ባለፈው ሰሞን ጋዜጠኛና አክቲቪስት (ስሉጥ) ርዕዮት ዓለሙ ዕለታዊ በተሰኘው የኢሳት ዝግጅት ላይ እርስ በእርስ የሚጋጩ የአጭሉጉን የዐቢይን መግለጫዎች በተመለከተ በተነሣ ዱላ ቀረሽ ክርክር ሲሳይ አጌናን፣ አበበ ገላውንና መሳይ መኮንንን ቀልባቸውን ክፉኛ ከገፈፈችበትና ከሕዝብ መሸፈጣቸውን ማስመሰያ ክንብንባቸውን ገፍፋ በመግለብ ካጋለጠችበት ዝግጅት በኋላ ዕለታዊ የተሰኘው ዝግጅት እንዲቋረጥ ወስነው ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በቋሚ የኢሳት ቤተሰብ ወይም ደጋፊዎች ጩኸት ዝግጅቱን ከሳምንት በኋላ ለመመለስ ተገደው መልሰውታል፡፡

ይሁንና ግን የዝግጅቱን ሰዓት ርዝመት በእጅጉ አሳጥረውታል፣ ለውዝግብ የሚዳርጉ ርእሶችም እንዳይቀርቡ አድርገዋል፡፡ አስቀድሞም ዝግጅቱን ሲያቋርጡት በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ሳይገልጹ ነበር አቋርጠውት የቆዩት፡፡ ዝግጅቱን ሲመልሱት ግን የሆነ ምክንያት መጥቀስ ነበረባቸውና ስቱዲዮው (መከወኛ ክፍሉ) ዜና እና ሌሎች ሳምንታዊ ዝግጅቶች እየተቀረጹበት ሲቀርቡ እየተመለከትን ስቱዲዮ (መከወኛ ክፍል) ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ነው ዕለታዊ ለሳምንት ተቋርጦ የነበረው!” የሚል ሐሰተኛ ምክንያት ሰጡ፡፡

ከዚህ ሁነት ጋር ተያይዞ አቶ መለስን አስደንግጦ ለሞት የዳረገው ጀግና!” እየተባለ ይወደስ ይመሰገን የነበረው የኢሳት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ለኢሕአዴግ ሊቀመንበር ለአቶ ዐቢይ ምክንያታዊ ባልሆነና ለትዝብት የሚዳርግ ግብዝነት በተሞላበት ሁኔታ ጥብቅና ሲቆም ቀልቡ መገፈፉና በዚህ አቋሙ ሲቀጥልም የቀደመ ስሙን ሊሰብር በሚችል መልኩ በተደጋጋሚ ሊዋረድ እንደሚችል ስለገባው ወዲያውኑ ነበር መልቀቂያ ደብዳቤ ያቀረበው፡፡

የኢሳት ቦርድም (ባለአደራም) ከራሱ ሰዎች ሲያማርጥ ቆይቶ አሁን አቶ ታማኝ በየነን እንደሾመ እየተነገረ ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ ግን ኢሳት የግ7ና የሸአቢያ መሆኑ አንዴ ታውቋልና ከታማኝ ይልቅ የኢሳት ዓለም አቀፍ የሥራ አመራር ዋና ኃላፊ የሆነውን አቶ ነአምን ዘለቀን ዕድገት ሰጥቶ በአበበ ገላው ቦታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢያደርገው ይሻል ይመስለኛል፡፡ አቶ ነአምን ዘለቀ የግ7 አመራር መሆኑ ይታወቃል፡፡

ስለ ታማኝ በየነ ካነሣን ዘንዳ በቅርቡ ኢሳት ላይ የታማኝ እንግዳ በሚል ርእስ በሚተላለፈው ዝግጅት የተመለከትኩትንና የገረመኝን ነገር ተናግሬ ልለፍ፡፡ ይህ የተመለከትኩት ዝግጅት ከዓመት በፊት የተቀረጸና ለረጅም ተከታታይ ሳምንታት ሲተላለፍ የቆየው ከመታሰቢያ ቀጸላ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ የመጨረሻ ክፍል ነበር፡፡

ጋዜጠኛ መታሰቢያ አንዳንዶቹ ታማኝ ለማኝ ይሉሃል ለማኝ ነህ እንዴ? ምን ትላቸዋለህ እነዚህን ወገኖች?” ብላ ጠየቀችው፡፡ እሱም በመልሱ አዎ በኢሳትና በሌሎች ስም ለምኖ እያጭበረበረ ይበላል!’ ይሉኛል፡፡ እኔ ግን የምለምነው ለኢሳትና ችግር አደጋ ለገጠማቸው ወገኖቻችን ነው፡፡ ወይ አለመተዋወቅ እኔነኝ ለምኘ የምበላው? እኔ መለመን ብፈልግ ሃያ ብር ከምለምን ሸህ አላሙዲን ወንድሜ ነው፣ ጓዳየ ነው፣ ወዳጀ ነው እሱን መለመን እችል ነበረአለና ከሸህ አላሙዲን ጋር ሲጨፍር የሚያሳይ እና ይሄንን በፎቶ (በምሥለ አካል) ያያያዝኩላቹህን ትዕይንት የሚያሳይ የሠርጉን ቪዲዮ (ትዕይንተ ሁነት) አሳየ፡፡

ከአላሙዲን ጋር ባለው ቅርበት የተነሣም ሰዎች ጸያፍ የሆኑ ስድቦችን እንደሚሰድቡትም ገለጸ፡፡ አስቀድሞም ለሌሎች ሕመም ለገጠማቸው ከያኔያንም ሳይቀር አላሙዲንን ጠይቆ ከሀገር ውጭ እንዲታከሙ እንዳደረገም ገልጿል፡፡

እኔን የገረመኝ ታማኝ ይሄንን የሚለን በ1983 እና 1984.. ላይ ቢሆን ኖሮ ምንም ባልገረመኝ ባልደነቀኝም ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን የሸህ አላሙዲን ማንነት ማለትም ከመጀመሪያው ጀምሮ የወያኔ ቀኝ እጅና ዋነኛ የትግል አጋር መሆኑ ግልጽ በሆነ መልኩ በሕዝብ ዘንድ በታወቀበት ወቅት ታማኝ እንዲህ ማለቱ እጅግ በጣም ገርሞኛል አስደንግጦኛልም፡፡

አላሙዲንን በተመለከተ ስንት መረጃ ከወጣ ከዚያ ሁሉ ነገር በኋላ ታማን አሁንም ለአላሙዲን ክብርና ፍቅር እንዳለው ደፍሮ መናገሩ በጣም በጣም ገርሞኛል ደንቆኛልም፡፡ በእውነት ነው የምላቹህ ወዲያውኑ ያልኩት ይሄ ሰው የዚህን ያህል ቆሻሻና ደደብ ነው እንዴ ለካ???” ነው ያልኩኝ፡፡ በእውነት ነው የምላቹህ ታማኝ የሚባል ሰው በጣም አስጠላኝ!!!ለምን መሰላቹህ? እንደምታስታውሱት በፊት ስለታማኝ ያለኝን አድናቆት ከፍ አድርጌ ገልጨ ባለው ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ግንዛቤ ግን መረዳት ያልቻላቸው ጉዳዮች ስላሉ ነው እንጅ በአማራ ማንነቱ አማራ ለተጋፈጣቸው የህልውና ፈተናዎች መታገል ጠልቶ አለመሆኑን የሚተነትን ረጅም ጽሑፍ አስነብቤ ነበር፡፡

በዚያ ጊዜ አንዳንድ ታማኝን በቅርበት የሚያውቁትና በሥራ ዓለም አብረው ያሳለፉ ጓደኞቹ ታማኝ ከአላሙዲን ጋር አለው የሚሉትን ግንኙነት፣ አሜሪካ ቤት ገዝቶ የሰጠው አላሙዲን መሆኑን፣ በአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ ያሰጠው እሱ መሆኑን፣ ሚስቱም እሱም ሥራ እንደማይሠሩና አላሙዲን ባንክ (ቤተ ንዋይ) ባስቀመጠላቸው ገንዘብ እንደሚኖሩ ወዘተርፈ. እያሉ የጻፍኩት ጽሑፍ ፈጽሞ ለታማኝ የሚገባ አለመሆኑን ተቃውመውኝ ነበር፡፡ በጊዜው እንኳንና ላምናቸው ይቅርና የፌስቡክ (የመጽሐፈ ገጽ) ጓደኝነታችንን እንኳ ሳይቀር ብሎክ በማድረግ (በማገድ) ነበር የሸኘኋቸው፡፡

በዚያ ሰዓት እነኝህ አስተያየቶች የጠላት ወሬ ወይም ከጥላቻ የመነጩ የሐሰተኛ ስም አጥፊ ሰው ሐሰተኛ ወሬ መስሎኝ ነበር፡፡ በእርግጥ አሁንም ለተባለው ሁሉ አስተማማኝ ማረጋገጫ አላገኘሁም፡፡ ይሁንና ግን የሠርጉን ወጪ የሸፈነለትና አብሮ ታድሞ የዳረው አላሙዲን መሆኑን እራሱ ታማኝ የሠርጉን ቪዲዮ (ትዕይንተ ሁነት) በማሳየት ማረጋገጡና ታማኝ ከላይ “…እኔ መለመን ከፈለኩ ወንድሜን፣ ጓደኛየን፣ ወዳጀን አላሙዲንን አልለምንም?” ሲል የተናገራት ነገር የተባለው ነገር እውነት ነው ማለት ነው!” ለማለት አስገድዶኛል፡፡

ምክኒያቱም ታማኝ አሜሪካ ከመግባቱ አሜሪካን ሀገር ቤት ለመግዛት የሚያስችለው ከፍተኛ ገንዘብ እንዳልነበረው ወይም ቤት ለመግዛት የሚያስችለውን ሥራ እንዳልሠራ ማንም ያውቀዋልና ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ቢሆን እስከአሁን ድረስ ታማኝ አሜሪካን ሀገር ሥራ ተቀጥሮ ሲሠራ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ሚስቱም ሥራ አትሠራም፡፡ እና ታዲያ ታማኝ ሥራ ካልሠራ፣ ሚስቱም ካልሠራች፣ ለኢሳትና ለተቸገሩ ወገኖች እርዳታ ሲያሰባስብም ከተገኘው እርዳታ ኮሚሽን (የድካሙን) እንዲከፈለው ወይም እንዲታሰብለት የማይፈልግ ከሆነ አሜሪካን ሀገር እንዲህ ተንቀባሮ የሚኖርበትን ገንዘብ ከየት አገኘው ታዲያ???

ከሁሉም ነገር እጅግ በጣም የገረመኝና የደነቀኝ ነገር ቢኖር ታማኝ ይሄንን ጉዱን ይዞ እንደ ጀግናና ሀገር ወዳድ ዜጋ ከሰው ፊት ለመቅረብ መድፈሩ ነው፡፡ ኧረ ለመሆኑ ታማኝ በምን ሞራሉ (ቅስሙ) ነው ታዲያ ነዋይ ደበበን ለወያኔ አሸርግደሃል!” ብሎ እንዲያ ሊጸየፈውና ሊጠላው የቻለው በሞቴ???

ታማኝ አላሙዲን ወያኔ እንደሆነና ከወያኔ ጋር ባለው ግንኙነት ሀገራችንን ጋጥ አድርጎ ዘርፎ ሀብት እንዳካበተ ቢያንስ በአሁኑ ጊዜ አያውቅም እንዴ??? አላሙዲን ወያኔ በረሃ እያለ ጀምሮ ወያኔ በዝርፊያ ያካበተውን ሀብት ያሥተዳድር እንደነበርና አሁንም አላሙዲን ካለው ሀብት የተወሰነው የወያኔ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ባረጋገጡበትና የኢትዮጵያ ሕዝብም ይሄንን ጉድ ባወቀበት ዘመን እንዴት ነው ታማኝ ላያውቅ የሚችለው???

አላሙዲን ወያኔ ሥልጣን ሲይዝ አብሮ ገብቶ የውጭ ዜግነት ላለው ሰው የማይፈቀዱ የኢንቨስትመንት (የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት) ዘርፎች ላይ ተሠማርቶ ከወያኔ ጋር ሀገር ሲዘርፍ ሲያራቁት የኖረ ወንበዴ መሆኑን፣ ሕግና ደንብ የሚባል ነገርም እሱ ላይ የማይሠሩ መሆናቸውን የ27 ዓመቱ የወያኔ የግፍ አገዛዝ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶ እያለ እንዴት ነው ይሄንን ጉድ ታማኝ ላያውቅ የሚችለው ጃል???

ታዲያ ታማኝ እንዲህ ዓይነቱን ወንበዴ እያመለከ፣ እያከበረ፣ እያፈቀረ፣ ከሀገርና ከድሃው ሕዝብ የተዘረፈን ሀብት እየበላ በምን ሞራሉ ነው ሰዎች ላይ ጣት ለመጠቆምና ወያኔን ለመቃወም የሚደፍረው በሞቴ??? እኔን እጅግ የደነቀኝ ነገር ቢኖር ይሄ ነው፡፡

ነው ወይስ ታማኝ እራሱ በእጁ ካልዘረፈና ካልሰረቀ በስተቀር በሰው ተዘርፎና ተሰርቆ የሚሰጠውን ገንዘብ እንደስርቆት አይቆጥረውም??? ጭንቅላቱ የዚህን ያህል ማገናዘብ የማይችል ደንቆሮ ነው እንዴ ታማኝ ማለት??? ለእኔ በታማኝ በየነና በነዋይ ደበበ መሃከል ምንም ልዩነት የለም!!! እንዲያውም ጉዱን በጉያው ሸሽጎ ሰው መስሎ ከሚቀርበውና እንደ ንጹሕ ሰው በሌሎች ላይ ጣት ከሚቀስረው ታማኝ በየነ ይልቅ ግልጽ ወጥቶ ወራዳነቱንና ሕሊናቢስነቱን በግልጽ ለሕዝብ እያሳየ የሚልከሰከሰው ነዋይ ደበበ ይሻለኛል!!!

ለማንኛውም የምትቀርቡት የምታውቁት ሰዎች ታማኝን ወራዳ፣ አሳፋሪ፣ ነውረኛ፣ አዋራጅ፣ ቆሻሻ ነህ!!! በጣም እጅግ በጣም አዝኛለሁ፣ ብትሞትና ዳግመኛ ባለይህ ደስታውን አልችለውም!!!” በሉልኝ አደራቹህን???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com