እነዚያ በረከትን በገባበት ሁሉ እያሳደዱ ወያኔ “የአማራ ክልል!” በሚለው ድርሽ እንዳይል ያደረጉትንና ደኅና ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ሳተና ሳተና የአማራ ወጣቶችን ብን ያድርገውና አብን የሚባል ቅጥረኛ ድርጅት ያዛቸውና አሁን ማን ይንቀሳቀስ???
ወጣቶቻችንን አብን በሚባል ገመዳቸው እጅ እግሩን አሰሩብን!!! አብንን የመሠረቱበት አንዱ ዓላማስ ይሄ አይደል??? ወጣቱን ለማሰር፡፡ እንዳጀማመሩ ይሄኔ የአማራ ወጣት ስንት እመርታ ባስመዘገበ ነበር!!!
ጭራሽ በአሁኑ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ጥቃት ደርሶብን አርፎ ሊቀመጥ??? ይሄኔ በየቦታው ቀውጢ ፈጥሮ ብአዴን/ወያኔን ሱሪው ላይ ባሸኑት ነበር!!! እኛም ታፍረን፣ ተፈርተን፣ ተከብረን በኖርን ነበር!!!
አሁንም እላለው አብን በሚባል የወያኔ/ብአዴን ገመድ የታሰርክ የአማራ ወጣት ሆይ! ይሄንን ገመድ በጣጥሰህ ጣልና በራስህ ቁም በራስህ ተደራጅ!!! ካልሆነ እጅ እግርህን ታስረህ ተኮድኩደህ የማንም መጫወቻ ሆነህ መቅረትህ ነው!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
