፍ ዓይተው እንዳላዩ እንዲያልፉ ስላዘዘ ዛሬ ያለ ስድብ በስተቀር ምንም ነገር ከማያውቁ ገለባ ጭፍሮቹ ስድብ ነጻ እንደምሆን ተስፋ አደርጋለሁ!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የአብን አመራሮች በሙሉ ስለአማራ ሲጮሁ፣ ሲታገሉ፣ ዋጋ ሲከፍሉ የነበሩ አይደሉም!!! አንዳቸውም እንኳ በአማራ ትግል የሚታወቁ አይደሉም፡፡ አንዳቸውም!!!
amsalugkidan@gmail.com
