January 17, 2019

አካደር ኢብራሂም (Akku)

የዚያድ ባሬ ስተራተጂ አስፈጻሚዎች በሶማሊ ክልል በኩል የአፋር መሬትን መያዝ የሚፍልጉት ለምንድነው ?
የዚያድ ባሬ ታላቋ ሶማሌ እዉን ማድረግ ወቅቱ ባይሳካም አሁንም በተለየዩ መንገድ ሶማሌዎች በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ተጽዕኖ ፈጣሪ የመሆን ፈላጎታቸው አልጠፋም።
እንደሚታወቀው ይህንን ለማድረግ ዋና አላማቸው ኢትዮጲያን ማዳከም እንደሆነ በግልጽ ይታያል።
ስለዚህ በቀጠናው በተለይ ለኢትዮጺያ የባህር በር መግብያና መውጫ የሆኑ ቦታዎችን መያዝ የሶማሌዎች ዋና የረጅም ጊዜ ዕቅዳቸው ነው።
በኢትዮጲያ ምናልባት መቼ እንደጀመረ የማይታወቀውና መፍትሄ አልባ የሆነው የኢሳና አፋሮች ግጭት የዚህ አካል ስለመሆኑ በብዙ ማስረጃዎች በማስደገፍ መናገር ይቻላል።
የኢሳ ሶማሌዎች በታሪክም ቢሆን በጀቡቲም ሆነ በኢትዮጲያ እንዳልነበሩ በቅርቡ ዶ/ር በለጠ በላቸው ይሁን በፃፉት ‘’ጀቡቲ የጥገኝነታችን መስፈሪያ’’ በተሰኘ መጽሀፋቸው በደንብ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ከዚህ ረጅም ዘመናት በሓላ የውጪ ወራሪ ሃይሎች ወደ ምስራቅ አፍሪካ መምጣት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ኢሳዎች አፋሮችን ከወራሪዎች ጋር በመሆን እያጠቁ እንደመጡ በብዙ የታሪክ ምሁራን ይነገራል።
የኢሳ ሶማሌዎችም ሆነ አፋሮች ሁለቱም በአብዛኛው የአርብቶ አደር ኑሮ መሰረት ያደረጉ ስለሆኑ ለዘመናት በእነሱ መሃል የሚፈጠረው ጦርነት ሁሉ በዉሃና በግጦሽ የሚነሱ ግጭቶች በማለት አሳንሶ ማየትና ተገቢ የሆነ ትኩረት አለማገኘቱ ችግሩ እንዳይፈታ ካደረጉ ነገሮች አንዱ ነው።
ምንም እንኳ በየጊዜው የሚጋጩት አርብቶ አደሮች ቢሆኑም በተለይ የኢሳዎች የመሬት ማስፋፋት አካሄድ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ድብቅ አላማ ባላቸው ፖለቲከኞች የሚመራ መሆኑ ጉዳዩን ቀረብ ብሎ ላየ ግልጽ ነው።
በንጉሰ ነግስቱ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት በሶማሌ ኢሳዎችና አፋሮች መሃል ሲደረጉ የነበሩ ግጭቶች እና ሽምግልናዎች የሚያሳዩ ማስረጃዎች ላይ እንደተገለጸው በየጊዜው የሚደረጉ ስምምነቶችን አፍርሶ የተገኙት ኢሳዎች ነበሩ። ይሄም እስካሁን በማስረጃ ተቀምጧል።
በነገራችን ላይ አሁን ኢሳዎች የእኛ መሬት ነው እያሉ ያሉት በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የኢሳ-ሶማሌዎችና አፋሮች የግጦሽ ክልል ወሰን ከነበረበት 447 ኪ/ሜ ወደ አሁኑ የአፋር ክልል ገብቶ ነው።
የአሁኑ የኢሳ እና የአፋር ጉዳይ ከድሮ ለየት የሚያደርገው ግን ከግጦሽ ክልልነት ወደ አስተዳደር ክልልነት ከፍ ያለ የፖለቲካ ጥያቄ ለታላቋ ሶማሌ ህልም ማሳኪያ የሚደረግ የመሬት ማስፋፋት ነው።
የኢሳ ሶማሌ ጎሳዎች በህግ፣ በታሪክና በዕውቀት አያምኑም።
ብዙ ጊዜ በብዙ ምሁራኖችና የሀገር ሽማግለዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ካሁን በሗላ ይህ ግጭት ማብቃት አለበት በማለት ለመነጋገር ተሞክሯል። በቁርዓን ሳይቀር ማሃላ ተፈጽሟል።
ይህም ኢሳዎች ብግልጽ እንደሚሉት በባህላቸው በሃይል መውሰድ እስከቻሉ ድረስ የማንም መሬት የእነሱ መሬት ይሆናል የሚል ባህላዊ ህግ እንዳላቸው ይናገራሉ።
በየመንስታቱ የተለየያዩ አጀንዳዎች ቢቀያየሩም የኢሳዎች ዋና ህልም ግን አንድ መዳረሻ ነው።
እሱም በአዋሽ ወንዝ ዳርቻና በሌሎች የአፋር ክልል ስተራተጂክ የሆኑ መሬቶችን በብቼኝነት መቆጣጠር።
ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ከነበሩበት አከባቢ በጣም ገፍቶ በመግባት በተለይ በደርግ ጊዜ በነበረው ጦርነት ውስጥ ብዙ የአፋር መሬቶች ይዘዋል።
እንዲያዉም ኢሳዎች በደርግ ጊዜ በጣም ወደ አፋር እየገቡ ሲመጡ የወታደራዊ መንግስት አንድ አዋጅ አውጆ እንደነብረ ይነገራል።
እሳዎች ከመንገዱ 25 ኪ/ሜ ወደ አፋር መሬት ገብቶ ከተገኙ በወታደር እርምጃ እንዲወሰድባቸው ታውጆ እንደበረ ይታወቃል።
የደርግ መንግስት ወድቆ የወያነ መንግስት ሲገባ ኢሳዎች አሁንም የመሬት ወረራ አካሀዱ።
ለኢህአዴግ መንግስት አቤት ቢባልም በጊዜው የኤርትራ ጦርነት እንደ ምክንያት ተነግሮ የአፋር ጥያቄ ሰሚ አጣ።
ጦርነቱ ካበቃ በኃላ ግን የወያነ መንግስት ከጀቡቲ ጋር ባደረገው የወደብ ስምምነት ጋር በተያያዘ ኢሳዎችና የወያነ ጀኔራሎች በዛ አከባቢ ሲፈልጉ ጦርነት፣ ሲፈልጉ ሌብነት፣ ሲፈልጉ ደግሞ እርቅ እየፈጸሙ የኮንትሮባድ ቀጠና አደረጉት።
እስካሁኑ ግጭት የነበረው ሁኔታ ይህን ይመስላል።
ባለፉት 28 አመታት ከወያነ ጋር በመሆን በእነ አባይ ጸሃዬ ወሳኝነት 3ቦታዎች ልዩ ቀበሌ ተብሎ እንዲሰጣቸው ደረጓል።
እነዚህ ከተሞች ጋዳማይቱ፣ ኡንዳፎዖ እና አዳይቱ የሚባሉ ሲሆኑ ለ28 አመታት አንድ አፋር እዛ አከባቢ በሰላም እንዳይንቀሳቀስ፣ በሰላም እንዳይኖር የሽብር ቀጠና ተደርጎ በሌላ በኩል ደግሞ የአፋር ህዝብ እራሱን እና መሬቱን እንዳይከላከል በሪሞት እያስተዳደሩ እዚህ ላይ ተደርሷል።
አሁን ደግሞ አራተኛው የመንግስት ለውጥ ላይ ደርሰናልና ኢሳዎች በዚህ ሁኔታ የያዙትን መሬቶች ወደ ሶማሌ ይካለሉልን እያሉ ያሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
ባለፉት አመታት ከወያነ ጋር በመሆን በእነ አባይ ጸሃዬ ወሳኝነት እነዚህ ቦታዎች ልዩ ቀበሌ ተብሎ እንዲሰጣቸው ደረጓል።
ይሁን እንንጂ ይህንን ውሳኔ በአፋር ህዝብ ዘንድ ምንም አይነት ተቀባይነት የለዉም። እንዲያዉም የኢትዮጲያ መንግስት ጉዳዩን በገለልተኛ አካል አጥንቶ ኢሳዎች በሃይል የያዙት የአፋር መሬቶች ሊያስመልስ ይገባል።
ማጠቃልያ፥
አሁን በሀግራችን ያለው ሁኔታ የለውጥ ባህሪ ነው እየተባለ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ይገኛል።
ከልቡ በኢትዮጲያዊነት የምያምን ሁሉ ስጋት ውስጥ ይገኛል።
ከብሔሮች ከፍ ብሎ ኢትዮጲያዊነት የሚል መሪ በተገኘበት፣ ከኢትዮጲያ ከፍ ብሎ አፍርካ በሚንልበት በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሃይሎች ውስጥ እንኳ ይህንን ችግር እንዳይፈታ የሚሰሩ ሰዎች አሉ።
የአሁኑ ኢሳና የአፋር ግጭትም ለአሁኑ የኢትዮጲያ ሁኔታ ተጨማሪ ፈተና እንዲሆን ተደርጎ በሰልጠና እና በሎጂስትክ ተደግፎ የተዘጋጀ እንደሆነ በጣም እርግጠኛ ነኝ።
ስለዚህ መንግስት አዲስ አበባ ላይ በሚቀርበለት ሪፖርት ብቻ ሳይሆን የተለየ ትኩረት በመስጠት ጉዳዩን ማርገብ ሳይሆን ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አለበት።
የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እዛ አከባቢ ላይ እንዳይሰፍር የሚያደርጉ የኦጋደን ነጻ አውጪ ግንባርና ሌሎች ታጣቂዎችን የፌደራል መንግስት ማስቆም አለበት።
ልዩ ሃይሉ ያልተመጣጠነ እርምጃ ይወስዳል ለሚለው ክስ የፌደራል መንግስት ልዩ ሃይሉ ከአከባቢው ሳይወጣ በቅንጅት ሊሰሩ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከአፋር ክልል መንግስት ጋር መምከር አለበት።
ከዚህ ዉጭ ግን በአፋር ክልል ለሚገኙ ኢሳዎች ጉዳይ ላይ የሶማሌ ክልል መንግስት የሚሳተፍበት ምክንያት ግልጽ መሆን አለበት።
ኢሳዎች እንደማንም ዜጋ በሰላም መኖር ካለባቸው የአፋር ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስት ብቻ ሊመለከተው ይገባል።
ግልጽ ያልሆኑ ከጀቡቲ እስከ ዲሬ ዳዋ እንዲሁም ጂጂጋ የሚደረጉ ውይይቶች የህዝብን ጥርጣረ ከመጨመር ዉጭ ምንም ወጤት አያመጡምና።
አበቃሁ !
ቸር ያሰማን። Ahak Aysuk !