ሰሞኑን ዐቢይ አውሮፓ ነው ያለው፡፡ ወያኔ በሚፈጽመው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰትና አንባገነንነቱ ምክንያት አውሮፓዎቹ ያቆሙትን ርዳታ፣ የቀጥተኛ የባጀት ድጋፍና ብድር እንደገና እንዲቀጥሉ ለማግባባት ነው የሔደው፡፡

እንግዲህ እነ በረከት ዛሬ የታሰሩትም ለዚህ ነው፡፡ ዐቢይ ለሚያደርገው ጅንጀና ለማሳመኛነት እንዲረዳው፡፡ ሐሳባቸውም የተሳካ ይመስላል፡፡ ወ/ሮ አና ጎሜዥ በቲዩተር ገጻቸው ላይ ስለዚህ በመጨረሻ ያ ወንጀለኛ በረከት ስምኦን የአንባገነኑ መለስ ዜናዊ የቀድሞ ጎብልስ ኢትዮጵያ ውስጥ ታሰረ!” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

አውሮፓዎቹ ለወያኔ የሚሰጡትን እርዳታ፣ ቀጥተኛ የባጀት ድጋፍና ብድር እንዲያቆሙ ለማድረግ በአውሮፓ ኅብረት በኩል የወ/ሮ አና ጎሜዥ ሚና ከፍተኛና የማይተካ ነበር፡፡ እንግዲህ ለወያኔ ማታለሉ ሆኖለታልና ያጣውን እርዳታ፣ ቀጥተኛ የባጀት ድጋፍና እርዳታ መልሶ ማግኘቱ የሚቀር አይመስለኝም!!!

ኧረ እባካቹህ ለአውሮፓና አሜሪካ ቅርብ የሆናቹህ ምሁራንና ፖለታከኞች እውነታውን በማስረዳት ትጉ??? ለነገሩ ምሁራኑና ፖለቲከኞቹ እራሳቸው የተጃጃሉ አይደሉ እንዴ!!! አየ ጉድ! ወይ ወያኔ! እንዲህ በሰው ላይ እንደተጫወትሽ እስከመቸ ትዘልቂ ይሆን???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com