January 17, 2019e

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዥ ደንበኞች ሻንጣ መጥፋት በአስደንጋጭ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎት ተጠቃሚ መንገደኞች ሻንጣ መጥፋት ከእለት ወደ እለት በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ለአየር መንገዱ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
እንደ መረጃ ምንጫችን ገለጻ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ሻንጣ መጥፋት የተለመደ ቢሆንም ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በአሳሳቢ ሁኔታ የሚጠፋው ሻንጣ ቁጥር እያሻቀበ በሆኑ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ የማስተካከያና የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ ካልቻለ የስታር አሊያንስ ሜምበር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥያቄ ምልክት ሊያስነሳ እንደሚችል አክለው ገልጸዋል።
