January 14, 2019

ይድረስ ለቲም ዓብይ :- በውሸት ታሪክ ላይ የተገነባ መንግሥት በልሳነ ግፉአን ጩኸት ይፈርሳል !!!

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed waves to supporters as he attends a rally in Addis Ababa, Ethiopia June 23, 2018. REUTERS/Stringer
“ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ : የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” ሲሉ አበው ያቆዩልንን ዘመን ተሻጋሪ ብሂል ለዚህ መጣጥፍ መንደርደሪያ ተውሰነዋል:: በእርግጥም ጀግናዎች ተዋርደው አገር እና ሕዝብ የሚሸጡ ባንዳዎች በሚገኑባት ምድር እንዲህ አይነቱ ተምሳሌታዊ ፈሊጥ የሕዝብን መሪር ብሶትን ለመግለጽ ትልቅ አቅም አለው :: የሩቁን እንኳን ትተን ” የሕዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢሕአዲግ ሰራዊት
: ተራራ አንቀጥቃጭ ትውልድ ” እየተባለ በተለይም ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮጵያ ምድር ሲፎከርለት እና ሲዘመርለት የኖረውን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ – ትህነግ ስላቃዊ የታሪክ ገድል ለመቃኘት ብንሞክር እንኳ በመግቢያችን ላይ የጠቀስነውን አባባል የሚጋራ ብዙ ተዛምዶ አለውና ታሪክ በየዘመናቱ እራሱን መድገሙ በእጅጉ እንድንደመም ያደርገናል:: በአሉ እና በመሰለኝ ታሪክ ላይ ተመስርተን ሳይሆን እራሳቸው ነባር የትህነግ መስራች ታጋዮች በአንደበታቸውም በመጣጥፎቻቸውም እንደነገሩን የወያኔ ሃርነት አመራሮች
ከ 60 ሺህ በላይ የትግራይ ወጣቶችን አማራ ጠል መርዘኛ የፈጠራ ትርክት እየሰበኩ ከጎናቸው አሰልፈው
የኤርትራ አማጽያን ጀበሃ እና ሻቢያ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ወራሪነት ፈርጀው አገር ለመገንጠል ያወጁትን የጦርነት ነጋሪት ኤርትራ ሳህል በረሃ ድረስ ወርደው በመቀላቀል የንጹሃንን ሕይወት አስገብረው ” ነጻነት ወይስ ባርነት ? ” በሚል የሸፍጥ ሴራ ኤርትራ እንድትገነጠል ትልቅ እገዛ እና የታሪክ ክህደት በኢትዮጵያ አገራቸው ላይ ፈጽመዋል:: የሚገርመው ነገር ትሕነግ ኤርትራን በማስገንጠል ብቻ ሳያበቃ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሃላፊ የነበሩት አሜሪካዊው ሸምጋይ አምባሳደር ኸርማን ኮኽን ለንደን ላይ የደርግ መንግሥት ተወካዮችን ከአማጽያኑ መሪዎች መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ከዛሬ 28 ዓመታት በፊት ለንደን ላይ ባደራደሩበት ወቅት እነ መለስ እንደ አሰብ ያሉ በወሎ እና አፋር ልዩ የአስተዳደር ገዞች ስር ለዘመናት ይተዳደሩ የነበሩ የባህር በሮችዋን ጭምር እንድታጣ ከፍተኛ ግፊት ማድረጋቸውን አምባሳደሩም ሆኑ እንደ እነ ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ ገብረመድህን አራያ እና አብርሃም ያየህን የመሳሰሉ ቀደምት የሕወሃት ታጋዮች ከረፈደም ቢሆን ማጋለጣቸውን ስናስብ ትሕነግ በአገርም ሆነ በሕዝብ ላይ የፈጸመውን የለየለት የታሪክ ክህደት ይበልጥ እንድንገነዘብ ያደርገናል :: ኢትዮጵያ ታሪካዊ ወደቧን አሰብን በማጣቷ እስከዛሬ ለኬንያ ሞምባሳ ለሶማሌ ላንድ በርበራ ለሱዳን እና ለጅቡቲ አሁን ደግሞ ለኤርትራ የአሰብ እና የምጽዋ ወደቦች በእያንዳንዱ ቀን በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ለኪራይ አገልግሎት እየገፈገፈች ትገኛለች:: ከዚህ ሌላ የሕወሃቱ የቀድሞ መሪ መለስ ዜናዊ ከሟቹ የግብጹ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ጋር እ.ኤ.አ በ1993 ዓ.ም የአባይን ወንዝ በተመከተ የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊ መብት እና ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ምስጢራዊ ስምምነት ማድረጉ እና በ 1980 ዎቹ አጋማሽ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበረው የትግራዩ አባይ ጸሃዬም ከ 23 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የሆነ ለም የኢትዮጵያን መሬት ከመተማ ወረዳ ደለሎ አካባቢ ቆርሶ በምስጢር እና በግዳጅ ለሱዳን አሳልፎ የሰጠበትን የክህደት ታሪክ ስንመረምር ይህ ድርጅት በአገሪቱም ሆነ በሕዝቧ ላይ ያለውን ውስጣዊ ጥላቻ እና በቀል በግልጽ አመላካች ሆኖ እናገኘዋለን:: እንግዲህ እንደ መለስ ዜናዊ እና አቦይ ስብሃትን በመሳሰሉ ኤርትራውያን መሰሪ ፕሮፓጋንዳ የንጹሃንን የትግራይ ወጣቶች ህይወት በመገበር አገርን ለመሸጥ እና ለማስገንጠል ተደራጅቶ በከዱ የቀድሞ የደርግ የጦር ወታደሮች እና መኮንኖች በሻእቢያ በኦነግ እና በወታደራዊው አገዛዝ የአፈና ሥርዓት በተማረረው የአማራ ፋኖ ሕዝብ ታጅበው ምኒልክ ቤተመንግስት ሰተት ብለው የገቡት ትህነጎች የማክሲሚሊያንን ከፋፍለህ ግዛ መር በማቀንቀን ማፍያ መር የሆነ አሃዳዊ የስልጣን እና የኢኮኖሚ መደላድላቸውን በመላ አገሪቱ ከዳር እስከዳር ከዘረጉ በኋላ ከኛ ወዲያ ፉጨት አፍን ለማሞጥሞጥ
ተራራን ያንቀጠቀጥን የወርቅ ዘሮች ነን ሥልጣን ከእጃችን ከወጣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ይፈርሳል
እያሉ ታሪክን ክደው እና ሕዝባዊ ድሉን ሸምጥጠው ደርግን ለብቻቸው የጣሉ እስኪመስል ድረስ ከሁለት አሥርተ ዓመታት በላይ በባዶ ጉራ ሲበጠረቁብን ኖረዋል:: እንደነ ዶክተር ዓብይ ያሉ ለውጥ አራማጅ ነን የሚሉ መሪዎች እና አንዳንድ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ኢክትቪስት ነን ባዮችን ጨምሮም ” እውነትም የወርቅ ዘር በትግል የተፈተነ የአገሪቱ ዋና ሞተር ሕዝብ ነው ” በሚል አገር የማስገንጠልን የባሕር በር የማሳጣትን እና ድንበር ቆርሶ የመሸጥን የክህደት ታሪክ እያንቆለጳጰሱ ባንዳን አግነው ለአገር ዳር ድንበር መከበር እና ለሉዓላዊነት የተሰዉ ሰማዕታትን በአደባባይ ሲያኮስሱ ማስተዋል ከትህነግ የክህደት ተግባር በላይ በእጅጉ ያማል::
በመሰረቱ እነ ዓብይም ሆኑ አንዳንድ ተገለባባጭ የፖለቲካ ቁማርተኞች እና ነጋዴዎች ፊውዳላዊውን የዘውግ ሥርዓት የከበርቴውን የመሬት አስተዳደር ስሪት ቀይሮ ” መሬትን ለአራሹ ገበሬ ያደረገ እና የተማረ ያልተማረን ያስተምር ” በሚለው መርሁም መኃይምነትን እና ድንቁርናን ከኢትዮጵያ የማጠፋት በጎ ራዕይን ሰንቆ ወደ ስልጣን የመጣውን የደርግ ሥርዓት ከኤርትራ ተገንጣዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሱዳን ግብጽ ሱማሊያ እና አረቦች ጋር ጭምር በማበር ሲወጋ የነበረው ትሕነግ ወታደራዊ ሥርዓቱን ሳይወድ በግድ ገፍቶ ይበልጥ ወደ አምባገነንነት እንደቀየረው ለአፍታ መዘንጋት የለባቸውም:: እንዲህ ባለው የክህደት ታሪክ ብቻ ሳይሆን አገሪቱን በግፍ የደም አበላ ሲያጨቀይ በዝርፊያ በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በጭቆና ኢትዮጵያን የምድር ሲዖል ሲያደርግ የኖረን ድርጅት ነው እንግዲህ ላለፉት 27 ዓመታት ” የአገሪቱ ዋና ሞተር ተራራን አንቀጥቃጭ ” በሚል ውዳሴ ሕዝቡ ሳይወድ በግድ በግንቦት 20 እና በልዩ ልዩ ሕዝባዊ መድረኮች
እንዲዘክረው መደረጉ በመግቢያችን ላይ የጠቀስነውን “አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ : የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የሚልለውን ብሂል ዛሬም እንድናስታውስ ግድ የሚለን:: እርግጥ ነው ይህ ዓይነቱን የውሸት ትርክት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲጠቀሙበት የኖሩት የሕወሃት አመራሮች እና አጋፋሪዎቻቸውም ኤርትራን ለማ
ስገንጠል ሲዋጉ የተሰዉትን እና እራሱ ወያኔ በፈጠረው ተንኮል በትግራይ ሃውዜን መንደር የልጆቻቸውን ሕይወት በደርግ ጦር የተነጠቁ እናቶችን ሕዝባዊ አመጽ እና ቁጣ በተቀሰቀሰባቸው ቁጥር የሟች ልጆቻቸውን ፎቶግራፍ እየያዙ አደባባይ ሰልፍ እንዲወጡ በማድረግ ልክ ለአገር ሕልውና የተሰዉ ሰማዕታት ይመስል አያሌ ድራማዎችን ሲተውኑልን ኖረዋል:: እውነታውን ግን ሕዝባችን በውል ጠንቅቆ ያውቀዋልና ከትዝብት ውጭ ሌላ ምላሽ ሳይሰጥ ኖሯል :: ይሁን እንጂ ዛሬ ዝምታችንን ሰብረን ለዶክተር አብይ አስተዳደርም ሆነ በተቃውሞ ጎራ ለተሰለፉ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች ሕወሃት-ትህነግ ለ 17 ዓመታት ደርግን የታገለው የሻቢያ ተላላኪ በመሆን ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት የተያዘች አገር ነች ብሎ በማመኑ እና ለዛም የሕይወት ዋጋ በመክፈሉ የአስብን ወደብ ጨምሮ ዳር ድንበርን ቆርሶ በመስጠት ታሪካዊ ክህደት የፈጸመ እና አያሌ ደባዎችን የፈጸመ በመሆኑ ከእንግዲህ በኋላ በግንቦት 20 ስም ዓመታዊ የድል በዓል በዛች የነጻነት አገር
ፈጽሞ ሊከበር አይገባም ስንል ጠንካራ አቋማችንን ማስተላለፍ ግድ ብሎናል::
የብሄር ብሄረሰቦች መብት እንዲከበር ታግያለሁ እና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትም መስርቻለሁ ሲል ትህነግ ላለፉት 28 ዓመታት የአገሪቱ ብሄረሰቦችን በዘር እና ሃይማኖት ግጭት የሚያባሉ የቁጭ በሉ ትርክቶች እየፈጠረ ዳር እስከዳር ሌብነቱን አጧጥፎት የስልጣን ኮርቻ ላይ ያለስጋት ተፈናጦ ቆይቷል:: ሕወሃት እንከን አልባ ህገመንግሥት የሚለውም ቢሆን በየትኛውም ዓለም የሌለ እስከመገንጠል ነጻነትን የሚፈቅድ አንቀጽ የተካተተበትን እና ከኦነግ ጋር ኤርትራ ሳህል በረሃ አገሪቱን በሚያመቻቸው መንገድ ሸንሽነው ለመቀራመት ያዘጋጁት ሕዝብ በነጻነት መክሮ እና ዘክሮ ያላጸደቀው የግል ስምምነታቸው ሰነድ ነው :: እንደአጋጣሚ ሆኖ የአማራው ሕዝብ የሁለቱም ብሄሮች ተጎራባች በመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ላይ እንደማይደራደር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አማራ ዛሬም ድረስ ያለ ሃጢአቱ ህቡይ እና እኩይ ዓላማቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ የሁለቱም ድርጅቶች መሰሪ ኢላማ ተጠቂ ሆኖ ቆይቷል:: ትህነግ የትጥቅ ትግሉ አብቅቶ
አገሪቱን በተቆጣጠረ ማግሥት ከአማራው ግዛት ከወሎ እና ከጎንደር በርካታ ለም መሬቶችን እንደ ወልቃይት ጸገዴ ሁመራ ጸለምት አላማጣ ራያ እና ሌሎችንም ወረዳዎች አስገድዶ በመውሰድ ክልሉን ከ 65 % በላይ ያስፋፋ ሲሆን ከጎጃምም እንደ መተከል ፓዌ ያሉትን ጥንታዊ መሬቶች ወደ ሌላ ክልል በማካለል አማራው ከሌላ ብሄር ጋር ቁርሾ ለመፍጠር የሚረዳውን የታሪክ ሸፍጥ ፈጽሟል:: በማኒፌስቶው መሰረት አሁንም ተጨማሪ መሬቶችን ከአማራ ከአፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለመቀራመት አካባቢውን በግጭት እና የእርስ በእርስ እልቂት እያተራመሰው ይገኛል:: ኦነግም ቢሆን ለውለታው በወሎ ልዩ የኦሮምያ ዞን እና በሰሜን ሸዋም የተወሰኑ የአማራ ነባር ወረዳዎችን በጊዜያዊነት ወደ እራሱ እንዲያካልል ሕገ መንግሥት ተብዬው ፈቅዶለታል:: አማራውን አሳንሶ ለእራስ ጥቅም ሲባል በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ክልል ተዋቅረው የማያውቁ ብሄሮችን በክልል ፈጥሮ እና የደቡብ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ አያሌ ሕዝቦች የሚኖሩበትንም አካባቢ ከ 66 በላይ ብሄሮችን ሕዝብ ሳይመክር እና ሳይፈቅድ በአንድ ቋት ሰብስቦ ክልል በመፍጠር የብሄር ጭቆናን አጥፍቼ እኩልነትን እና ነጻነትን አምጥቻለሁ የሚለው የትህነግ የእለት ተዕለት ስላቃዊ መዝሙርም እንደ ማክሲሚሊያን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በማር የተለወሰ መርዝ መሆኑን ሁሉም ጠንቅቆ ከተረዳው ውሎ አድሯል:: ከሁሉ በፊት ትህነግም ሆነ እንደ ኦነግ ያሉ አክራሪ ብሄርተኛ ድርጅቶች ማወቅ ያለባቸው አማራ ጠል የሆነ ፖሊሲን ሰንቀው የብሄር ጭቆናን ልንፋለም በረሃ ገባን ብለው ህዝብ ሲፎግሩ የደርግ ሥርዓት ዋና አመሰራረቱ በራሱ በአብዛኛው በኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ተቀንቅኖ እንደነበር ታሪክን በውል
አለማገናዘባቸው ነው :: በደምሳሳው በወያኔ እና ኦነግ የሴራ ፖለቲካ ትርክት በእርግጥ በደርግ ሥርዓት ነፍጥ ለመምዘዝ ጫካ ገብቶ ለመሸፈት ያበቃቸው የብሄር ጭቆና ከነበረ ጨቋኞቹ የደርግ ግንባር ቀደም መስራች እና አቀንቃኞች የትግራይ እና የኦሮሞ የጦር መኮንኖች ነበሩ እንላለን :: እንዴት ይሄ ይሆናል ለምትሉ ደግሞ መልሳችን እንዲህ የሚል ነው ::
አምባገነኑን እና በተለይም በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ማለትም ኢሕአፓ ስም የበርካታ አማሮችን ሕይወት የቀጠፈውን አምባገነኑን ወታደራዊ መንግሥት አነሳስ ስንመረምር የመጀመሪያው የደርግ ወታደራዊ አስተዳደር መስራቾች እና ዋና መሪዎች በኋላም የርዕዮተ ዓለም ልዩነትን ጨምሮ በንጉስ ኃይለስላሴ የሞት ፍርድ ውሳኔ እና በኤርትራ ነጻነት ጉዳይ የተለየ አስተሳሰብ በማቀንቀናቸው የተገደሉት ኤርትራዊው ሌተናል ጄኔራል አማን ሚካኤል አንዶም እና የኦሮሞ ብሄር ተወላጁ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሆነው እናገኛቸዋለን :: ይሁን እንጂ የስልጣን እና የመሬት ወረራ ልክፍት የተጠናወታቸው ኦነግ እና ሕወሃት የደርግ ሥርዓትን ሳይቀር የአማራ ገዢ መደብ እንደነበር በተደጋጋሚ በመስበክ ሕዝብን ሲያታልሉ ኖረዋል :: በመሰረቱ ደርግ የተፈጠረው በአብዛኛው በኦሮሞ እና በትግራይ ወታደራዊ መኮንኖች የበላይ አመራር መሆኑን ዓለም ጠንቅቆ ያውቀዋል :: የመጀመሪያው የደርግ መስራች እና ሊቀመንበር ከሚባሉት ውስጥ የኦሮሞው ተወላጅ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ተጠቃሽ ናቸው :: እሳቸው በእርስ በእርስ ሹክቻ ከተገደሉ በኋላ ስልጣኑን የተረከበው ከኦሮሞ እና ደቡብ ኮንሶ ቤተሰቦች መወለዱ የሚነገረው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አያና እንደነበረ እሙን ነው:: መንግሥቱ ሃገር ጥሎ ወደ ዚምባብዌ ሲኮበልል የሃረር ኦሮሞ የሆኑት እና የኢትዮጵያ መንግሥት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሌፍተናንት ጄነራል ተስፋዬ የደርግንም የፕሬዝዳንትነቱንም ስልጣን ደርበው ያዙ :: በደርግ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቅማንት ተወላጅ ናቸው :: በጣም ጨካኝ እና ለብዙዎች ሞት ተጠያቂ የነበሩት የደርግ የደህንነት ሚኒስትሩ ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደስላሴ ወላይታ ነበሩ :: የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ሻለቃ ተስፋዬ ዲንቃ ደግሞ የአምቦ ኦሮሞ ናቸው :: በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ የትግራይ ተወላጅ ናቸው :: ኤርትራዊው ሌተናል ጄኔራል አማን ሚካኤል አንዶምም በአቋም ልዩነት አፍታም ሳይቆዩ ቢገደሉም የደርግ መስራች እና ቁንጮ አመራር እንደነበሩ ታሪካቸው ይዘክራል:: ከዚህ ሌላ ወያኔ ትግራይ ላይ ባቀናበረው አሳዛኙ የሃውዜን ድራማ እና በብዙ አውደ ውጊያዎች ጭካኔው የሚወሳው መቶ አለቃ ለገሰ አስፋው, ንጉስ ኃይለስላሴ ከስልጣን መውረዳቸውን ነግሮ በቮልክስ መኪና ጭኖ የወሰዳቸው ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ, ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ, ኮሎኔል ተካ ቱሉ, ጄኔራል ረጋሳ ጅማ ከኢሊባቡር , ኮማንደር ለማ ጉተማ, ጄኔራል ባጫ ደበሌ , ዶክተር ምትኩ ኡርጌ, ካፒቴን መንግስቱ ገመቹ, ሜጀር ጄኔራል መርድ ንጉሴ የሸዋ ኦሮሞ , ሜጀር ጄኔራል አስራት ብሩ, ሜጀር ጄኔራል በድሉ ዱኪ ሸዋ ኦሮሞ , ሜጀር ጄኔራል አበራ አበበ እነዚህ እና ሌሎችም በርካታ ኦሮሞዎች ደርግን በአመራርነት አገልግለዋል :: እንግዲህ የአማራ ገዥ መደብ በሚባለው የደርግ ሥርዓት አማራ ከፍተኛው ዋና ዋና የሥልጣን እርከን ላይ እንኳ እንዳልነበረ ከዝርዝሩ መረዳት ይቻላል :: ዛሬ አንዳንድ በኦነግ እና ሕወሃት በዘረኝነት የብሄር ቋት የተደራጁ የፈጠራ ታሪክ ሰለባዎች ዘመዶቻችን በኦነግ ስም በደርግ አማራ ገዥ መደብ ተገለውብን ነበር በሚል ዓይነት የበሬ ወለደ ተረት እሳቤ የኦነግን ባንዲራ የነጻነት አርማቸው አድርገው ሲያውለበልቡ ስናይ በእጅጉ ታሪክ ባለማወቃቸው ልናዝንላቸው ግድ ይለናል :: በአንጻሩ ደግሞ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ እንደነ ዶክተር ዓብይ እና አንበሳው ኦቦ ለማ መገርሳን የመሳሰሉ እውነተኛ የኢትዮጵያ ኦሮሞ የቁርጥ ቀን ልጆችን የዘመኑ አገር እና ትውልድን የማዳን ገድል ስንመለከት ለእማማ ኢትዮጵያ አኩሪ ተጋድሎ ፈጽመው ስማቸው ከመቃብር በላይ የዋለ ዘመን ተሻግሮም ዛሬ ድረስ ትውልድ በኩራት የሚዘክራቸው የአገሪቱ የቁርጥ ቀን አርበኞች ምትክ በመሆናቸው ደስታችን እጥፍ ድርብ ይሆናል::
የዘመኑን ለውጥ አራማጆች በአንድ በኩል እንዲህ ስናወድስ በሌላ በኩል ደግሞ የምንወቅሳቸውም አያሌ ምክንያቶች አሉን :: ለምሳሌ እነ ዶክተር ዓብይ የጀመሩት የተሃድሶ ጉዞ እና የመንግሥታቸው ዋልታ እና ማገር
የሚጸናው በትግራይ ይሁንታ ብቻ ይመስል በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በሌብነት የሚጠረጠሩ አሁንም አገሪቱን በእርስ በእርስ ግጭት የሚያተራምሱ ወንጀለኞችን አልሰጥም ከማለት አልፎ በክልሉ ደብቆ እና ሹመት ሰጥቶ በመላው ኢትዮጵያውያን ሕይወት ላይ ከሚቆምረው እንዲሁም እኔ ያልመራኋት አገር ትፍረስ ብሎ የጥፋት ነጋሪት ከሚጎስመው የትግራይ ክልል መንግስት ጋር የፈጠሩት የሸፍጥ የፖለቲካ ሽርክናም ለለውጥ ባላቸው ቁርጠኝነት እና አቋማቸው ላይ ጥርጣሬን የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል:: ታጣቂ የመከላከያ ሰራዊቱን አባላት ቤተ መንግሥት ድረስ በመላክ መፈንቅለ-መንግሥቱ እንኳ ባይሳካ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአደባባይ ፑሽ አፕ ያሰሩት የትህነግ አሻጥረኞች መቀሌ ላይ ተሰባስበው የአገሪቱ መንግሥት ደክሟል አቅም የለውም ባሉን ማግሥት በኢትዮጵያ ህግ ከፍተኛ ወንጀል ነው የሚባለውን ተግባር ዛላአንበሳ እና ሽሬ ላይ የፌደራል መከላከያ ሰራዊቱን የጦር ተሽከርካሪዎች በማገት እና የጦር መሳሪያዎችን በመዝረፍ ጭምር አሳይተው እንዳሻችሁ ሁኑ ተኩሰን እናንተ ከምታዝኑ መንግስታችን ሆደ ሰፊ ነው ይችላችኋል የሚል መግለጫ እንዲያወጣ አስገድደውት ስናይ ሕዝባዊ ድጋፍ ባለው ግን ደግሞ በጥርስ አልባ መንግሥት እንድንመራ ልንረዳ ችለናል:: የመንግስታችን ገርነት እና ሆደሰፊነት ድፍን ዓመት ሊሞላው በተቃረበበት በአሁኑ ሰዓት መከላከያ ሰራዊትን በማገት የተጀመረው ሥርአት አልበኝነት በሌሎችም አካባቢዎች
እንዳይስፋፋ ቆርጦ መታገል አማራጭ እንደማይገኝለት እውነታውን መጋፈጥ የተሳነው የዶክተር ዓብይ አስተዳደር እንዲሁም በአማራ ስም የሚነግዱት የአዴፓ ቁማርተኞች ይባስ ብለው ጥቂት የሕወሃት አመራሮች በፈጸሙት በደል ምንም ያልተጠቀመውን የትግራይ ሕዝብ በጅምላ አትውቀሱት ሲሉ ሕዝብን ሊያሞኙ ደጋግመው መጣራቸው ጊዜያዊም ሆነ ዘለቄታዊ መፍትሄ እንደማያስገኝላቸው ሊረዱት ይገባል ::
በድን እየተባለ የሚወቀሰው ብአዴን አዴፓም ቢሆን በፈጠራ የጥላቻ ታሪክ አሳሩን የሚበላውን እና ለኢትዮጵያ አንድነት ሲል በወራሪ እና ገዥነት ተፈርጆ ለዘር እልቂት የተዳረገውን የአማራ ህብረተሰብ ሕይወት ከመታደግ ይልቅ በውስጡ አማራን ለማጥፋት ቀን ተሌት የሚያሴሩ ሌላ ብሄርን የሚወክሉ ተንኮለኞችን በአመራርነት አስቀምጦ የገዛ ህዝቡን ሲጨፈጭፍ እና እሰር ሲሉት ሲገድል እና ብልት ሲያኮላሽ የኖረ አማራን በዋና ጠላትነት በፖሊሲው ቀርጾ ለማጥፋት ከሚንቀሳቀስ ትህነግ ላይ ሕብረት ፈጥሮ የሚንቀሳቀስ የሙሰኞች የአደርባዮች እና የፈፍሰገዳዮች ቡድን በመሆኑ ሕዝባችን በዚህ የፖለቲካ ነጋዴ ላይ ዕምነቱን ካጣ ዘመናት አስቆጥረዋል:: ለዚህም አያሌ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል :: የሕወሃቱ አባይ ጸሃዬ ለሱዳን የአገርን ዳር ድንበር ከ 23 ሺህ ሄክታር በላይ ለም መሬት ከአማራ ምድር ቆርሶ ሲያስረክብ እንደነ ካሳ ተክለብርሃን ያሉ የብአዲን አመራሮች በቦታው እንደተገኙ እና ሌሎቹም የሕወሃት አሽከር ሆነው ተቃውሞ ያሰሙ ገበሬዎችን በሽብር ወንጀል እየከሰሱ ማዕከላዊ ሲያስቀጠቅጡ የነበሩ ለመሆናቸው የግፉ ቀማሽ ከሆኑት የቀድሞው የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ ሙሉዓለም ገሌ ገለጻ መረዳት ይቻላል:: ወያኔ ያለ ማንም ከልካይ ወልቃይት ሁመራን ጸገዴን አላማጣ ራያን እና ሌሎችንም የአማራ ከተሞች ቀምቶ ወደራሱ ግዛት ሲያካልልም ሆዳቸውን ከመሙላት እና የገዛ ሕዝባቸውን ለእርድ ከማቅረብ በስተቀር የአማራ አዴፓ ድርጅት አባል ነኝ ባይ ካድሬዎች ምንም የፈየዱት አልነበረም:: ትህነግ ከ 4 ዓመታት በላይ በአማራ ክልል ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ውስጥ ለዘመናት ተዋልደው በፍቅር የሚኖሩ የቅማንት ብሄር ተወላጆችን ከአማራው ጋር ደም አቃብቶ ለማለያየት ከ 4 በላይ ወረዳዎችን ከልለው ወታደራዊ ስልጠና በሚሰጡበትም ወቅት ብአዲን አይቶ እንዳላየ በማለፉ ዛሬ በየዕለቱ ከሁለቱም ወገን ሕዝብ በእርስ በእርስ ግጭት እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል :: ጉደኛው አዴፓ ለቅማንት ኮሚቴ ነን ባዮቹ የትህነግ ተላላኪዎች ሱር ኮንስትራክሽን በመባል የሚታወቀው የትግራይ ኢፈርቱ የግንባታ ድርጅት በተደጋጋሚ በከባድ መኪናዎችቹ የጦር መሳሪያ እያመላለሰ እንደሚረዳ መረጃው ቢኖረውም ይህን አማራ ጠል የሆነ ድርጅት ከክልሉ ከማስወጣት ይልቅ ተጨማሪ የግንባታ ስምምነቶችን በክልሉ እየሰጠ ዛሬም ሕዝባችንን የሚያስፈጅ የለየለት የእጅ አዙር ጠላት ሆኖ የሚፈረጅ ድርጅት ሆኗል :: ይህን ሁሉ ህልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍ በገዛ ወገኑ ላይ ሲፈጸም የአማራ ጠላቶች የትግል አጋር እና ተባባሪ የሆነው አዴፓ በዋና አመራሩ አቶ ገዱ አማካኝነት አማራው ላይ ጥቃት በተከፈተ ቁጥር የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ የሚጥሩ ሰላም ኃይሎች ናቸው ከማለት ባሻገር አሽከር በጌታው ሙርጥ ያጨበጭባል እንደሚባለው ተረት አማራን ሰብስቦ የትግራይን ገድል እየዘከረ ሕዝቡ ምንም አልተጠቀመም የሚል ጉንጭ አልፋ ዲስኩሩን ማሰማት የሰርክ ተግባሩ ሆኗል:: ከዚህ ሌላ እራሱ ተበዳይ አማራውን የችግሩ ምንጭ የሚያደርጉ አሳዛኝ መግለጫዎችን በመስጠት ዛሬ ላይ ከተቃጣበት ጥፋት ለመዳን የሚታገለውን ህዝባችንን ቅስም ለመስበር ሲሞክር በተደጋጋሚ መስተዋሉም መቀመጫው ላይ ቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህም የሚለውን ብሂል እንድናስታውስ ያደርገናል:: በመሆኑም በሙስና በአምቻ ጋብቻ እና በእከክልኝ ልከክልህ ላለፉት 28 ዓመታት ተጋምዶ አማራ ጠላቴ ነው ብሎ ከተነሳ ድርጅት ጋር ሕብረት ፈጥሮ ወገኖቹን የሚያጠቃው አዴፓ በቀጣይም የትግል እንቅስቃሴም ቢሆን ከፋይዳው ጉዳቱ አመዛኝ ነውና ከእንግዲህ በቃ ልንለው ይገባል::
በዚህ አጋጣሚ ግን ነገርን ነገር ያነሳዋል ይባላልና እንደው ለመሆኑ ዶክተር አብይ እውን በዓለም ዙሪያ ባሉት ሁሉም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ ምን ያህል የትግራይ ሰዎች ተመድበው እንደሚሰሩ አታውቅም? በመላው ክልል በአስተዳደር መዋቅር ውስጥ በሚኒስትር ቢሮዎች በነጻ የትምህርት ዕድል ስኮላርሽፕ በህገወጥ ንግድ በመላው ክልል በመሬት ነጠቃ እና መቀራመት በሕገወጥ ነጻ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በኮንትሮባንድ እና የሰዎች ዝውውር ንግድ በገንዘብ ምንዛሪ ስንቱን አንስተን ስንቱን እንተው የትግራይ ተወላጆች ያልገቡበት ቦታ እና ያችን አገር ያልመዘበሩበት ሁኔታ እውን አለን ለምን ይዋሻል ???? ትላንት አብረን አንድ የስራ ገበታ ላይ የነበርን ሰዎች ከጽዳት እና ተላላኪነት ተነስተው በትግሬ ዘራቸው ምክንያት የመስሪያ ቤት አስተዳደር ሃላፊ የቀበሌ እና ወረዳ አመራር ሲሆኑ አላየንም?? በአዲስ አበባ ከተሞች የተንጣለሉ ሕንጻዎች አብዛኛዎቹ የማን ንብረት ናቸው ???? አንድ ሰው ያለ አግባብ ሚልዮነር እና ቢልዮነር እንዲሆን ሥርዓቱ በዘሩ ምክንያት ምቹ ሁኔታን ሲፈጥርለት በስሩ የሚኖሩ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እንደሚለውጥ አንርሳ :: ጥቂት የሕወሃት አመራሮች ናቸው የተጠቀሙት የሚለው ተደጋጋሚ ዲስኩር ውሃ የማይቋጥር ከመሆኑም በላይ ተበዳዩ ህዝብ ቁስልም ላይ እንጨት የመስደድ ያህል ነው :: በልቶ አለማመስገን ወይም በቃኝ የሚለውን ቃል አለማወቅ ካልሆነ በስተቀር ዛሬ በቢልዮን የሚቆጠር ብር ካፒታል ያላቸው በትግራይ ክልል የተገነቡ ከ 60 በላይ ግዙፍ የሚሆኑ የኢፈርት ሜጋ ኢንዱስትሪዎች እና ካምፓኒዎችም በሚልዮን ለሚቆጠሩ የትግራይ ዜጎች የስራ ዕድልን ፈጥረዋል እኮ :: ከዚህ በላይ ጥቅም ምንድነው ?? ለአብነት ያህልም የትግራይ ሕዝብን እና ክልል በተለይ ለመጥቀም በኢፈርት ስር ከተቋቋሙ እስከ መቶ የሚደርሱ የልማት እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መካከል መስፍን ኢንዱስትሪያል አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መቀሌ ልዩ ልዩ ኢንጅኖች / ሞተሮች ማምረቻ ኢንዱስትሪ /Mekelle Engine Production Factory has a production capacity of manufacturing 20,000 engines annually/ ስታር እና አዲስ የመድኃኒት ምርቶች ኢንዱስትሪዎች ኢዛና የመአድን ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሼባ የቆዳ ውጤት ምርቶች ፋብሪካ ትራንስ ኢትዮጵያ አድዋ ዱቄት ፋብሪካ ሳባ እብነበረድ ራህዋ የበግ እና ፍየል ኤክስፖርት መሶበ ሲሚንቶ ፋብሪካ አፍሪካ ኢንሹራንስ አክስዮን ዲላቴ ቢራ ፋብሪካ ሰገል እና ሱር ኮንስትራክሽን ሕይወት የግብርና ሜካናይዜሽን ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን መስከረም ኢንቨስትመንት…ወዘት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው :: ይህ እንግዲህ የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና ዓለማቀፍ ተቋማት በተደጋጋሚ በርካታ የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች በግንባር ቀደምትነት ትግራይ ውስጥ መገንባታቸውን ይፋ ያደረጉት ልዩ ልዩ ዘገባን ሳይጨምር ነው :: እና ገና ለገና የጦር መሳሪያ በደህና ጊዜ አከማችተዋል በሚል ፍርሃት አልያም ከትህነግ ጋር ያለው ጥምረት ከፈረሰ መንግስቱም ይፈርሳል ከሚል ሥጋት ከህዝብ በደል በላይ ትግራይ አልተጠቀመም የሚሉት ፈሊጥ ምን ይሉታል ? ለማንኛውም በውሸት ታሪክ ላይ ለመገንባት የምንጥረው መንግስት ውሎ አድሮ በግፉአን ጩኸት መፍረሱ አይቀርምና የወንጀለኞችን ገመና በመደበቅ እና ፍትህን በማዘግየት የምንጓዝበት የተሳሳተ መንገድ እራሳችንን ጠልፎ እንዳይጥለን ብሎም አገራችንንም ከማትወጣበት አዘቅት ውስጥ እንዳይከታት ፍትህን ለማስፈን የጀመርነውን ጥረት ብናጠናክር መልካም ነው የሚል ምክራችንን እንለግሳለን::
በመጨረሻም:- ወያኔ እና አጋሮቹ ኩታ ገጠም ለም መሬቶቹን ለመቀራመት በፈጠሩት የፖለቲካ ሴራ የኢትዮጵያ አንድነት ዋና ምሰሶ የሆነው የአማራ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው ግፍ ግድያ መፈናቀል እንዲሁም አያሌ የአካል እና የስነ ልቦና ጉዳት በድርጅቶችም ሆነ በተቋም ደረጃ ጭምር ተፈጽሞበታል :: ዛሬም ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ባደረገው እልህ አስጨራሽ የነጻነት ተጋድሎ የለውጥ ምዕራፍ ባለቤት ቢሆንም ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በትህነግ የተቃኙት አማራ ጠል የሆኑ ተቋማት ሁሉንም ብሔር ባማከለ ሁኔታ ሥር ነቀል የአደረጃጀት ለውጥ ስላልተደረገባቸው እንደ ፌደራል የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ያሉ መዋቅሮች በወንጀል የሚጠረጠሩ የትህነግ የግል ድርጅቶችን ወታደራዊ ከለላ እና ጥበቃ በማድረግ በአማራው ክልል እንዳሻቸው ጦራቸውን በማዝመት ሕዝቡን በጠራራ ጸሃይ መፍጀታቸው ሃዘናችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል:: የትላንቱ የደርግ ምርኮኛ ወታደር አስር አለቃ የዛሬው የፌደራል መንግሥት የአገር መከላከያ ሰራዊት ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ምንም እንኳ ከወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ነጻ እንደሆነ ብናውቅም ያን ያህል በጭፍን የዘረኝነት ጥላቻ ተሞልቶ በመገናኛ ብዙሃን ፊት ቀርቦ ሰራዊታችን በጎንደር ሰው አልገደለም ወደ ሰማይ ተኮሰ እንጂ ሲል በሕዝባችን ላይ መሳለቁ ተስፋ በተጣለበት የለውጥ ሂደት ላይ አንዳች ጥርጣሬን ማጫሩ አልቀረም:: አቋመ ቢስ ብቻ ሳይሆን አደርባይ እና አቅም አልባ የነበረው አስር ዓለቃ ብርሃኑ ጁላ በህይወቱ አስቦትም ይሁን አልሞት የማያውቀው የስልጣን እና የማዕረግ ኮርቻ ላይ ተፈናጦ ሕጻናት ጭምር በጠገቡ ሰራዊቶቹ የስናይፐር ጥይት አሩር ግንባራቸው እየተነደለ የተቀጩበትን የነፍስ ግድያ ወንጀል ለማድበስበስ መሞከሩ ከታሪክ ተጠያቂነት እንደማያስመልጠው ማወቅ ይኖርበታል:: ወያኔ ለዘመናት ተዋልደው እና ተፋቅረው የሚኖሩ የአማራ እና የቅማንት ብሄረሰቦችን አጋድሎ ተጨማሪ የአማራውን መሬት ሥልታዊ በሆነ መንገድ ለመቀማት የጦር መሳሪያዎችን ሱር ኮንስትራክሽን በተባለ ድርጅቱ ከባድ መኪናዎች ማጋጋዙ ይቁም ፍተሻም ይደረግልን ባለ ሕዝብን ለወንጀለኛው የሕወሃት ድርጅት ወታደራዊ ከለላ ሰቶ ለማስመለጥ ንጹሃንን በግፍ መጨፍጨፍ እንደ ብርሃኑ ያሉ የመከላከያ አመራሮችን የሞራል ውድቀትን እና በአማራው ላይ ዛሬም ያልተቀረፈውን የጥላቻ አባዜ ፍንትው አድርጎ ነው የሚያሳየው:: የኦሮሞ መሪ ድርጅት ኦሕዲድ ከመስረቱ በፊት የቀድሞው ኢሕዲን የአሁኑ ብአዲን ወይም አዴፓ ድርጅት አባል የነበረው የደርግ ምርኮኛ ወታደር አስር አለቃ ብርሃኑ ጁላ የሱዳን ጦር በተደጋጋሚ በመተማ ድንበር እየዘለቀ የአማራ ገበሬ ላይ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና ተሽከርካሪ ታጅቦ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽም ድንበር የማስከበር ተልዕኮውን መወጣት ተስኖት የአማራ ክልል ከአቅሜ በላይ ችግር ገጥሞኛል የመከላከያ ሰራዊት እርዳታን እፈልጋለሁ ባላለበት ሁኔታ ጦሩን አሰማርቶ የወያኔ ዘራፊ እና ወንጀለኛ የግል ድርጅቶችን በአጀብ ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ የቀረጥ ከፋዩን ሕዝብ ገንዘብ ማባከኑም ወንጀሉን እጥፍ ድርብ እንደሚያደርገው ሊታወቅ ይገባዋል:: የዶክተር አብይ አስተዳደርም በየተቋማቱ ሕዝብ በመንግሥት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ውስጥ ለውስጥ ሆን ተብለው የሚሰሩ ከፋፋይ ደባዎችን ነቅተው ሊከላከሉ እንደሚገባ እግረ መንገዳችንን ሳንጠቁም አናልፍም:: ልብ ያለው ልብ ይበል !
የለውጡ ቡድን “እኔ በበላይነት ያልገዛኋት ኢትዮጵያ ትፍረስ” የሚል ምንደኛን ጠላት ወያኔ ያልሰራውን ታሪክ ይዘክራል : ትህነግ ግን መቃብራቸውን አጥልቆ ይቆፍራል – በሬ ካራጁ ይውላል !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !
መይሳው ሳልሳዊ