(Wubshet Mulat)
********
አልጣሽ ፓርክ ወደ ፌደራል መንግሥት የዞረው በ2006 ዓ.ም. ነው። ከዚያ በፊት በአማራ ክልል ሥር ነበር። ለምን ወደ ፌደራል እንደተዛወረ በቂም አሳማኝም መረጃ የለም። ፓርኮች በፌደራል መንግሥት ሥር እንዲተዳደሩ የሚደረግበትን መሥፈርትም አያሟላም። (አዋጅ ቁጥር 541/1999 አንቀጽ 4ን ይመልከቱ!)

በዚያ ላይ የአልጣሽ አካል የነበረው አሁን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በመተክል ዞን ሥር የሚተዳደረውን የ”አውጀሚስ” ፓርክንም በመጨመር በአንድነት የፌደራል ፓርክ አልሆኑም። ከአልጣሽ የተቆረጠው ‘አውጀሚስ’ የክልል፣ አልጣሽን ግን ነጥሎ ፌደራል ወሰደው።

በምዕራብ ጎንደር የሚግኘው የአልጣሽ ብሂራዊ ፓርክ

የናይጄሪያ ፈላታዎች ቋሚ መኖሪያ እንዲሆን አደረጉት። የክልሉ መንግሥት ሊያሠራው የነበረውን 502 ኪ.ሜ. የውስጥ ለውስጥ መንገድ ፌደራል መንግሥቱ ሲረከበው የውሃ ሽታ ሆነ። ለምን መንገዱ ተሠረዘ? ወይም አልተሠራም? የአቅም ችግር እንዳይባል እንኳን የፌደራል መንግሥቱ የክልሉም ሊያሠራው ጥናቱ ሁሉ ተጠናቆ ነበር። መንገዱ ቢሠራ ፈላታዎቹ አይኖሩም። መንገዱ ቢሠራ የወያኔ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ አይኖርም። መንገዱ ቢሠራ ብዙ ነገር ይከተላል።

ልብ በሉ። ከአልጣሽ በደቡብ ምእራብ አቅጣጫ ፣ ቤነሻንጉል፣ አልመሃ ላይ ሠፋፊ የእርሻ መሬቶችን ልክ እንደ ጋምቤላ በሕወሃት ባለሃብቶች ይዞታ ሥር ሆነዋል። የእርሻ መሬቶቹን ሰበብ አድርገው የሚሠራው ሥራ እየተሠራ ነው።

በአልመሃ በኩል የአልጣሽ ፓርክ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሆኗል አሉ። ማሠልጠኛው ያለው ‘አይበዛ’ ላይ ነው። አይበዛ ላይ ያለው የፓርኩ ስካውቶች ካምፕ አገልግሎት አይሠጡም። ስካውቶቹ እንደምን አድርገው የወንበደዎቹን ወታደር ይቋቋሙታል? የፈላታዎቹንስ ጥቃት በምን መንገድ ይከላከሉታል? አይደለም ፈላታዎቹን ከብቶቻቸውን መቋቋም ከባድ ነው። እንግዳ ሰው ካዩ አሳድደው ይዋጋሉ።

ወያኔ በፓርኩ በስተደቡብ ምእራብ ላይ የነበረውን የጉምሩክ ጣቢያ (ኦሜድላ) ክፍት አድርጋዋለች። ያሻትን አስገብታ ያሻትን ወደ ሱዳን ታስወጣበታለች። ኦሜድላ የአልጣሽ አካል ነው።

በአጭሩ አልጣሽ ሌላው የወያኔ ምሽግ ሆኗል። ወንበዴውን፣ በቅማንት ኮሚቴ ስም የምትጠራውን ቡድንም ታሠለጥንበታለች። ‘አይበዛ’ን አንዱ ጣቢያ በማድረግ።

ብ/ጀ አሳምነው ጽጌ በአማራ ክልል ውስጥ የተደመሰሱትንም አሁንም ላይ ያሉትን የባቲ ወታደራዊ ማሠልጠኛዎች (ጎረቤት ክልል ላይ ያሉትንም ጨምሮ) አስተያየት መስጠታቸውን ያስታውሷል።

የአለፋ ወረዳ የአስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዛሬ በቋራ ፋኖዎች ወደ አልጣሽ ሲሔድ መያዙንም ልብ ይሏል።

በምዕራብ ጎንደር የሚግኘው የአልጣሽ ብሂራዊ ፓርክ

አልጣሽ የወንበዴዎች ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሆኗል አሉ! ከመይሳዉ ምሽግ የወንበዴ ምሽግ ይሆን ዘንድ የተጓዙትን እርቀት ተመልከቱት!

————–

ናይጄሪያዊ ዘላን አርብቶ አደሮች በኢትዮጵያ፤ አማራ የፈላታ (Fellata) ማኅበረሰብ በአልጣሽ ፓርክ፤ ቋራ

ውብሸት ሙላት

ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚኖሩት የናይጀሪያ ዘላን አርብቶ አደሮች ለማዉጋት በቀጠሯችን መሠረት መጥተናል፡፡ ይህ ነገር ለሰሚዉ ግራ እንደሚሆን ይገባኛል፡፡ እኔም በአንድ ወቅት ግራ ገብቶኝ ምን ትኩረት ሳልሰጠዉ አልፌዉ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነበር፡፡ ኤልቲቪ ላይ ሰፊዉ ምህዳርላይ ዉይይት እያደረግን ሳለ በመካከል አንዱ፣ እግረ መንገዱን “ኢትዮጵያ ዉስጥ እኮ ናይጀሪያዊ ከብት አርቢዎች መጥተዉ ሲኖሩ መንግሥት ምንም እርምጃ አልወሰደም” አለ፡፡
እኔ ደግሞ በልቤ ይቃዣል ወይስ ካርታ አያውቅም አልኩ፡፡ በእኔ ቤት መቼም እዉነት ሊሆን ይችላል ብዬ ማሰብም አልፈለግኩም፤ለማጣራትም አልሞከርኩ፡፡ ምክንያቴ ደግሞ በናይጀሪያና በኢትዮጵያ መካከል ቢያንስ ቻድና ሱዳን፤ሲበዛ ካሜሩን፣ቻድ፣ማዕከላዊ አፍሪካ ከዚያም ሱዳንን ማቋረጥ ያስፈልጋል፡፡ እንዴት ይህ እውነት ይሆናል ብዬ ልገምት? ለማንኛዉም እውነት ነዉ፡፡ ከወራት በኋላ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች 18ኛ ፎረም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ላይ ሲካሔድ እኔም ታዳሚ ነበርኩና በመድረኩ ላይ ስለ አልጣሽ ፓርክ አንድ ጥናት ቀርቦ ስለነበር በዚያ ምክንያት ከእንደገና ሰማሁ፤አጣራሁ፡፡ መረጃዎቹንም ይዠ ትንሽ ኢንተርኔት ላይ ፍተሻ አደረግኩ፡፡ እነሆ!

ፈላታ ዘላን ከብት አርቢዎች በኢትዮጵያ
******************
የፈላታ ጎሳ ብሔረሰባቸዉ ፉላኒ ነዉ፡፡ የአሁኑ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት የሙሃመድ ቡሃሪ ብሔረሰብ፡፡ ወደ ቋራ ወረዳ፣አልጣሽ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያሉት በ1962 ዓ.ም. ገደማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ትንሽ ጊዜ ቆይተዉ ተመልሰዋል፡፡ የአልጣሽ ጥብቅ ደን በሱዳን በኩል ከመቶ ባላነሱ ታጣቂዎች ይጠበቅ ነበር እና ፈላታዎቹ ሊቆዩ አይችሉም፡፡ በደርግም ጊዜ እንዲሁ ብቅ ምልስ ይሉ ነበር አሉ፡፡ ከደርግ በተጨማሪም ፈላታዎቹ በሚመጡበት አካባቢ ኢሕአፓ ትንቀሳቀስ ስለነበር ከሕዝቡ ጋር ሆና ባዕዳኖቹን ታባርር ነበር፡፡

ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላ፣ በአካባቢዉ የፈላታ ማኅበረሰብ በነጻነት እንዲገቡም እንዲኖሩም ተፈቀደላቸዉ፡፡ ይባስ ብሎም በ1984 ዓ.ም. ከቋራ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተስማማተዉ እንዲኖሩ ተፈቀደላቸዉ፡፡ የቋራ ሕዝብ ተገድዶ እንደ ዐይኑ ብሌን በሚጠብቀው አልጣሽ ደን ዉስጥ በነጻነት መኖር ጀመሩ፡፡ ፈላታ ድንበር ዘለል ዘላን ከብት አርቢዎች ናቸዉ፡፡

በምዕራብ ጎንደር የሚግኘው የአልጣሽ ብሂራዊ ፓርክ

የፈላታዎቹ በዘመነ ኢሕአዴግ

ፈላታዎቹ ከቋራ ሕዝብ ጋር ድሙር በምትባል ቦታ ላይ በ1984 ስምምነት ሲያደርጉ ከብት ላይዘርፉ፣በደኑ ዉሥጥ የሚኖሩ ከብት ሲያገኙ የሚቀላቀሉ ጎሾች ስላሉ እንሱን እንዳይገድሉ ስምምነት አድርገዉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወያኔ ያጠገበቻቸዉ ፈላታዎቹ በ1986 ዓ.ም. ጎሾቹንም ገድለዉ ሕዝቡ እንዲያቸዉ አደረጉ፡፡ የቋራ ሕዝብ ምንም ዓይነት ጥበቃ እንዳያደርግ በወያኔ ተከልክሏል፡፡

ፈላታዎች ጋምቤላም አካባቢ አልፎ አልፎ ብቅ ይላሉ፡፡ ስለ ጋምቤላ የጸጥታ ሁኔታ የተሠሩ ጥናቶችን ላገላበጠ ይሔንኑ ይረዳል፡፡ ከቋራ ወረዳ በስተደቡብ (ቀድሞ የቋራ አካል የነበረዉ) አሁን “አዉጀሚስ” ተብሎ በሚጠራዉና በመተክል ዞን ሥር በሚገኘዉ ክልላዊ ፓርክ አጠገብም ይገኛሉ፡፡ እዚህ አካባቢ ላይ በርካታ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ ሰዎች ናቸዉ የሚኖሩት፡፡ ከትግራይ ባለሃብቶቹ ጎን ፈላታዎች ይኖራሉ፡፡

አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዉሥጥ ስለሚኖሩት ፈላታዎች ጉዳይ ልመለስ፡፡ አልጣሽ ፓርክ አጠቃላይ ስፋቱ የአዲስ አበባን አምስት እጥፍ እንደሚሆን እናስታውስ፡፡ የአዲስ አበባ ስፋት 527፤ የአልጣሽ ደግሞ 2665 ስኩየር ኪሎ ሜትር ነዉ፡፡

በአልጣሽ ትይዩ ሱዳን ዉሥጥም ፓርክ አለ-የድንደር ፓርክ፡፡ ፈላታዎቹ ድንደር ፓርክ መግባት አይፈቀድላቸዉም፡፡ ከብቶቻቸዉም አይገቡም፡፡ ከገቡም የገቡት ከብቶች ግማሾቹን በቅጣት መልክ ለሱዳን ይሰጣሉ፤ወይም ይወረሳሉ፡፡

በድንደር በኩል ወደ አልጣሽ መምጣት አይችሉም፡፡ ሱዳኖቹ የራሳቸዉን ፓርክ ስለሚጠብቁ ፈላታዎች ከሱዳን ተነስተዉ ወደ አልጣሽ የሚገቡት ከድንደር በሰሜን አልያም በደቡብ በኩል አድርገዉ ነዉ፡፡ ከድንደር በስተሰሜን በኩል ወደ አልጣሽ የሚገቡት በ”መብትገበያ” ነዉ፡፡ አባቶቻችን መብታቸዉን (ሕይወታቸዉን) ሽጠዉ አገር ስላቀኑ ስለጠበቁ ነዉ ያ ቦታ መብትገበያ መባሉ፡፡ ወያኔ ከገባች በኋላ ፈላታ እንዳሻዉ እንዲገባ ክፍት አደረገችዉ፡፡ ሁለተኛው፣ከድንደር በስተደቡብ አድረገዉ በኦሜድላ በኩል ወደ አልጣሽ ይገባሉ፡፡

አሁን ላይ 410 አካባቢ የሚሆን የፈላታ ቤተሰብ (Household) አልጣሽ ዉሥጥ በቋሚነት ከብት እያረቡ ይኖራሉ፡፡ ይህ 410 ቤተሰብ በስምንት “ገታ” (በእኛ አጠራር ቀበሌ ማለት ይቻላል) ሥር ይተዳደራሉ፡፡ በአማካይ በአንድ ቤተሰብ ዉስጥ አምስት ሰዉ ቢኖር በአጠቃላይ ወደ 2000 ገደማ ፈላታዎች አሉ ማለት ነዉ፡፡

የከብቶቻቸዉ ብዛት ከ800,000 (ስምንት መቶ ሺ) እስከ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ይደርሳል፡፡
የፈላታ ሕዝብ ኢትዮጵያ ዉስጥ እየኖሩ ግብር የሚከፍሉት ግን ለሱዳን መንግሥት ነዉ፡፡

የፈላታ ማኅበረሰብ እስከአፍንጫቸዉ ድረስ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ናቸዉ፡፡ የጦር መሳሪያም ይነግዳሉ፡፡ ስለ ሱዳን ድንበር አካባቢ የመሳሪያ ዝውውር የተሰሩ ጥናቶችም ለዚሁ አብነት ናቸዉ፡፡

ፈላታ የወያኔ (ሕወሃት) መረጃና መሳሪያ አቀባባይም ናቸዉ፡፡

ፈላታዎች ከቤኒሻንጉል/ጉሙዝ በቋራ እስከ መተማ፣ከመተማ እስከ ጎንደር የሚዘልቅ የወንበዴም የሌባም የኮንትሮ ባንድ ነጋዴም ሰንሰለት እንዳላቸዉ ይነገራል፡፡

ፈላታዎች በጋ በሚሆንበት ጊዜ እንኳን በአልጣሽ ደን ዉሥጥ በስፋት የሚገኘዉን ዓመቱን ሙሉ አረንጓ የሚሆነዉን ላሎ የተባለ ዛፍ በመጨፍጨፍ ይህንን የከብት መንጋቸዉን ይመግባሉ፡፡

አሁን ላይ በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዉስጥ “አቡኒን” በሚባለዉ አካባቢ እየኖሩ ነዉ፡፡
አልጣሽ በፌደራል መንግሥት ሥር ነዉ የሚተዳደረዉ፡፡ አዲስ አበባን አምስት እጥፍ የሚሆን ፓርክ ሃምሳ በማይሞሉ

ጥበቃዎች እንዲጠብቁት ነዉ የታሰበዉ፡፡ ከክልሉ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል-የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት ላይ ሲቋቋም፡፡ ቋረኛዉ ወገኔ አንጀቱ እያረረ ባእዳን ሲወሩት የፌደራል ሁኗል እየተባለ መሬቱን ለናይጀሪያዉያን አስረክቧል፡፡

ወያኔ ፓርኩን ወደ ፌደራል አዞረች፡፡ በዉሥጡም ናይጀሪያኖች እንዲኖሩ ፈቀደች፡፡ ከቋራ የቆረጠችውን የደቡቡን ክፍል የራሷን ሰዉ በባለሃብት ስም አሰፈረች፡፡

እንግዲህ ወያኔ ቢመቻት እኮ የፈላታ ሕዝብ የማንነት ይታወቅልኝ፣የልዩ ወረዳ (ዞን) ጥያቄ እቅርቧል ይሰጠዉ ማለቷ አይቀርም ነበር፡፡

የፌደራል መንግሥት እነዚህን የፈላታ ማኅበረሰብ ከዚህ ፓርክ ዉስጥ በስቸኳይ ማስወጣት ይጠበቅበታል፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን ከፈለጉ ከፓርኩ ወጥተዉ ከሌላዉ ሕዝብ ጋር ተቀላቅለዉ እንዲኖሩ ማድረግ ካልሆነ ደግሞ ግብር ወደሚከፍሉበት ወደ ሱዳን እንዲመለሱ ማድረግ ነዉ፡፡ ካልሆነ ደግሞ ለሙሃመድ ቡሃሪ በመንገር ወደ ናይጀሪያ ይውሰዳቸዉ፡፡

ስለ አልጣሽ ፓርክ በቅርቡ እመለስበታለሁ፡፡

(መረጃ ምንጮቼን በስምምነት ነዉ ስማቸዉን ያልገለጽኩት፤ምስጋናዬ ግን ወደር የለዉም!)

በምዕራብ ጎንደር የሚግኘው የአልጣሽ ብሂራዊ ፓርክ

*****************
Wubishet Mulat

ፈላታዎች የስለላና የመረጃ ሥራ እንደሚሠሩ ከታች የተያያዘው ደብዳቤ አንዱ ማስረጃ ነው። የቋራ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ፣ ኢንስፔክተር ከፍያለው ጀንበር፣ የካቲት 1 ቀን 2005 ላይ አቶ አደም ኢስማኤል የተባለው ፍላታ የጸጥታ ተልእኮ ስለተሰጠው የንግድ እቃ ሳይይዝ እንዲገባና እንዲወጣ እንደተፈቀደለት አሳውቋል። ፈላታው መጀመሪያ ላይ ከየካቲት 2 እስከ 12 ድስረ ቢሆንም የይለፍ የተጻፈለት ድጋሜ ወሩን በመቀየር ነሐሴ አድርጎታል። ለሁለተኛ ጊዜ የተጠቀመበት መሆኑን ያመለክታል።

በቀጥታ ደብዳቤው ፈላታው የጸጥታ ተልእኮ እንደተሰጠው ይገልጻል። ይሁን እንጂ ኢንስፔክተሩ ጋር በግል ግንኙነት በመፍጠር የሌለውን ሥልጣን ተጠቅሞ የይለፍ ሊጽፍለት እንደሚችል መጠርጠርም ይቻላል። ያው ፈላታዎቹ ከፍተኛ ሃብት ስላላቸው ከቋራ በመተማ እስከ ጎንደር የሚዘልቅ ኔትወርክም እንደነበራቸው በአካባቢው ከሚሠሩ የጸጥታ ሰዎች ሰምቻለሁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኔትወርክ መስመሩ ከቋራ በመተማ ቀጥታ ባህርዳር ላይ ሆኗል አሉ። ይሄ ገንዘብን (ሙስናን) መሠረት ያደረገው ሽፋናቸው ነው። ይህን ዓይነቱን ኔትወርክ መበጣጠስ ይዋል ይደር የማይባል ነው።

በሌላ በኩል ኢንስፔክተሩ የቪዛ ዉጤት ያለው የይለፍ ደብዳቤ በስሙና ማህተም አድርጎ ለፈላታው የሚሰጥ፣ ወረቀቱን ያየ ፖሊስም ይህን ዓይኑን ያፈጠጠ የሙስና ተግባር ሕጋዊ እንደሆነ በመቁጠር ማንም ምንም አይለኝም የሚል ተላላ ቢጤ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። ስለሆነም ኢንስፔክተሩ በተደራቢነት የደኅነነት መዋቅሩ ውስጥ የነበረ እና በእዚያ ሥልጣኑ የጻፈው ነው ቢባል ለማመን ይቀርባል። በየፖሊስ ጣቢያው ለፌደራል ደኅንነት መረጃ የሚሰጡ ድርብ ማንነትና ክፍያ ያላቸው ፖሊሶች እንደነበሩ በቅርቡ ሰምቻለሁ።

———————-

የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ – (ምዕራብ ጎንደር ዞን – ቋራ)

By Getu Temesgen

March 6, 2018 1276

ከአዲስ አበባ 1025 ኪ.ሜትር እንዲሁም ከጎንደር 310 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ይገኛል፡፡ ከሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጥሎ ለአማራ ክልል ሁለተኛው ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡

ፓርኩ የተከለለው የካቲት 13 ቀን 1998 ዓ/ም ሲሆን የፓርኩ መከለል ከሰሃራ አካባቢ ተነስቶ በጎረቤት ሀገር ሱዳን በኩል ወደ ሀገራችን ሊዛመት የሚችለውን በረሃማነት በመግታት ጤናማ ስርዓተ-ምሕዳር እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡

በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙት የዱር እንስሳትና እፅዋት በአካባቢው ሕብረተሰብ ቀጥተኛ ተሳትፎ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያገኙና ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ እንዲሁም አካባቢው የቱሪስት መስህብ ሆኖ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ታስቦ ነበር፡፡

የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በምዕራብ በኩል በሱዳን (ዲንደር_ፓርክ)፣ በምስራቅና በሰሜን በኩል በወረዳው 7 ቀበሌዎች እንዲሁም በደቡብ በኩል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (አይማ_ወንዝ) ይዋሰናል፡፡

የቆዳ ስፋቱ 266570 ሄክታር (2666 ስኩየር ኪ.ሜትር) ነው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ 800 ሚ.ሜትር ሲሆን የሙቀት መጠኑ ደግሞ እስከ 46 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡

በምዕራብ ጎንደር የሚግኘው የአልጣሽ ብሂራዊ ፓርክ

ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ በአማካይ በ700 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን አልፎ አልፎ ከሚታዩት የበርሚል፣ አምራኩባ፣ ሙሉጌታ፣ ዲናር፣ አያልነሽ (ኢሐፓ_ታጋይ የነበረችው አያልነሽ_ስሜነህ)፣ ኒጂላ፣ አምጥሽ፣ አልቢድ፣ አብዲዋን እና አምዶክ ተራሮች በስተቀር የመሬት አቀማመጡ በአብዛኛው ሜዳማ ነው፡፡

በፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የብዝሐ-ሕይወት ሃብት በተመለከተ 32 ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት (ዝሆን፣ አንበሳ፣ ጎሽ፣ ነብር፣ አነር፣ አቦ ሸማኔ፣ ፌቆ፣ አጋዘን፣ ውድንቢ፣ ድኩላ፣ አምባራይሌ፣ ከርከሮ፣ ጥርኝ፣ ..ወዘተ)

180 የአዕዋፍት ዝርያዎች (የመስቀል_ወፍ፣ ጅግራ፣ ቆቅ፣ ዋኔ፣ ሰጎን፣ የግብጽ ዝይ፣ ድንቢጥ፣ ግንደ ቆርቁር፣ ጉጉት፣ መጎጥ…ወዘተ)

8 ተሳቢ እንስሳት (ዘንዶ፣ አርጃኖ ….ወዘተ)፤ 16 የዓይጥ ዝርያዎች፤ 57 ትላልቅ የዛፍ ዝርያዎች (የእጣን ዛፍ፣ እንኮይ፣ ዞቢ፣ ባምባ፣ ዘንባባ፣ ዋርካ፣ ሾላ፣ ችብሃ፣ ግማርዳ፣ ኩመር፣ ጋባ፣ ዶቅማ፣ ለንቋጣ፣ ግመሮ፣ ክርክራ፣ ሰርኪን፣ ሱማያ፣ ብርብራ፣ …ወዘተ)

14 የተለያዩ የቁጥቋጦ ዝርያዎች፣ 10 ዓይነት የሳር ዝርያዎች እንዲሁም 16 ዓይነት የዓሳ ዝርያዎች (ቆረሶ፣ አንባዛ፣ በርሙጥ፣ ጥርሶ፣ ሃይላ፣ ጓንጃ፣ ለምለም ኩሬ፣ ሶርዝ፣ ተጋሎ፣ አይጦ፣ ሰፌዶ፣ ደረቅ ኩሬ፣ ጎሽ ምላስ፣ ዶለሴ፣ አደዝዝ እና አባቡቴ) ይገኙበታል፡፡

በነገራችን ላይ በፓርኩ ውስጥ አላጥሽ የሚባል ወንዝ የሚገኝ በመሆኑ የፓርኩም ስያሜ መጀመሪያ ላይ አላጥሽ ነበር፡፡ ‹‹አላጥሽ›› የሚለው ቃል አረበኛ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ በሆነ ቋንቋ መሰየም አለበት በሚል በቅርቡ አልጣሽ ተብሎ ተሰይሟል፡፡

የስያሜ ለውጡ አማርኛ ቃል ፍለጋ ይሁን እንጂ እግረ መንገዱን አጼ_ቴዎድሮስ ከመምህር እንግዳወርቅ ልጅ ከወ/ሮ ዛላ የወለዷትንና የአፄ_ምኒሊክ ሚስት የነበረችውን ልጃቸውን ወ/ሮ አልጣሽ_ቴዎድሮስን ለማስታወስ በር ከፍቷል፡፡

ምንጭ፡- Chalachew SimenehFacebookTwitterGoogle+