አማራ ከኢትዮጵያ ሊሸሽ አይችልም! ሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቢሸሹ እንኳን አማራ የመጨረሻው ይሆናል!” ይሄ ቃል የአብን ሊቀመንበር የተናገረው ቃል ነው፡፡

ብዙዎቻቹህ ይሄ አነጋገር ካለመብሰል ማለትም የፖለቲካ ብስለት ከማጣት የተነገረ አነጋገር ይመስላቹህ ይሆናል፡፡ ግን አይደለም ሰውየው እንደቅጥረኝነቱ የአማራ ሕዝብ የኢትዮጵያን መገነጣጠል በጸጋ እንዲቀበል ወይም እንዲፈቅድ ለማግባባት አስቦ የተናገረው ነው፡፡

እኛ አባቶቻችን የምናውቃቸው እምብኝ ለሀገሬ እምብኝ ለድንበሬ!” ሲሉ ነው፡፡ አማራነት ማለትም ይሄው ነው!!!

አማራ የኢትዮጵያን ህልውና እና የግዛት አንድነት ለድርድር አቅርቦ አያውቅም ወደፊትም አያቀርብም፡፡ ለድርድር አያቀርብም ማለት ሌሎቹ እንገነጠላለን!” ቢሉ እንኳ አይፈቅድም ማለት ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

አብን ግን ዓላማውና የተቀጠረበት ተግባሩ ኢትዮጵያን ማፈራረስ ነውና የኢትዮጵያን ህልውናና የግዛት አንድነትን በአጥፊዎቿ ፈቃድና ፍላጎት እንዲወሰን ሰጥቷል!!!

ጭራሽም በመገንጠሉ መጨረሻኛ እንሆናለን አለ፡፡ አብኖች በዚህ አባባል ማስተላለፍ የፈለጉት መልእክት እገነጠላለሁ የሚል ካለ ከወዲሁ የአብንን ፈቃድና ይሁንታ አግኝቷል!” ነው ማለት የፈለጉት፡፡ ይታያቹህ የአማራን ሕዝብ ስም ይዞ ነው እንግዲህ መገንጠልን ፈቃጅ የሆነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት አልተመቸኝም!” የሚል ፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ቡድን ካለ ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል እንጅ አንዲት ጋት መሬት ታክል እንኳ ብትሆን አማራ ርስቱን፣ ሀገሩን፣ ምድሩን ቆርሶ ለወራሪና ለስደተኛ አይሰጥም!!! ሰጥቶም አያውቅም!!!

እርግጥ ነው ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ተገንጥላለች፡፡ ይሁን እንጅ ጠላት ሀገራትና ባንዶች ተባብረው ቢረባረቡብን ቢያይሉብን ለጊዜው አቃቱንና ሀገራችንን ርስታችንን ሊገነጥሉብን ቻሉ እንጅ ወደንና ፈቅደን አልሰጠንም!!! የጊዜ ጉዳይ ነው እንመልሳታለን!!!

ለነገሩ አለአግባብ የተሰጠብንን ወደባችንን ከመለስን የተቀረው ዕዳው ገብስ ነው፡፡ ተገንጥለው አይተውታልና ከአሳር መከራ ውጭ ያገኙት ነገር የለምና ከዚህ በኋላ አንድ የመሆን ፍላጎቱ የሚያይለው በእነሱ በኩል ነው የሚሆነው ማለቴ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ለአንተ ያሰቡ መስለው ርስትህን ሀገርህን ለማንም አሳልፈህ እንድትሰጥ የሚያግባቡህንና የሚሠሩትን ሁሉ ቅጥረኞች ናቸውና ተጠንቀቅ!!!

ምን ያህሎቻቹህ ልብ እንዳላቹህት አላውቅም እንጅ በፊት ቤተ አማራ ነንይሉ የነበሩት የዛሬዎቹ አብን ነን!” ባዮች ባሕረ ምድርን (ኤርትራን) የኢትዮጵያ እንደሆነች አድርጋቹህ ስታወሩ ቢያገኟቹህ ወይም ደግሞ ሙሉ የኢትዮጵያን ካርታ (ትልመ ምድር) ስትጠቀሙ ቢያገኟቹህ ግራ እስኪገባቹህ ድረስ የሚያደርሱባቹህ ትችት አያድርስ ነው፡፡

አሁን ላይ እንኳን ነገሩ ግልጥ ሆኗል፡፡ ቤተ አማራ ነን!” ይሉ ከነበሩት የሚበዙት በአንድ ጎናቸው ወይም ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደው ያደጉ ኤርትራውያን ስለሆኑና በአማራ ስም ሆነው የኤርትራን ጥቅም ለማስከበር ስለሚፈልጉ ነበር እንደዚያ የሚያደርጉት፡፡ ቂሉ የኛ ወገን ግን ሳይገባው ዝም ብሎ ያጫፍር ነበር፡፡

የወያኔና የሸአቢያ ትልቁ ብቃታቸው ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ??? ሥነልቡናችንን በልተውታል፡፡ አማራን መቸ ምን ብለው ማጃጃል፣ መቸ ምን አርገው ማታለል፣ መቸ ምን ብለው መገልገል እንደሚችሉ ያውቁታል፡፡ ስለዚህም አማራ የቱንም ያህል ቢያመር አያሳስባቸውም፡፡ በአንዲት ቃል ቁጣውን አብርደው በግ እንደሚያደርጉት ያውቁታል፡፡ እንዲያገለግላቸው ሲፈልጉም እንደዚሁ ምን ብለው እንዲያገለግላቸው እንደሚያደርጉት ያውቁታል፡፡

ወገኔ ምንም ነገር ለማድረግም ቢሆን በዚህች ምድር ላይ ትልቁ ጨዋታ ወይም ብቃት የአንድን አካል ሥነልቡናን ማወቅ ነው፡፡ ሥነልቡናውን ካወቃቹህ ሶፍትዌሩን (ረቂቅ ዘአካሉን) ተቆጣጠራቹህ ማለት ነው፡፡ ሶፍትዌሩን (ረቂቅ ዘአካሉን) ተቆጣጠራቹህት ማለት ደግሞ ሃርድዌሩን (ግዘፈ አካሉን) እንደፈለጋቹህ ማድረግ ትችላላቹህ ማለት ነው This is the key secret to control everything you want.

ወገኔ ሆይ! እባክህን ንቃ??? የዋህ አትሁን??? ማንም አማራ አማራ ስላለ ብቻ አትመን??? ሸአቢያም ሆነ ወያኔ ልትገምተው ከምትችለው በላይ ቀና እንዳትልና ከወደክበት እንዳትነሣ ለሚቀጥሉት በርካታ ዐሥርት ዓመታት የሚሆናቸውን የሸፍጥ የሴራ መረባቸውን ተብትበው እላይህ ላይ ጥለውብሃልና ንቃ!!! ይሄንን የሸፍጥ የሴራ መረባቸውን በጣጥሰህ ውጣ!!! ምንጊዜም ቢሆን ዓይንህን ከእነሱ አታንሣ!!! በምንም ተአምር ቢሆን ፈጽሞ እነሱን አትመን!!!

የግድ እነሱ በቀጥታ ላይሆን ይችላል የሚመጡት፡፡ ከእነሱ የተደቀሉትንና የገዛ ሆዳም ወንድምህን ተጠንቀቅ!!! ብአዴንን አስብ!!! ብአዴን ለማን ሲሠራ፣ ማንን ሲያገለግል ነው የኖረው??? ብአዴን ውስጥ ያሉ አማሮች ለአንድ ቀን እንኳ ለወያኔና ሸአቢያ ብየ የገዛ ወገኔንማ ለምን ብየ አርዳለሁ አሳርዳለሁ?” ብለው ያውቃሉ ወይ??? ፈጽሞ ብለው አያውቁም!!!

ሸአቢያና ወያኔ ወደፊትም የሚመጡብህና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ጥረት የሚያደርጉብህ በዚህ መልኩ እየመጡ ነው፡፡ እመነኝ አብን ቀጣዩ ብአዴን ነው!!! እመንም አትመንም የራስህ ጉዳይ ነው!!! እኔ ከራሴ አውርጃለሁ!!! ዛሬ ባታምን ነገ የግድህን ታምናለህ የጊዜ ጉዳይ ነው!!! ምንም ነገር ማድረግ በማትችልበት ጊዜ ነቅተህ ከምታር አሁኑኑ ንቃና አብንን ትተህ ፈጥነህ ተደራጅ!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com