January 23, 2019

በአቶ ሙስጠፋ ዑመር የሚመራው የሶማሌ ክልል መንግስት ካቢኔ 6 ከፍተኛ አመራሮችን አባረረ። ስድስቱ አመራሮች በቀድሞ የአብዲ ዒሌ አስተዳደር ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ሲሆኑ አቶ ሙስጥፋን ከስልጣን ለማስወገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸውን የሸገር ታይምስ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
ካቢኔው ከሰአታት በፊት ባጠናቀቀው አስቸኳይ ስብሰባ በስድስቱ አመራሮች ላይ ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ክልሉን ከአብዲ ኢሌ ስውር መዋቅር የማጽዳት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑም ታውቋል።
በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ከካቢኔ የተባረሩት
- አቶ ጉሌድ አዋሊ/ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ/
- አቶ አብዲ ሃኪ / የፕሬዝዳንቱ አማካሪ/
- አቶ ሀሰን አሊ / የልዩ ፖሊስ ኢንትርፕራይዝ ምክትል ኃላፊ/
- አቶ አብዲ ህኩም አሊ/ የቴክኒክና ሙያ ተቋም ኃላፊ/
- አቶ አብዲ ኢሌ አብዱላሂ/ የከተማ ስራ ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አብዲ ሙህመድ ኡስማን /የውኃ ልማት አማካሪ/
እንደሆኑ ሸገር ታይምስ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
Via Sheger Times
