January 29, 2019

“ነጻነት የማያወቅ ነጻ አውጪ” በሚለው መጽሐፉ፣ በገጽ ሁለት መቶ አምሳ ስድስት፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ኦሮምኛ ሁለተኛ የስራ ቋንቋ ቢሆን ጥሩ እንደሆነ ጠቅሶ ፣ የኦሮምኛ ፊደሉ በላቲን መሆኑ ግን ኦሮምኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ማድረጉ አስቸጋሪ እንደሚያደርገው የሚገልጹ እድምታ ያላቸውን ሐሳቦች አስቀምጧል።
“የኦሮሞ ህዝብ የአማርኛ ቋንቋ የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ ሆኖ በሚቀጥልባት የብዙ ቋንቋቆች ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አካል ሆኖ የመኖሩ ጉዳይ በምናልባዊነቱ ወደ መቶ በመቶ በሚጠጋ እርግጠኝነት ለመናገር በሚቻልበት ሁኔታ የግእዝ ፊደላትን ትቶ በላቲን እንዲገለገል ማበረታታትን ምን ይሉታል? “ ሲል ላቲንን ለኦሮምኛ መጠቀሙ ስህተት እንደሆነ ይናገራል።
“አማርኛ ቋንቋ የሚገለገልበትን ፊደል በጋራ በመጠቀም የኦሮሞ ህዝብ የሃገሩቱን የስራ ቋንቋ በቀላሉ ለመማር እና መልሶም የኦሮምኛን ቋንቋ ሌሎች የግእዝ ፊደልን የሚጠቀሙ ህዝቦች በቀላሉ ሊማሩ የሚችሉበትን እድል ማስፋት አይሻልም ነበር ወይ? ” ሲል፣ ኦሮምኛን በግእዝ ፊደል ቢጻፍ ኖሮ፣ የቋንቋዉን አዳማስ ከማስፋት አንጻር የበለጠ ጠቃሚ እንደሆነ ለማሳየት የሞከረው።
ኦሮምኛ በግእዝ ፊደል እንዲጻፍ በማድረግ ኦሮምኛ የበለጠ ተቀባይነቱ ጨመሮ ከአማርኛ ጋር ተድራቢ የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ ማድረጉ የበለጠ ለኦሮሞ ማህበረሰብ የሚጠቅም እንደነበረ የጻፈው አንዳርጋቸው፣ ሌሎች ኦሮምኛ የማያወቁ ወገኖችን ቋንቋዉን የመማር እድላላቸው በጣል ይሰፋ እንደነበረ ያስረዳል። “ይሄን አድርጎ (ኦሮምኛ በግ እዝ በመጻፍ) ከሃገሪቱ ሕዝቦች ትልቅ ቁጥር ያለውን የኦሮሞ ሕዝዝቦ ቋንቋ የህገሩቱ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲሆን መሟገት የተሻለ ዘዉጊያዊ እና ሃገራዊ ፋይዳ አልነበረውም ወይ ? አልፎ ተርፎ ከአማርኛ በስተቀር ምንም ሌል ሀገራዊ ቋንቋ የመማር ግዴታ በሌለባቸው አካባቢዎች የኦሮምኛን ቋንቋ ትምህርት፣ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ፣ የባህል እና የቋንቋ እክሉነት እና የሕዝቦችን የባህል ትሥር በጠንካራ መሰረት ላይ መጣል አይሻልም ነበር ?” ሲል አንዳርጋቸው ጥያቄ ያቀርባል።
ከሃያ ሰባት አመታት በፊት ሕወሃትርና ኦነግ በጋራ አገር ያስተዳድሩ የነበረ ጊዜ ኦነጎችና የኦነግ ደጋፊ ምሁራን ሕዝብን ሳያማክሩ ነበር ኦሮምኛ በላቲን እንዲጻፍ የወሰኑት። ያንን ያደረጉበት ፣ ላይ ላዩን የግእዝ ፊደል ኦሮምኛን ለመግለጽ አይችልም የሚል፣ ከእዉነት የራቀ፣ በጥናት ላይ ያልተመሰረተ መከራከሪያ እንደ ምክኗት አቅርበው የነበረ ቢሆንም ዋናው ምክንያታቸው ግን የኦሮሞ ሪፑብሊክ ለመፍጠር ሐሳብ ስለነበራቸው፣ ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር ካለመፈለግና ከሌላው ማሀብረሰብ ጋር በስጋ፣ በታሪክ በባህል የተሳሳሰረዉን የኦሮሞ ማሀረሰብ ለመነጠል፣ከኢትዮጵያዊነት የተለየ የኦሮሞ ማንነትን ለመገንባት ፈልገው ስለነበረ ነው። በአጭሩ የፖለቲካ ዉሳኔ ነበር።
ግእዝ ለኦሮምኛ ከብቃት በላይ ብቃት እንዳለው በርካታ ምሁራን በመረጃ ተመርኩዘው የኦነግ የፖለቲካ ዉሳኔ ትክክል እንዳልሆነ፣ የኦሮምኛ ቋንቋን እድገት እንደሚጎዳ ገልጸዋል፣ እየገለጹም ነው። ከነዚህ ምሁራን መካከል የአጋርፋ ተወላጅ የሆኑት ዶር አበራ ሞላ ናቸው።ስለ ዶ/ር አበራ ስራ በዊፒኪዲያ አማርኛ ሴክሽን ፣ ኦሮምኛን በግእዝ መጻፍ እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን ከላቲን በእጅጉ የተሻለ እንደሆነ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡
“ ኣንድ ኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ የኦሮምኛ ቃላትን ኣይጽፍም በማለቱ በኣለማወቅ በስሕተቱ ገፍተውበታል። ጎዸቱ፣ ቶኮፋዸ፣ ዹፌ፣ ዹጉማ፣ ጀዺ፣ ዻባ፣ ዻራርቱ፣ ባዻዻ፣ ዻዻ፣ ጄዼ፣ ዼራ፣ ዽባፍ፣ ዽባ፣ ነንዾከዼስ ምሳሌዎች ናቸው። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን “ዻ” የግዕዝ ኦሮምኛ ቀለም በኣንድ ቀለም በሁለት መርገጫዎች ከመክተብ ይልቅ “dha” በማለት በሦስት ቀለሞችና በሦስት መርገጫዎች በኦሮሚፋ መክተብ የተሻለ ሳይንስ ይመስላቸዋል።
ኣንድ ኣንድ የግዕዝ ቀለሞችን በላቲን ለመለየት ሦስትና ከሦስት በላይ ቀለሞችን መደርደር ያስፈልጋል። ግዕዝ ለኣዳዲስ ድምጾች ፊደል ሲፈጥር ቁቤ ለኣለው ፊደል ሌላ ድምጽና እስፔሊንግ በመጨመር መሻሻል ስለሚፈልግ ችግሩን ያባብሳል። ግዕዝን በላቲን እስፔሊንግ ለመጻፍ የሞከሩትም ጥቂቶቹን እስከኣሁን የኣዋጣቸው የሕዝቡ ስለቴክኖሎጂው በሚገ’ባ ኣለመረዳት ነው።
በሚገባ ሳይታሰብበት የግዕዝ ቀለሞች በላጭነትና ጥቅሞች ሳይገለጹ ታልፈዋል። ምሳሌ፦ ግዕዝ ችግር የለውም ማለት ሳይሆን የላቲን ቃላት እስፔሊንግ ዕድሜ ልክ ቢማሩትም ማስታወስ ኣይቻልም። በእዚህ ላይ “ኦሮሞ” የሚለው ቃል እስፔሊንግ በላቲን “Oromo” በኦሮሚፋ የኣለ በቂ ምክንያት “Oromoo” ነው። የቁቤ ላቲንና የላቲንን እንግሊዝኛ ተደራራቢ እስፔሊንግ ማስታወስ ኣስቸጋሪነት የተነሳ ትክክለኛዎቹን ማስተማርና ማስታወስ ሳያስቸግር ኣይቀርም። ግዕዝ ኣዳዲስ ቀለሞችን እየፈጠረ ሲያድግ ቁቤ በኣሉት የላቲን ቀለሞች ላይ እስፔሊንግ መጨመር ስለኣለበት ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየጠቀመ ማደጉ ኣጠራጣሪ ነው። ስለዚህ ቁቤ የኣናሳ ተጠቃሚዎች በመሆን ኦሮሚፋንና ኢትዮጵያን ሊያቈረቍዝ ይችላል።
በኣጠቃቀም የላቲን ፊደል ከግዕዝ ሳድሳን ቀለሞች ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ግዕዝ እንዚራኑን በኣንድኣንድ ቀለሞች ሲወክል ላቲን ዋየሎቹን ሳድሳኑ ጎን ማስከተብ ስለኣለበት ከሰባት ጊዜ በላይ እጥፍ ስፍራዎችን ያስባክናል። ይኸንን የግዕዝ ምሳሌ የ“ገ” 11 እንዚራን በላቲን ጠብቆና ሳይጠብቅ በመክተብ ልዩነቱን መመልከት ይቻላል።
ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ኦሮሚፋ 10 እንዚራን ሲያስፈልገው ግዕዝ ሰባት ብቻ ኣለው ይላሉ። ዋየል መደራረብ ትርፉ ስፍራ ማባከን ነው። ለምሳሌ ያህል “ዸ”ን በኣሥር ዋየሎቹ ለመክተብ ለቁቤ ላቲን 35 ቀለሞች ሲያስፈልጉት ለግዕዙ 15 በቂ ናቸው። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት የግዕዙ ብዙ ናቸው ይላሉ። የላቲን “a” ዓይነቶች ከ26 በላይ ናቸው። ዋናዎቹ 26 የላቲን ቀለሞች እንደግዕዙ 37 የተሟሉ ኣይደሉም።
ግዕዝ እንደኦሮሚፋ የኣሉትን (ኩሻዊ) ቋንቋዎን ጥሩ ኣድርጎ ኣይጽፍም የሚለው ወይም የግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም መወከል እንደችግር ተቆጥሮ ወደ ላቲን ለመዞር የቀረቡት ምክንያቶች ወደ እውነት የተጠጉ ኣልነበሩም። ግዕዝ ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለምና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ በማድረግ የተራቀቀ ፊደል ነው።
በግዕዝና በላቲን የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ስለማይግባቡ በየእለቱ እየተራራቁ ናቸው። ኣንድ ሕዝብ በተለያዩ ፊደላትና ቋንቋዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር። ኦሮሞው ዓማርኛ እንዳይማር ተወስኖ የፌዴራል ሥራ እንዳያገኝ ሆኗል። “
