January 23, 2019

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪ አቶ ዳዎድ ኢብሳ የድርጅታቸው ታጣቂዎች የያዙትን መሳሪያ እንደሚያስረከቡ ገለጹ። “ለኦሮሞ ህዝብና ለአባገዳዎች ትጥቃችንን እናስረክብለን” ሲሉ ነገር የገለጹት።

የኦነግ ሰራዊት ደቡብ ምእራብ ኦሮሞ ክልል ከፍተኛ ወታደራዊ ሽንፈት ያጋጠው ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ዜናዉ ቢያስተባብሉም፣ በርካታ ጫካ መካከል ያሉ የኦነግ ማስልጠኛ ካምፖች በአየር መደምሰሳቸውን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

በጉጂ ያለው የኦነግ ሰራዊት አዛዥ “አባ ገዳዎችን አለመስማት አይቻልም” በሚል ትጥቅ ለመፍታት መወሰኑን መዘገባቸው ይታወሳል። የአቶ ዳዎድ ምክትል ጃል አራርሳ ቢቂላ ” ጦራችን ህዝቡን ብሎ ፍራፍሬ እና የእንጨት ልጣጭ እየተመገበ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፏል። አሁን ዝለናል።ከዚህ በኃላ ጦርነት የሚባል ነገር አያስፈልግም።ከዚህ በኃላ ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላም ነው። ትብብር ነው። ጦሩ በሰላም ከህዝቡ ጋር እንዳይቀላቀል የሚያደርጉ ሃይሎችን ከዚህ በኃላ በዘመቻ መልክ ልንከላከላቸው ያስልፈጋል። እኛ ስልጣን ብለን አልመጣንም ።እኛ ምን መደረግ እራሱ እንዳለበን ገና ከህዝባችን ጋር በደንብ አልተነጋገርንም።እኛ የሚንፈልገው ወንበር አይደለም።እኛ የሚንፈልገው እሄ በህዝባችን መሰዋዓትነት የተገኘው ለውጥ እንዳይቀለበስ ነው።ይህ ለውጥ እንዲቀለበስ ብዙ ሃይሎች ይፈልጋሉ።ስለዚህ እኛ የሚንፈልገው ይህ ለውጥ እንዳይቀለበስ እና እውነተኛ ዲሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን ከመንግስት እና ከሌሎች ኃይሎች ጋር በሰላም እና በትብብር መስራት ነው።” ሲሉ ቀደም ሲል ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ አቶ ዳዎድ አማራጭ ስለሌላቸው እጅ እንደሚሰጡ በብዙዎች ይጠበቅ ነበር።

ኦነግ ከዉትድርና ሽንፈቱ በተጨማሪ፣ በሕዝብ ዘንድ ያለውም ድጋፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዳሽቆለቆለ የሚናገሩት ተንታኞች ፣ የለማ ቡድን በአንጻሩ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘ እንደሆነ ይናገራሉ። “የለማ ቲም፣ በኦነግ ላይ ወታደራዊ ድሎችን ቢያስመዘግብ ፣ ደርግና ወያኔዎች ያደርጉት እንደነበረ ከመፎከር ይልቅ፣ በጦርነት የተሸነፉት ኦነጎች የተሸናፊነት ስሜት እንዳያድርባቸው ለማድረግ፣ ከአባ ገዳዎⶭ ጋር በመስራት ሁኔታዎች ለማብረድ የተጠቀመባቸው ዘዴዎች ብዙዎችን አስደስቷል።

ሳተናው