January 17, 2019

እዚህ ላይ የኦሮሞ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎችን እናያለን። የአቃቂ፣ የሎሜ፣ የአዳማ ዙሪያና የአዳ ወረዳች።
ከአስራ ሁለት አመታት በፊት በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት፡
በአዳማ 213797 ፣በአዳማ ዙሪያ ደግሞ 155349፣ በቢሾፍቱ 99928 በቢሾፍቱ ዙሪያ በአዳ ወረዳ 130321 ህዝብ ይኖራል። የአዳማ ከተማ ሕዝብ ከአዳማ ዙሪያ ሕዝብ ይበልጣል። የቢሺፍቱ ህዝብ ከአዳ ወረዳ ሕዝብ ያኔ ተቀራራቢ ነበር።የሎሜ ወረዳ 117080 ይደርሳል። እዚህ ውስጥ የሞጆ ከተማ ሕዝብን ያጠቃልላል። የአቃቂ ወረዳ አሁን ከአዲስ አበባ ተቀላቅሏን መሳለኝ ባልሳሳት።
አሁን እነዚህ ወረዳዎች ቁጥራቸው እጅግ በጣም ነው የሚያድገው። ሞጆ፣ ዱከም፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ ወደ ላይ ተተኩሰዋል በሕዝብ ብዛት። እነዚህ ወረዳዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሕብረ ብሄራዊና እንደ አዲስ አበባ አማርኛ ተናጋሪዎች በጣም እየበዙበት ነው። ከአዲስ አበባና ከአማራ ክልል ጋር የተገጠጠሙም ናቸው።
እንግዲህ ቋንቋ እንደ መስፈርት ከተወሰደ፣ ኦሮምኛ ብቻ የስራ ቋንቋ በሆነበት ክልል ውስጥ መቀጠሉ ፍትሃዊ አይደለም።
ህዝብ ድምጹን እንዲሰጥ መጠየቅ ያለበት መሰለኝ። ህዝቡ ምንድን ነው የሚፈልገው? መቼም ተገዶ ከወለጋና ከቦረና የመጡ እንዲያስተዳድሩት መፈቀድ የለበትም !!!!!
ሶስት ምርጫ ቢቀርብለት ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡
፩. አሁን ባለው የኦሮሞዎች ብቻ በሆኑ የኦሮሞ ክልል መቀጠል
፪. ወደ አማራ ክልል መጠቃለል
፫. ከአዲስ አበባ የሸዋ ፌዴራል መስተዳደር መሆን
እስቲ አስተያየት ስጡበት።
ለጊዜው እነዚህን ወረዳዎችን ነው ያነሳሁት። በሚቀጥለው ጊዜ የኦሮሞ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እመለሳለሁ።
ደግሜ እጽፋለሁ ህዝብ ይጠየቅ ነው ያልኩት።ሕዝብ ድምጽ ይስጥ። እኛ እናወቅልሃለን አይባል። አሁን ያለውን የኦሮሞ ክልል ከፈለገ ምርጫው ነው። ግን ወለጋን አርሲ፣ ቦረናና ጂማ ያሉት ለርሱ ሊወስኑለት አይችልም። ወለጋ ያለው በወላጋ ዙሪያ ይወስን። ቦረና ያለው በቦረና። ሽዋን ለሸዋዬዎች ይተዉት !!!
