ወይ ጉድ! እኔ በተናገርኩ በአምስት ዓመቱ ነው እንዴ የተናገርኩት ነገር ሰውን የሚገባው???
በዚያም በዚህም ያም ይሄም ትምክህት ትምክህት ይላል!
ይህ ከታች ሊንኩን (ይዙን) ያስቀመጥኩላቹህን የአማራ ሕዝብ በጠላቱ በወያኔ ላይ እንዲነሣ በኃይለኛው ለመቅቀስ በማሰብ የጻፍኩትንና በድረ ገጾች ላይ ያስነበብኩትን ረዘም ያለ ጽሑፍ ከጻፍኩት አምስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ላይ ትምክህት ለአማራ ሕዝብ የሦስት ሽህና ከዛም በላይ ዓመት ድካሙ የፈጠረለት የሥነ ልቡና ሀብቱ፣ ውርስና ቅርሱ፣ የልብ ኩራቱ፣ ወደፊትም ከወደቀበት መነሻ ጉልበቱ፣ የትንሣኤ ስንቁ፣ ሁሉንም ተነጥቆ አንድ የቀረችለት ንብረቱ መሆኑንና ወያኔ አማራን “ትምክህተኛ!”
እያለ ለማሸማቀቅ የሚሞክሩበት ሸፍጠኛ ምክንያት ምን እንደሆነ፣ ትምክህት ማለት ምን ማለት
እንደሆነ ወዘተረፈ. ገልጨ ነበረ፡፡
ጽሑፉን አሁንም ብታነቡት ትቀሰቀሱበታላቹህና፣ ትሸነጡበታላቹህና ሊንኩን ተጭናቹህ ክፈቱና አንብቡት፡፡ ይህ ስለ ትምክህት የጻፍኩት ግጥም ከጽሑፉ የተወሰደ ነው፦
እኔስ እኮራለሁ ፤ ቅርሴ ነው ትምክሕቴ በደም የወረስኩት ፤ ከእናትና አባቴ የትንሣኤየ አቅም ፤ መነሻ ጉልበቴ
ትምክሕቴ ነው ውርስ ፤ ቅርስ የታሪክ ሀብቴ፡፡
ትልቅ እንደነበርን ፤ ትልቅ እንሆናለን ያለው እኮ ካሳ ፤ ተናግሮ ኃይለ ቃልን ለማገናኘት ነው ፤ ትናንትና ነገን፡፡
የሀገርን ታሪክ ፤ ታሪኬ ካላሉት ከወዴት ይገኛል ፤ ያ ቅርስ ትምክሕት?
አንተ ባንዳ ሆነህ ፤ ከነ ዘርማንዘርህ ስታደማ የኖርክ ፤ ለሀገር ጠላት አድረህ ታዲያ ትምክህቱ ፤ ከወዴት ይምጣልህ?
ተከናነብ እንጅ ፤ ውርደት እንደ አባትህ፡፡
ከጥንት ከመሠረት ፤ ሳይደከምበት ከእናትና ከአባት ፤ ሳይወራረሱት ግራ ቀኝ ቢያፈጡ ፤ ከየት ይገኛል ትምክህት?