የአልሸባብ ደጋፊዎች ጥቃቱን አወደሱ

አል ሸባብ ለዛሬው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱን ተከትሎ የጽንፈኛው ቡድን ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ነበር ተብሏል።

በቴሌግራም መልዕክት መላላኪያ የተለቀቁ መልዕክቶች እንደሚያሳዩት ደጋፊዎቻቸው ጥቃቱን ሲያወድሱና በሶማሊያ ያለውን የኬንያ ወታደራዊ ኃይል ላይ ሲዘባበቱ ነበር በማለት ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘግቧል።

በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድኖችን ለመዋጋት እና የሶማሊያ መንግሥትን ለመደገፍ የኬንያ መንግሥት ጦሩን በሶማሊያ ማሰማራቱ ይታወቃል።

    1. ደም ለሚለግሱ ነጻ ትራንስፖርት

      ኡበር ለተጎጂዎች ደም ለሚለግሱ ነጻ ትራንስፖርት እሰጣለሁ አለ

      በናይሮቢ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የደም ልገሳ ጥሪ ቀርቧል። ኡበር የተሰኘው የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢም

      በሽብር ጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ደም ለሚለግሱ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እሰጣለሁ ብሏል።

      ኡበር በትዊተር ገጹ ይፋ እንዳደረገው ወደ ሆስፒታሎች ነጻ የደርሶ መልስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።

      Social embed from twitter

      Uber Kenya

      @uber_kenya

      Nairobi, help assist victims of the tragic Westlands attack by donating blood today! Enter the code NBODONATE & get 2 free Uber rides to the following hospitals: Avenue, M.P. Shah, Aga Khan and Kenyatta Hospitals. Find out more: https://goo.gl/wX2FcR 

    1. ስለ ሽብር ጥቃቱ እስካሁን የምናውቀው

      በናይሮቢ እየተፈጸመ ስላለው የሽብር ጥቃት እስካሁን የምናውቀው

      ጥቃት አድራሾቹ የታርጋ ቁጥሯ KCN 340E Toyota Ractis በሆነች መኪና ወደ ሆቴሉ ሳይመጡ እንዳልቀሩ ተነግሯል።
      Image caption: ጥቃት አድራሾቹ የታርጋ ቁጥሯ KCN 340E Toyota Ractis በሆነች መኪና ወደ ሆቴሉ ሳይመጡ እንዳልቀሩ ተነግሯል።

      ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ የአል ሸባብ ታጣቂዎች እንደሆኑ የተገመቱ አሸባሪዎች ዱሲት2ናይሮቢ ሆቴል ደረሱ።

      የዓይን እማኞች የታጣቂዎቹን ቁጥር ከ4-6 ያደርሱታል።

      ታጣቂዎቹ የሆቴሉ መግቢያ በር ላይ እንደደረሱ ተቀጣጣይ ነገር ወረወሩ። ከዚያም ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰማ። ከዚያም አካባቢው በጥቁር ጭስ ታፈነ።

      ከዚያም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሳይቋረጥ የቀጠለ የተኩስ ድምጽ መሰማት ጀመረ።

      በሆቴሉ ዋና በር አቅራቢያ በሚገኝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ ቆመው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ መኪኖች በእሳት ጋዩ።

      9፡30 ላይ የሽብር ጥቃቱ ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ተዘገበ።

      በጥይት እና በፍንዳታው የቆሰሉ በርካታ ሰዎች በድጋፍ ከሆቴሉ ቅጥር ግቢ ሲወጡ ታዩ።

      10 ሰዓት አካባቢ የእሳት አደጋ ሠራተኞች እና የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች ከስፍራው ደረሱ።

      በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታሎች መላክ ጀመሩ።

      10፡45 የኬንያ ጸጥታ አስከባሪዎች ወደ ሆቴሉ ዘልቆ በመግባት ጥቃት አድራሾቹን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ጀመሩ።

      እስከ ምሽቱ 3፡30 ድረስ የከፍተኛ ፍንዳታ እና የተኩስ ድምጽ ይሰማል።

    1. ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሞተዋል

      የሟቾች ቁጥር ቢያንስ ሦስት ደርሷል

      በዱሲት2ናይሮቢ ሆቴል ምግብ ቤት የተነሳ ፎቶግራፍ ቢያንስ ሦስት ሰዎችን መሞታቸውን ያሳያል።

      የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፎቶ አንሺ በበኩሉ ቢያንስ አምስት የሞቱ ሰዎችን ማየቱን ተናግረዋል።

    1. የዓይን እማኞች

      Quote Message: በህይወት መትረፋችን የፈጣሪ በረከት ነው። ሌሎች የት እንዳሉ አናውቅም። ምን እየተፈጠረ እንዳለም አልገባንም። እንደው ምህረት በዝቶልን ነው። ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ግራ ገብቶናል

      ለቢቢሲ ቃሏን የሰጠች በሆቴሉ ህንጻ ላይ የምትሰራ የዓይን እማኝ።
      Image caption: ለቢቢሲ ቃሏን የሰጠች በሆቴሉ ህንጻ ላይ የምትሰራ የዓይን እማኝ።

      በናይሮቢ ቅንጡ ሆቴል የሽብር ጥቃት መፈጸም የጀመረው ዛሬ ከሰዓት 9 ሰዓት አካባቢ ነበረ።

      በሽብር ጥቃቱ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ አልቀረም ቢባልም እስካሁን ግን የሆስፒታል ምንጮች የአንድ ሰው ህይወት ብቻ ማለፉን ይፋ አድርገዋል።

      በስፍራው የነበረው የኬንያ ፖሊስ ባልደረባ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ‘‘ሁኔታዎች ጥሩ አይደሉም። ሰዎች እየሞቱ ነው።’’

      ሆቴሉ አቅራቢያ የምትሠራ አንዲት ሴት ለሬውተርስ የዜና አገልግሎት ስትናገር ‘‘የተኩስ ድምጽ መስማት ጀመርኩ፤ ከዚያም በርካታ ሰዎች እጃቸውን ወደላይ በማድረግ ሲሸሹ ተመለከትኩ። ህይወታቸውን ለማዳን ወደ ባንክ የገቡም ነበሩ።’’ በማለት ተናግራለች።

      ኬንያ በቅርብ ዓመታት በአል ሸባብ በሚሰነዘሩ የሽብር ጥቃቶች ሰለባ ሆና ቆይታለች። በተለይም ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ከተሞች እና መዲናዋ በርካታ ጥቃቶችን አስተናግደዋል።

    1. ‘‘የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ነው’’

      የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የሽብር ጥቃቱን ‘‘የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ነው’’ ሲሉ ገለጹት።

      ጸጥታ አስከባሪዎች እና ጋዜጠኞች በሆቴሉ ዋና በር። ይህ ፎቶ የተነሳው አምሻሽ 11 ሰዓት አካባቢ ነበር
      Image caption: ጸጥታ አስከባሪዎች እና ጋዜጠኞች በሆቴሉ ዋና በር ላይ። ይህ ፎቶ የተነሳው አምሻሽ 11 ሰዓት አካባቢ ነበር።

      የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የሽብር ጥቃቱን ‘‘የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ነው’’ ሲሉ ገለጹት። የፖሊስ አዛዡ ጨምረውም በሆቴሉ ውስጥ የነበሩ በርካታ እንግዶች ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሟቸዋል ብለዋል።

      ባለ ሰባት ወለል በሆነው የሆቴል ህንጻ ፖሊስ እስካሁን ስድስቱን ወለል መቆጣጠሩን አሳውቋል።

      በሆቴሉ አቅራቢያ የሚገኙ የቢቢሲ ዘጋቢዎች አሁንም ድረስ የተኩስ ድምጽ እየሰሙ እንደሆነ ተናግረዋል።

    1. በሽብር ጥቃቱ 1 ሰው መሞቱ ተዘገበ

      አል ሸባብ አደረስኩ ባለው ጥቃት 1 ሰው መሞቱን 4 መቁሰላቸውን የሆስፒታል ምንጭ አስታወቀ

      በዱሲት2ናይሮቢ አል ሸባብ አደረስኩ ባለው ጥቃት 1 ሰው መሞቱን እና 4 ሰዎች መቁሰላቸውን በናይሮቢ የሚገኝ ኤም.ፒ ሻህ ሆስፒታል አስታወቀ። በሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ክፍል ባልደረባ የሆኑት ቶሴ ዲን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ወደ ሆስፒታላቸው ለህክምና እርዳታ ከመጡት 5 ሰዎች መካከል አንዱ መሞቱን አስታወቀዋል።

      የኬንያ የፖሊስ አገልግሎት ቢሮ ሆቴሉ በሚገኘበት ስፍራ ጥቃት መኖሩን ገልጾ ስፍራው መከለሉን እና አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ በመግለጽ ዝርዝር መረጃዎችን ይዞ እንደሚቀርብ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

      ዱሲት2ናይሮቢ የሆቴል አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን ዌስትላንድ በሚባለው የናይሮቢ ስፍራ ይገኛል።

      ጥቃቱ የተፈጸመው ዌስትላንድስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው
      Image caption: ጥቃቱ የተፈጸመው ዌስትላንድስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው
    1. ሆቴሉ ቅጥር ግቢ ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ስሜታቸውን እየገለጹ ነው

      በሆቴሉ ውስጥ ተደብቀው ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ስሜታቸውን እየገለጹ ነው

      የኬንያ ፖሊስ የሽብር ጥቃቱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥረት እያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በስፍራው የሚገኙ የዓይን እማኞች አሁን የተኩስ ድምጽ በስፍራው እየተሰማ እንደሆነ ይናገራሉ።

      በስፍራው የሚገኘው ሮናልድ እን’ጌኖ በትዊተር ገጹ ላይ በሆቴሉ መታጠቢያ ቤት መደበቁን እና ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ገልጿል። ከባድ ፍንዳታ ከመስማቱም በተጨማሪ ተኩስ መሰማቱንም አክሎ ከተናገረ በኋላ “ዛሬ ከሞትኩኝ ፈጣሪዬን እንደምወድና ለቤተሰቤ እንደምወዳቸው ንገሩልኝ” ብሎ የቤተሰብ አባላት ስም ዘርዝሯል።

  1. ለናይሮቢው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን ወሰደ

    በናይሮቢው ሆቴል ለተፈጸመው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን ወሰደ

    በሆቴሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቆመው የነበሩ መኪኖች ጋይተዋል።
    Image caption: በሆቴሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቆመው የነበሩ መኪኖች ጋይተዋል።

    በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ቅንጡ ሆቴል ላይ ለተፈጸመው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ አለ። የአልሸባብ ቃል አቀባይ በናይሮቢ ለደረሰው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ለቢቢሲ ሶማልኛ በስልክ ተናግሯል። የአልሸባብ ቃል አቃባይ ጨምሮም ”በናይሮቢ ኦፕሬሽን እያካሄድን ነው” ብሏል።

    ከሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የተኩስ ድምጽ ሳይቋረጥ ተሰምቶ ነበር። የአይን እማኞች እንደሚሉት አራት የታጠቁ ወንዶች ወደ ሆቴሉ ቅጥር ጊቢ ሲገቡ አይተዋል።