ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ግፍ ተፈጽሞባቸው ነፍሳቸውን ከአውሬ አድነው ባሕርዳር የገቡ ልጆችህ በአሁኑ ሰዓት ለምን “አማራነታችን የመጠቂያ ምክንያት ከሆነበት ዩኒቨርሲቲ ተቀይረን አማራነታችን የመጠቂያ ምክንያት ወዳልሆነበትና ደኅንነታችን ተጠብቆ መማር ወደምንችልበት አካባቢ መማር የምንችልበት ዕድል ይመቻችልን??? ይህ የዜግነት መብታችን ነውና!!!” ብለው ስለጠየቁና ለዚህ አግባብነት ላለው አንገብጋቢ የአማራ ተማሪዎች ጥያቄ አግባብነት ያለው መልስ መስጠት ያልፈለገውና ተማሪዎቹ በአረመኔ ተበልተው እንዲያልቁ የፈለገው ብአዴን ጥቃቱ ወደተፈጸመባቸውና ከፍተኛ የደኅንነት ሥጋት ወዳለበት እንዲሁም ዋስትና ወደማይሰጥበት ቦታ “ተመልሳቹህ ሒዱ ከዚህ ውጭ ልናደርግላቹህ የምንችለው ነገር የለም!” በማለት ይህ ግዴታውንና ኃላፊነቱን መወጣት ፈጽሞ የማይፈልገው የቅጥረኛው ብአዴንና “በጸጥታና ደኅንነት ጉዳይ ላይ ከብአዴን ጋር አብሬው ለመሥራት ተስማምቻለሁ!” ባዩ የልጁ የአብን የጥፋት ኃይል በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎቹን ካረፉበት ቦታ እየጎተቱና እየቀጠቀጡ አስወጥተዋቸዋል፡፡
የወያኔ ቅጥረኛው ፀረ አማራ ብአዴን የተባለው የጥፋት ኃይልም ይሄንን ሕገወጥ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያመቸው ተማሪው ሰልፍ በሚወጣበት ሰዓት የራሱን ኃይል ከተማሪዎቹ ጋር ቀላቅሎ በማሰማራትና ድንጋይ እየወረወሩ ንብረት እንዲያወድሙ በማድረግ ጥቃቱን ተማሪዎቹ የፈጸሙት አስመስሎ አሳይቷል፡፡
ብአዴንን የምናውቀው በእንዲህ ዓይነት ሸፍጥ አማራን እየወነጀለ ሲፈጅና ሲያስፈጅ እንጅ ከሕዝብ ለሚነሡ ጥያቄዎች አግባብነት ያለው ምላሽ ሲሰጥ አይደለምና የሚደንቀን አይሆንም!!! ከደነቀም ብአዴንን “ተለውጧል!” የሚሉ ቂሎችን ይድነቃቸው!!!
የአማራ ሕዝብ ሆይ! አሁን በዚህ ሰዓት ከልጆችህ ጎን ቆመህ ጥያቄያቸውን አብረህ እያስተጋባህ መብታቸውን ማስከበር ካልቻልክና በኃይል ወደመጡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲመለሱ ተደርገው ነገ በአውሬዎች ተጨፍጭፈው ቢያልቁ ከገዳዮቻቸው ጋር ተባብረህ እንዳስፈጃሃቸው እወቅ!!!
እነኝህ ከቡሌሆራ የመጡ ተማሪዎች ብቻ አይደሉም የአደጋ ሥጋት ላይ ያሉት በሌሎች ከዚህ ቀደም ጥቃት በተፈጸመባቸው ዩኒቨርሲቲዎችም ያሉ ተማሪዎች አሉ፡፡ አደጋ ከመጣሉ በፊት በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የአማራ ተማሪዎች ጉዳይም ታይቶ ደኅንነታቸው ተጠብቆ ከሥጋት ነጻ ሆነው መማር ወደሚችሉበት ማለትም በትውልድ አካባቢዎቻቸው አቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተደልድለው እንዲማሩ መደረግ አለበት!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
