January 25, 2019

አህመድ ሺዴ ላለፉት 15 ዓመታት በሥልጣን ላይ ባለበት ዘመን ለፈፀማቸው በተለይም ከአብዲ ኢሌ ጋር በመተባበር ክልሉን የመዘበረበት፣ በቅርቡ ደግሞ ከሄጎዎች ጋር በመሆን ለውጡን ለመቀልበስ ኢ-ህገ-መንግስታዊ ድርግቶቹን በማሰባሰብ ለፍርድ ለማቅረብ የክልሉ ዓቃቤ-ሕግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የውስጥ ምንጮች በተለይ ለረጆ ገልፀዋል፡፡
መረጃው እንደሚጠቁመው አህመድ ሺዴ የአብዲ ኢሌን ወንጆሎች በመደበቅ ካለሱ ሌላ ሰው ክልሉን ማስተዳደር እንደማይችል በመናገር እንድሁም የፌዴራል ባለሥልጣናትን በመደለል በክልሉ ላይ ብሎም በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ወንጀል ፈፅሟል፡፡ለዝህም እኩይ ሥራው ከቢልዮን ብር በላይ በኮንትራት መልኩና በገንዘብ እንደተሰጠው የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝቷል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ አህመድ ሺዴ በተገቢው መንገድ ለፍርድ ቀርቦ መብቱ ሳይጓደልበት እንድከራከርና ፍርድ ቤቱ ፍትሃዊ ውሳኔውን እንድያሳልፍ እንድያደርግ መረባረብ አለበት! የፋይናንስ ና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር በመሆኑ ብቻ የዶ/ር አብይን ገፅታ ያበላሻል ተብሎ ሊተው አይገባም! የሕግ-የበላይነት መከበሩን የሚናረጋግጠው እንደ አህመድ ሺዴ ያሉትን ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ ሲቻል ነው፡፡ ሰዎቹን እየለዩ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል አይገባም፡፡ ተደማሪ ነኝም የሚለው መሰሪ ሲያጠፋ ተይዞ መጠየቅ አለበት፡፡ ለዝህ ጥሩ ማስረጃ የሚሆነው በአንድ ወቅት ነብዩ መሀመድ (ሰዐወ) አንዲት ከተከበሩት ቁሬይሽ ጎሳ የሆነት ሴት ሰርቃ ሲትከሰስ ጎሳዎቿ ህጉ እንዲላላቸው ሲጠይቋቸው ግዜ፣ ነብዩ (ሰዐወ) እንድህ በማለት ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡- “ልጄ ፋጥማ ብትሰርቅ እጇን እቆርጣት ነበር” አሉ፡፡ ስለዝህ ዶ/ር አብይም የቅርብ ጓደኛቸው የሆነውን አህመድ ሺዴ አሳልፈው ለሕግ የበላይነት ይሰጡት ይሆን? ወይስ ይከላከሉለታል? በቅርብ የሚናየው ጉዳይ ይሆናል፡፡ መታወቅ ያለበት ጉዳይ አህመድ ሺዴ ከአሁን በኃላ ሶማሊ ክልል መጥቶ እንደበፊቱ ሊቦርቅበት አይችልም! የሶማሊ ሕዝብ ነቅቷል ወንጀሉንም አውቋል፡፡ ከአሁን በኃላ የሚያጃጅለው ሰው አይኖርም! ዶ/ር አብይ ይህ መፈተኛው ነው ፈረንጆቹ እንደሚሉት defining moment ነው!