የአማራን ልኂቃን ከቶ ምን እናድርገው ይሆን ወገኖቸ??? አምርሬ ልርገመው ይሆን ከቶ??? እንኳንስ ተረግሞ እንዲሁም አላማረበት!!!

ፈጽሞ አልነቃ አለኮ!!! ታዲያ ምን እናድርገው??? መድረኩን ቅጥረኞች፣ ባንዶችና ሆድ አምላኪዎች እንደፈለጉ እንዲፈነጩበት ትቶ በዕጣፈንታው ላይ እየተቋመሩ በዓይኑ በብረቱ እያየ፣ በገዛ ጆሮው እየሰማ ጨርሶ የማይበርደውና የማይሞቀው ሆኖ ዳር ቆሞ ሲመለከት ወይም በሌላ አነጋገር እንደፈለጉ እንዲያደርጉት ሲፈቅድ ስታዩት ምን ትሉታላቹህ ታዲያ???

ስለራሱ፣ ስለሀገሩ፣ ስለዕጣፋንታው ሊከፍለው ግድ የሚለውን ዋጋ እየከፈለ በሙሉ የያገባኛል ስሜት መሳተፍ ሲኖርበት መድረኩን ሌሎች ያውም ጠላቶቹ በብቸኝነት እንደፈለጉ እንዲፈነጩበት ትቶላቸው ሲያበቃ እነኝህ ጠላቶቹ ሥልጣንን ይዘው፣ ኃይል አደራጅተው አረመኔያዊ ጥቃት እየፈጸሙበት መከራና ሰቆቃ ቢያጸኑበት፣ ከምድረ ገጽም ዘሩን ፈጽሞ ሊያጠፉት ቢጥሩ በእነሱ ይፈረዳል ወይ??? እሱስ እንዲህ አረጉኝ እያለ ሊያላዝን ይገባል ወይ???

እንዲያው ከዚህ በላይ ምን ቢሉትና ምንስ ቢደርስበት ነው ግን የአማራ ልኂቃን ሊነቃና ሆ ብሎ በሙሉ የያገባኛል ስሜት ተነሥቶ ለአማራ ሕዝብ ህልውና፣ ለመብቱ፣ ለነጻነቱ፣ ለጥቅሙ ሊቆም ሊታገል የሚችለው በሞቴ??? በላዩ ላይ ምን እየተሠራበት እንደሆነ ጨርሶ ሊገነዘብ እኮ አልቻለም!!!

ቅጥረኛው ብአዴን አማራን ያለ አማራጭ መጭው ምርጫ ላይ የማድረስና አጋጣሚውን ሳይጠቀምበት የማስመለጥ ከወያኔ የተሰጠውን የቤት ሥራውን በሚገባ እየተወጣ ነው ያለው!!! የአማራ ልኂቃን ግን እስከአሁን ይሄንን እላዩ ላይ እየተሠራበት ያለውን ቁማር አልተረዳም!!!

ብነግረው ብነግረው፣ ብወቅረው ብወቅረው፣ ብወግረው ብወግረው ፈጽሞ ሊገባው፣ ሊደነግጥ፣ ሊነቃ፣ ሊቀሰቀስ አልቻለም፡፡ ወይም ደግሞ ገብቶት ነገር ግን እያንዳንዱ በግለኝነት ገመድ ስለታነቀ የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጎ ለህልውናው ዘብ መቆም አልፈለገም፡፡ ቆይ ግን ግለኝነቱ ታዲያ ከጠላቱ ጥቃት ይታደገዋል ወይ??? ያሳለፈው የ27 ዓመት የግፍ የሰቆቃ ዘመን ግለኝነትና እራስን ማግለል እንደማያድን በቂ መማሪያ አይደለም ወይ??? 27ቱ ዓመት የግፍ የሰቆቃ የፍዳ ዘመን አማራ በጋራ ወይም ተደራጅቶ ካልቆመና የሚፈጸምበትን ጥቃት በጋራ ቆሞ ወይም ተደራጅቶ ካልመከተ ካልታገለ በስተቀር ከምድረገጽ መጥፋቱ እንደሆነ አስተማሪነቱ ከበቂ በላይ አይደለም ወይ???

ምን ይሻላል ትላላቹህ ከቶ??? ወይ እንዲያው ይሄንን አማራ የሚባል ዘር በደቂቃ ምጥጥ አድርጎ የሚፈጀው ነገር በመጣና ፈጅቶት በተገላገላገለ እንዴት ጥሩ በነበር!!! እኔም እንደእናንተው አንድ ነፍስ እንጅ ሽህ ነፍስ የያዝኩ ይመስላቹሃል እንዴ??? አንድ ሞት እንጅ ሽህ ሞት ይጠብቀኛል እንዴ እኔስ አማራ እንዲህ ተፈጸመበት፣ እንዲህ ተሸረበለት፣ እንዲህ ታቀደለትእያልኩ ተጨንቄ የምሞተው??? ምን ይሻለኛል ይሆን ከቶ??? ተቃጥየ፣ በግኘ፣ አርሬ፣ ነድጀ ከምሞት አሁኑኑ እራሴን አጥፍቸ ልገላገል ይሆን ከቶ???

የአማራ ልኂቃን አጋጣሚውን ተጠቅሞ ፈጥኖ በመደራጀት ለራሱ ዘብ እንደመቆም ባለመደራጀቱና እራሱን በማግለሉ መከራውና ሰቆቃው ይቀርለት ይመስል ገና ለገና ችግር ይገጥመኛል ብሎ በመፍራት ሳይደራጅ በመቅረቱ ሕዝባችን ያለ አማራጭ ቀርቶ መጭውን ምርጫ ሊያስመልጡት ነው ልብ በሉ!!! መጭውን ምርጫ አማራ አማራጭ አጥቶ አጋጣሚውን ሳይጠቀምበት አመለጠው ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ይገባናል ለመሆኑ???

እነኝህ አደራ በላ የአማራ ልኂቃን አጋጣሚውን ተጠቅመው ባይደራጁም እንደምታውቁት የአማራ ሕዝብ ለመጭው ምርጫ አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሁለት አማራጭ ድርጅቶች ነበሩት፡፡ እነሱም አዴኃን እና የአርበኞች ግንባር ነበሩ፡፡

ምን ዋጋ አለው በመጭው ምርጫ ላይ አማራ አማራጭ እንዳይኖረው አድርጎ ምርጫውን ሳይጠቀምበት የማሳለፍ የማስመለጥ ተልእኮ ተሰጥቶት ይሄንን ተልእኮ በሚገባ እየተወጣ ያለው ቀንደኛው የአማራ ጠላት ብአዴን የአዴኃንን አባላት በገንዘብ የሚደለሉትን በገንዘብ ደልሎ በገንዘብ ሊደልላቸው የማይችላቸውን አስፈራርቶ ከራሱ ጋር እንዲዋሐዱ በማድረግ ተዋሕደናል!” የሚል ዜና አስነገረና እንዲከስሙ አደረጋቸው፡፡ ይሄንን አንድ በሉልኝ፡፡

የአርበኞች ግንባርንም ኃላፊዎችን በገንዘብ ደልሎ የአርበኞች ግንባር የትግል ዓላማ የነበረው የወያኔ ሥርዓት ተገርስሶ በነጻና ፍትሐዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት መመሥረት የሚችልበት ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ መታገል በሚል ስለነበረ በረሃ ወርደን ስንታገል የቆየነው ይሄም ስለተፈጸመ ከዚህ በኋላ የምንታገልበት ምክንያት ስለሌለን ትግላችንን ቋጭተን ሠራዊታችንንም በትነናል!” የሚል እጅግ አስቂኝ፣ ካለው ሁኔታ ጋር ጨርሶ የማይጣጣምና ነባራዊውን ሐቅ የማያንጸባርቅ መግለጫ እንዲሰጡ አድርጎ እንዲበተኑ በማድረግ አከሰማቸው፡፡ ሁለት በሉልኝ፡፡

በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ብአዴን በአማራ ሕዝብ ዘንድ እንደመርገም ጨርቅ እንደሚጠላ ስለሚያውቅ ከአማራ ሕዝብ ጋር የሚያቀራርበውን ስትራቴጂ (ስልት) ነደፈና በካድሬዎቹ (በወስዋሾቹ) አብን እንዲመሠረት አደረገ፡፡

አብንን ለመመሥረት ሲያስብ ተቀባይነት እንዲያገኙና እንዳይጠረጠሩ ለማድረግ መሥራች የተባሉትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ተሰብስበው በመገኘታቸው!” በሚል ምክንያት ለጥቂት ቀናት እንዲታሠሩ አደረገና በበቂ ሁኔታ ወሬው ተራግቦ ዕውቅና ካገኙለት በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው ተፈቱ፡፡ እስሩ የውሸትና ዕውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ ነበረና ተከሰው እንዲፈረድባቸው አልተደረገም፡፡

ከዚያም አብን ከብአዴን በግልጽ የሚታዩ በርካታ እገዛዎች እየተደረገለት በብአዴኑ የሙሉዓለም አዳራሽ በካድሬዎቹ ተመሠረተ፡፡ የዋሁ ወገናችን ግን ይሄንን ሁሉ እያየ ሊነቃ አልቻለም፡፡ ባለመቻሉም አብን በየስፍራው ስብሰባ ሲጠራ አዳራሽ ሞልቶ እየተረፈ ተሰበሰበለት፡፡

ብአዴን አብንን የመሠረተው አብን የሕዝብ ድጋፍ ካገኘ በኋላ ተዋሐድን!” ብሎ ከአማራ ሕዝብ ጋር ለመቀራረብ፣ በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተመራጭ ለመሆን ወይም ለመደገፍ ብቻ አይደለም፡፡ የአማራ ልኂቃን ትክክለኛ የአማራ ሕዝብን ድርጅት እንዳይመሠርቱ መንገዱን ለመያዝም ነው፡፡ ዋናው ዓላማ እንዲያውም ይሄኛው ነው፡፡

በዚህም መሠረት አብኖች ኮርኳሪ ኃይለቃሎችን እየተናገሩ የአማራን ልብ ቆስቁሰው ቆስቁሰው ድጋፉን ካገኙ በኋላ ባለፈው ሳምንት በዜና እንደሰማቹህት በጸጥታና ደኅንነት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከብአዴን ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል!” ብለው አውጀዋል፡፡

ስምምነታቸው በስድስት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት!” ቢባልም ክርስቲያን ወይም መንግሥቱ ታደለ የተባለው የቀድሞ የብአዴን ካድሬ (ወስዋሽ) የአሁን የአብን አመራር በፓርቲው (በቡድኑ) የፌስቡክ አካውንት (በመጽሐፈገጽ መዝገብ) ላይ የገለጸው ግን ውሕደት የተፈጸመ አስመስሎ ነው ከብአዴን ጋር አንድ ካልሆንን ከማን ጋር አንድ ልንሆን ነው ታዲያ?” ሲል በመናገር ነበር ስለስምምነቱ የገለጸው፡፡

አብንን ለመመሥረት እስከተመለመለበት ጊዜ ድረስ አማራ የሚባል ብሔረሰብ የለም!” ይል የነበረው ሌላኛው የአብን አመራር ጋሻው መርሻ የተባለውም በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከብአዴን ጋር ስላደረጉት ስምምነት ተጠይቆ ሲመልስ የሞሮሞ ድርጅቶች እየተዋሐዱ በአንድ ቆመዋል፣ የትግራይ ድርጅቶችም እንዲሁ እየተዋሐዱ በአንድ ቆመዋል፡፡ ለአማራ ሕዝብ እታገላለሁ የሚል ማንኛውም ድርጅት ሁሉም ተዋሕደው በአንድ መቆም ይጠበቅባቸዋል!” ሲል ነበር የመለሰው፡፡

ከሁለቱ አነጋገር የምትረዱት ነገር ቢኖር አብንና ብአዴን አንድ መሆናቸውን ወይም ደግሞ የተዋሐዱ መሆናቸውን ነው፡፡ ተዋሕደናል!” ብለው እንዳያውጁ ለብዙው አማራ የማይጠበቅና የማይታሰብም በመሆኑ ነው እንዲያ ብለው ከማወጃቸው በፊት ጆሮን ለማላመድ ወይም ለማለሳለስ ተብሎ “…በጋራ ለመሥራት ተስማማን!” ሲሉ የተናገሩት፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያቹህ! የአማራ ሕዝብ ካሉት ጠላቶች ቀንደኛውና የአማራ ሕዝብም አምርሮ የሚታገለውም ብአዴን ነው፡፡ ለአማራ ሕዝብ በጠላትነት የብአዴንን የሚያክል ጠላት የለም!!! ብአዴን ማለት ወያኔ የዘር ማጥፋት ጥቃትን ጨምሮ በአማራ ሕዝብ ላይ መፈጸም የሚፈልገውን አረመኔያዊ ግፍ ሁሉ መፈጸም እንዲችል ያደረገ የጠላት ጠላት ድርጅት ነው!!! ብአዴን ባይኖር ኖሮ ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን የፈጸመውን ግፍ ፍዳና ሰቆቃ አንዷን እንኳ መፈጸም ባልቻለ ዕድሉንም ጨርሶ ባላገኘ ነበር፡፡ ቅጥረኛ ካልሆነ በስተቀር ይሄንን እውነት የማያውቅ አማራ የለም!!! ብአዴን ከዚህ ቀደም የፈጸመብንና ያስፈጸመብን ግፍ አልበቃውም፡፡ አሁንም ተለውጫለሁ!” እያለ የአማራን ሕዝብ ለማጃጃል በሚጥርበት ወቅትም ቢሆን ወያኔ በሥነሥርዓት ማኒፌስቶ (አቋመ አቅድ) ቀርጾ በዓላማ የፈጸመብንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመካድ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት አልተፈጸመም!” በማለት ጌታውን ወያኔን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት ሌት ተቀን እየጣረ ያለ ነቀርሳ ድርጅት ነው ብአዴን ማለት፡፡

ከዚህ ድርጅት ጋር ነው እንግዲህ አማራን ከጠላት ለመጠበቅ፣ ለአማራ ሕዝብ መብት፣ ነጻነት፣ ጥቅምና ህልውና መረጋገጥ እንታገላለን፣ ለተፈጸመበትም ተቆጥሮ የማያልቅ አረመኔያዊ ግፍ ፍትሕ እንዲያገኝ እናደርጋለን!” እያሉ ብአዴን ለዚህ በአማራ ሕዝብ ለፈጸመው ተነግሮ የማያልቅ ግፍ ይቅርታ ሳይጠይቅ ጭራሽም በማንነቱ የተፈጸሙበትን አረመኔያዊ ግፎች ሸምጥጦ እየካደ ባለበትና ፈጽሞ ባልተጸጸተበት እንዲሁም የቅጥረኝነት ሥራውን አሁንም በቀጠለበት ሁኔታ ከዚህ ቀንደኛ ጠላት ድርጅት ጋር ውሕደት እየፈጸሙና ሌሎቻቹህም ተዋሐዱ!” እያሉ የሚገኙት፡፡ እኮ ለምን??? አማራን ጨርሶ ለመቅበር ወይስ ለማዳን??? አማራን እንዳያንሠራራ አድርጎ ለመስበር ወይስ ለመጠገን??? ለመጣል ወይስ ለማንሣት???

ከመቸ ወዲህ በማን ሀገርስ ነው ክፉ ደመኛ ጠላት መከታና አዳኝ የሚሆነው??? አብን ቀድሞውንም ቢሆን ከላይ ለገለጽኩላቹህ ዓላማ በብአዴን የተመሠረተ ስለሆነ ነው እንጅ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ ነው የምነግራቹህ የአማራ ሕዝብ ሰቆቃ ግፍና ፍዳ የወለዳቸው ቢሆኑ ኖሮ ብአዴንን ለአማራ ሕዝብ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብት፣ ጥቅም ሲጋደልና ሲታገል የኖረ ይመስል ያን ሁሉ ግፍ ፍዳ ሰቆቃና እልቂት እንደዘበት እንደ ቀላል ነገር እረስተውት ከብአዴን ጋር ያልተዋሐድን ከማን ጋር ልንዋሐድ ነው ታዲያ?” ሲሉ አያላግጡብንም ነበር፡፡

አብኖች እንዲህ እንዳያቹሃቸው መርሕ አልባ የሆኑት ወይም የመርሕ ሰዎች ያልሆኑት የብአዴን/ወያኔ ቅጥረኞች ስለሆኑ ነው ሌላ አይደለም፡፡ ብአዴንን ከነ ኩነኔው፣ ከነ ግፉ፣ ከነ ክህደቱ የተቀበለ አካል ወያኔን ከነኩነኔው ከነ ግፉ ላለመቀበል ሊጠቅሰው የሚችለው ምንም ምክንያት የለውም!!! ወያኔን የአማራ ጠላት ያደረገው የደነቆረ አስተሳሰቡ እንጅ ትግሬነቱ አይደለምና፡፡ የአማራ ሕዝብም ጨፍጫፊየ አማራ ከሆነ ቅጥረኛም ሆኖ ወይም በራሱ እንደፈለገ ይጨፍጭፈኝ! ጨፍጫፊየ ሌላ ዘር ሲሆን ብቻ ነው የሚከፋኝ!” ብሎ አያውቅምና፡፡ አይልምም!!!

እንዲያውም የአማራ ሕዝብ በባሕሉ ከጠላት ይልቅ አሾክሿኪን ወይም ቅጥረኛ ባንዳን አምርሮ የሚጠላ የሚጸየፍ ሕዝብ ነው፡፡ መርሕ አልባ ፖለቲካ የባንዳነት የቅጥረኝነት ተልእኮ እንጅ ተጋድሎ አይደለም!!! በተለይ አሁን ላይ የአብኖችን ማንነት ለመለየት የሚያዳግት ባይሆንም ካስፈለገ ግን አመክንዮውም እንዲህ ያጋልጣቸዋል፡፡ ከአመክንዮ ጋር የሚቃረን የማይስማማ እውነት የለም!!!

እናም እንግዲህ ከላይ በገለጽኩላቹህ መሠረት ብአዴን እስከአሁን ባለው ጊዜ በተፈጠረው አጋጣሚ የአማራ ሕዝብ የሚወክለውንና ለህልውናው፣ ለመብቱ፣ ለነጻነቱ፣ ለጥቅሙ የቆመለትን ትክክለኛ ድርጅት እንዳያገኝ አድርጎ መጭው ምርጫ እንዲያመልጠውና ህልውናውን፣ መብቱን፣ ጥቅሙን፣ ነጻነቱን ሳያስጠብቅ እየማቀቀ፣ ፍዳውን እየቆጠረ፣ በግልጽና በስውር የሚፈጸምበት የዘር ማጥፋት ጥቃት እየተፈጸመበት መኖሩን እንዲቀጥል የማድረጉን ተልእኮ በሚገባ ተወጥቷል፡፡

ፀረ አማራ አቋማቸውን በተለያዩ አስተሳሰቦቻቸውና ከአማራ ጠላቶች ጎን በመሰለፍ በተደጋጋሚ ያረጋገጠው፣ በአማራ ደም ወይም መሥዋዕትነት ደቡቦችን ባለተራ ገዥ ለማድረግ የሚታገለው የአንድነት ኃይል የሚባለው በግ7 የሚመራው የውሸት የአንድነት ኃይልም ዕድሉን ቢያገኝ ለአማራ ሕዝብ ከወያኔ አገዛዝ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ሳይታለም የተፈታ ነውና ይህ የአንድነት ኃይል ተብየም ለአማራ ሕዝብ አማራጭ ሊሆን አይችልም!!! መኢአድና አንድነት የሚባሉትም ለወያኔ ቅጥረኞች ከተሰጡ ቆዩ፡፡

እንግዲህ በቀሪው ጊዜም ቢሆን የአማራ ልኂቃን በአማራ ሕዝብ ላይ እየተሠራ ያለው ቁማር ገብቶት ፈተናዎችን ተጋፍጦ በመውጣት ትክክለኛ የአማራን ሕዝብ ድርጅት በማቋቋም ለምርጫ በመቅረብና ለአማራ ህልውና፣ መብት፣ ነጻነትና ጥቅም የመታገል የትውልድ አደራ ኃላፊነቱንና ግዴታውን ይወጣል!” የሚለው ተስፋ በእጅጉ የመነመነ በመሆኑ አማራን የሚወክለውን የራሱን ድርጅት እንዳያገኝና አማራጭ አሳጥቶ መጭውን ምርጫ ሳይጠቀምበት እንዲያልፈው የማድረጉ የወያኔ ዓላማ የተሳካ ለመሆኑ ከወዲሁ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ይሄ ታዲያ ለአማራ ሕዝብ በቁም መቀበር አይደለም ወይ ወገኖቸ??? ኧረ ተው ኧረ ተው ኧረ ተው ወገኔ ተው ለራስህ ብትል ቁረጥ ተው???

የአማራ ልኂቃን በማንነቱ መደራጀት የማይፈልግበት ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር የሚቆራረጥ የሚለያይ እየመሰለው ነው፡፡ ይሄ ግን ፈጽሞ የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ በዚህች ሀገር ላይ እንደሠለጠነው ዓለም ሁሉ ኋላ ቀሩና በተፈጥሮው ፀረ ዲሞክራሲ እንዲሁም ፀረ ሰብአዊ መብት የሆነው የጎሳ ፖለቲካ ክልክል መሆኑ እስካልተደነገገና ፖለቲካችን እንደሠለጠነው ዓለም ሐሳብ ላይ ብቻ እንዲያጠነጥን እስካልተደረገ ጊዜ ድረስ በጎሳ ፖለቲካ ጦስ ይህችን ሀገር ካንዣበበባት ጥፋት ማዳኛ ብቸኛው መንገድ የአማራ ብሔርተኝነትና መደራጀት ብቻ ነው!!!

ከዚህም ሌላ አማራ በማንነቱ መደራጀት ግድ የሚልበት ምክንያት የአማራን ዘር ከዚህች ሀገር የማጥፋት አጋንንታዊ ዓላማ ያላቸው የጥፋት ኃይሎች በመኖራቸውና በዚህ ዓላማቸው መሠረትም አማራን እያጠፉት በመሆናቸው ተደራጅቶ የሚፈጸምበት ጥቃት በመቀልበስ ህልውናውን መታደግ ስላለበት ነው!!!

እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ የአማራ ልኂቃን በዚህ ምክንያት ነው በማንነቱ መደራጀት ያልፈለገው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱን የአንድነት ኃይል በሚባለውስ ቢሆን የአማራ ልኂቃን መሳተፍ የሚጠበቅበትን ያህል ነው ወይ እየተሳተፈ ያለው?” ብለን የጠየቅን እንደሆን መልሱ አይደለም የሚለው ነው፡፡ ያልሆነበት ምክንያት ደግሞ ሐሰተኛው ወያኔ እና ሌሎችም የጥፋት ኃይሎች አማራን ነፍጠኛ፣ ጨቋኝ፣ ፊውዳል ምንንትስ እያሉ በፈጠሩት የማሸማቀቂያና የማግለያ ዘዴ ሰለባ ስለሆነ ፖለቲካን እርም ብሎ በመሸሹ ነው፡፡

የአማራ ልኂቃን ለዚህ ጠላት ለፈጠረው ሐሰተኛና ፈጠራ የተሞላበት የማሸማቀቂያ የማግለያ ዘዴ ጆሮ ሰጥቶ እራሱን ከፖለቲካ (ከእምነተ አሥተዳደር) ማግለሉ በእውነት አሳፋሪና ውርደትም ነው፡፡ ውጤቱም ሀገሩን አስነጠቀው፣ ሁለነገሩን አሳጣው፣ ለማመን በማይቻል ማጥ ውስጥ ጣለው፣ በሕግ ሳይደነገግ በሀገር ጉዳይ ላይ የማያገባው የማኅበረሰብ ክፍል ተደርጎ እንዲቆጠር አደረገው፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር የአማራ ልኂቃን ይሄንን ሁሉ ነገር ሆኖም በቃኝ አለማለቱ ነው!!!

ከዚህ በኋላ ግን መጃጃሉ፣ የማንም ምናምንቴ ውሪ መጫወቻና መቀለጃ መሆኑ ይብቃ!!! አማራ ሆይ ንቃ!!! ቁረጥ!!! ጨክን!!! መጠን የለሽ ትዕግሥትህ፣ መቻልህና ማሳለፍህ ለምን እንደሆነ ጨርሶ ለማይገባቸው ደናቁርት አህዮች እንዲህ መሆንህ መቃብርህን መቆፈር ሆነብህ እንጅ ሕይዎት አልሆነልህምና፡፡ ከዚህም በኋላ በዚህ ልቀጥል ካልክ ግን ግብአተመሬትህን ለመፈጸም ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ለምንም እንደማይጠቅምህ ዕወቅ!!! ስለሆነም ይብቃህ!!! በቃ በልና ተነሥ!!! ተደራጅ!!! ፈጥነህ ተደራጅና ህልውናህን ሀገርህን ታደግ!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com