የደራ አማራ ማንነት ኮሚቴ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ አስገባ
ኢትዮጵያዉያን ተደባልቀዋል፤ ተጋብተዋል። በአንድ አካባቢ መቶ በመቶ አንድ ብሄረሰብ ብቻ አይደለም የሚኖረው። በዘር አካባቢዎችን መሸንሸን የይግባኛል ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ የታወቀ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ የጋሪ ማህበረሰብ ኦሮሞ ተደርገው ነበር የሚታዩት። ኦሮሞኛ ቢናገሩም ሶማሌ ነን አሉ። ጃርሶ አካባቢም እንደዚሁ። ወልቃይት ትግሬ ነው አማራ ነው የሚል ዉዝግብ አለ። ትልቁ አደጋ ደግሞ በአማራና በኦሮሞ መካከል ነው የሚሆነው። በተለይም በሸዋ ዙሪያ። የአዲስ አበባ ጉዳይ የታወቀ ነው። እነ በቀለ ገርባ ፊንፌኔ ኬኛ ይላሉ፣ እነ ዶ/ር ደሳለኝ ደግሞ የለም አዲስ አበባ የአማራ ናት ይላሉ። ይኸው ከዚህ በታችን እንደተዘገበው በደራ አማራ ነን የሚል ጥያቄ እየቀረቡ ነው።
በደራ ዙሪያ የሚከተለውን ከደራ ነዋሪ ዘገባ ደርሶናል”ሺ ጊዜ ለክተህ አንድ ጊዜ ቁረጥ” ይህ አባባል ከደራዎች ነው ለምን ይህን እንዳሉ እነሱ ያውቃሉ።
ደራ የቃሉ ትርጓሜ ሞቅ ሞቅ አለ ደመቀ ፈካ ሲሆን በሸዋ ውስጥ የሚገኝ ወረዳ ነው። በዚህ ወረዳ ውስጥ 85%ቱ ፍፁም አማራ ሲሆን 15% ያህሉ ከሁለት ወገን የሚወለድና ኦሮሞ ብሔረሰብ በጋራ የሚኖርበት ወረዳ ነው። የወረዳውን ህዝብ አሰፋፈር ከስር ይመልከቱ። ታዲያ ይህ ወረዳ ከ1983 በፊት በነበረው አስተዳር መርሃቤቴ ስር የሚተዳደር የነበረ ሲሆን ከዚያ በኅላ በወያኔ በብአዴን እና ኦህዴድ ስምምነት ያለ ህዝቡ ፍቃድ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲካለልና ኦሮሞነት በግድ እንዲቀበል እየተገደደ የኖረ ህዝብ ነው።
ደራ ውስጥ 39 ቀበሌ አለ
21 ቀበሌ ሙሉ ለሙሉ አማራ ነው
7 ቀበሌ ኦሮሞ ነው
11 ቀበሌ አማራ እና ኦሮሞ ነው
ከ 85 % አማራ ነው ወረዳው
ደራዎች ከዚህኛው ጥያቄ በፊት በተደጋጋሚ ይፋዊ የማንነታችን ይከበልን አቤቱታቸውን ያሰሙ ሲሆን ዛሬ ላይ የትግላቸውን ምሬት በሚያሳይ መልኩ አዲስ አበባ ድረስ ተጉዘው ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
በዚህ የዛሬው የአዲስ አበባ ጉዞ ከ 200 በላይ የደራ ነዋሪዎች ከዚያው ከደራ ድረስ የመጡ ሲሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት በተወካዮች ምክር ቤትና በሌሎች መንግታዊ ተቋማት በር ላይ በመገኘት ድምፃቸው በአደባባይ አሰምተው።
ማሳሰቢያ የደራ አማራ ማንነት ኮሚቴ ሁሉንም መስፈርቶች አሟልቶ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፤ለተወካዬች ምክር ቤት፤ለጠቅላይ ምኒስትር ፅህፈት ቤት፤ለአማራ ክልል፤ለኦሮምያ ክልል፤ለሁለቱም ክልሎች ፕሬዝዳንቶች እና ምክር ቤቶች ደብዳቤ አስገብቷል።
የዛሬውንም ሰልፍ በማስመልከት ለኢቢሲ ለአማራ ቴሌቪዥን ለፋና ለዋልታና ሌሎች ሚድያዎች ደብዳቤ ተፅፏል።




