ከዚህ ቀደም እንደገለጽኩላቹህ ማንም ታሰረ!” ቢባል አይድነቃቹህ!!! እስሩ የእውነት አይደለም!!! ሊሠሩት የፈለጉትን ፖለቲካ ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ምርጫው በተከናወነ ማግሥት የተመሠረተባቸውን ክስ ውድቅ እያደረጉ ይፈቷቸዋል፡፡

ለዚህም እንዲመቻቸው የሚመሠረትባቸው ክስ ለማስተባበልና ውድቅ ለማድረግ በሚመች መልኩ ነው ተቀምሮ ክሱ እየተመሠረተባቸው ያለው!!!

ግልብ አትሁኑ!!! ሕዝቡ ሲሆን የቆየው ነገር ሁሉ የተቀመረ ባዶ ድራማ መሆኑን ትንሽ ትንሽ እየተረዳ ስለመጣ እንዳይነቃ፣ እንዳይባንን፣ እንደተጃጃለ እንዲቀጥል ለማድረግ ልክ ለልጅ አሻንጉሊት እንደሚሰጡት ለሕዝቡም እያነሣ የሚጥለው ወይም ቢዚ (ባተሌ) የሚያደርገውን አጀንዳ (ርእሰ ጉዳይ) መስጠታቸው ነው!!! ይሄ ሲያልፍበት ደሞ ሌላ ያመጣሉ፡፡

እንዲህ ዓይነት ነገሮችን እየሰጡ ለማሰብ ጊዜ ሳይሰጡህ እስከ ምርጫው ያደርሱሃል የይስሙላ ምርጫው ከተከናወነ በኋላም ለይስሙላ ያሰራቸውን የሰው ደም ጠጭና የሀገር የሕዝብ ካዝና አራቋች ሌባ ዘራፊ ባለሥልጣናቱን በሙሉ ይፈታና ወደነበረበት ቦታ ይመለሳል!!! አለቀ ቀመሩ ይሄው ነው!!!

አስተማማኝ ለውጥና ትክክለኛ ነጻነት ከፈለክ ለዚህ ዋስትናህ የወያኔ/ኢሕአዴግን ሥርዓት ገርስሰህ መቃብሩ ላይ መቆም ብቻ ነው!!! ለዚህ በርትተህ ሥራ፣ ቆርጠህ ጨክነህ ታገል!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com