14 January 2019
የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 12 ኃላፊዎችና ሁለት ግለሰቦች ከመርከቦች ግዥ ጋር በተገናኘ 544.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመሠረተባቸው፡፡
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ምክትል ዳይሬክተሮች የነበሩት ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤል፣ ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤል፣ ብርጋዴር ጀኔራል ጠና ቁርንዲን ጨምሮ 12 ኃላፊዎችና ሁለት ግለሰቦች፣ ዓባይና አብዮት ከሚባሉት መርከቦች ግዥ ጋር ነው፡፡
ተጠራጣሪዎቹ መርከቦቹን በ3.2 ሚሊዮን ዶላር ገዝተው በ7.3 ሚሊዮን ዶላር ካሳደሱ በኋላ ወደ ሥራ ያስገቡዋቸው ቢሆንም፣ መርከቦቹ ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ እንዳደረሱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ መርከቦቹ አዋጭ ባለመሆናቸው በኪሳራ 607,432 ዶላር በመሸጣቸው፣ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ በአጠቃላይ 544,772,623 ብር ጉዳት መድረሱን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስታውቋል፡፡
