January 26, 2019

በሕወሃት የሚታዘዘው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ፓርላማ በወሰን፣ ማንነትና አከላለል ዙሪያ የወሰነውን ዉሳኔ እንደማይቀበል አሳወቀ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ ግጭቶች፣ የዜጎች መፈናቀል፣ በክልሎች መካከል ያሉ የድንበር ውዝግቦች፣ የወልቃይት ጠገዴ፣ራያ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ አዲስ አበባና ሸዋ በመሳሰሉ አካባቢዎች ያሉ የፍትህና የ እኩልነት ጥይቄዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እየገፉ በመምጣታቸው ፣ አገሪቷን በዚህ ጉዳይ መምከር አለባት ከሚል ሲሆን ፓርላማው እነዚህን ጉዳዮች የሚያጠና ኮሚሽን እንዲቋቋም የወሰው፣ በተለያዩ ጊዚያት የሕወሃት እና በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ ፓርቲ አረና አመራሮች የኮሚሽኑን መቋቋም እንደማያደግፉ ሲገለጹ ነበር።

ሆኖም የትግራይ ክልል ምክር ቤት ይፋዊ በሆነ መንገድ በፓርላማ የጸደቀውን የኮሚሽኑን ዉሳኔ አንቀበለም ማለቱ ሕወሃት በሕግ የሚፈለጉ ወንጀለኞች ከመደበቁና ለሕግ አሳልፌ አልሰጥም ከማለቱ ባሻገር በይፋ በፌዴራል መንግስቱ ላይ ማመጹን የሚያመለከት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እየተናገሩ ነው።

በፓርላማው ዉሳኔ መሰረት፣ በወሰን፣ በማንነትና አከላለል ጉዳዮች ዙሪያ ሊቋቋም ያለው ኮሚሽን በቶሎ ተቋቁሞ ስራውን እንዲጀመር የብአዴን/አዴፓ የስራ አስፈጻሚ በመግለጫ የጠየቀ ሲሆን፣ የዶ/ር አብይ አስተዳደርም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ኮሚሽኑ በቅርብ ቀን ይቁቋማል ተብሎ ይጠበቃል።