
የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ፖፕ የሆኑት ፖፕ ፍራንሲስ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እንደፈለጉና ጉደኛው የታይታ ሰው ዐቢይ አሕመድም መልካም ፈቃዱን ገልጾ እንደመጣ የጠ/ሚ ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አሁን ማምሻውን ኢቴቪ ባቀረበው የምሽት ሁለት ሰዓት ዜና ላይ ገልጿል፡፡
አስቀድሞ ጉደኛው የታይታ ሰው ዐቢይ አሕመድ በጉብኝቱ ወቅት ለፖፑ የሥነጥበብና የባሕላዊ አልባሳት ስጦታ አበርክቶ ሲለካለክ ሳየው ይሄ ሊከተል እንደሚችል ፈርቸ ነበር፡፡
ቀደም ሲል የነበሩ የካቶሊክ ፖፖችም ሀገራችንን የመጎብኘት ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በ1928ዓ.ም. በሀገራችን ላይ ወረራ በመፈጸም በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (በመንግሥታቱ ማኅበር) አገለግሎት ላይ እንዳይውል የተከለከለን የመርዝ ጋዝ መጠቀምን ጨምሮ በወገን ላይ መጠነ ሰፊ አረመኔያዊ ጅምላ ጭፍጨፋ በመፈጸም መጠነ ሰፊ እልቂትና ውድመት በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ ካደረሰው የፋሺስት ጣሊያንን ወራሪ ጦር ጋር በተያያዘ የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ለዚህ አረመኔ ወራሪ የፋሽስት ጦር በወቅቱ በነበሩት ፎቶው (ምሥለ አካሉ) ላይ በምታዩዋቸው መሪዋ ፖፕ ጆን ፖል 2ኛ በኩል “ይቅናቹህ!” ከሚል የመልካም ምኞት ቃልና የማበረታቻ ንግግር ጋር ቡራኬ ሰጥታ በመሸኘቷና በዚህ ኢክርስቲያናዊ ተግባሯ ምክንያትም የኢትዮጵያ ሕዝብ በ “ቤተክርስቲያኗ” ላይ በእጅጉ ስላቄመ፣ ስለተከፋ፣ ስለተቀየመና “ቤተክርስቲያኗም” ለስሕተቷ ይቅርታ እንድትጠይቅ ብዙ ጉትጎታ ቢደረግባትም እስከ አሁንም ድረስ ለዚህ ኢክርስቲያናዊ ታሪካዊ ስሕተት የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት “ከሕዝብ ተቃውሞ ይነሣል!” በሚል ፍራቻ ጉብኝቱ ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡
በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሮማ ካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ለዚህ ለፈጸመችብን ኢክርስቲያናዊና ታሪካዊ ግፍና በደል ይቅርታ እንድትጠይቅና ካሳ እንድትከፍል ለማድረግ ከዓመታት በፊት ጀምረው ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
እንግዲህ ይታያቹህ ክልፍልፉ ዐቢይ ይህ ታሪካዊ ችግር፣ በደልና ግፍ በአግባቡ ባልታከመበት፣ ባልተፈታበት፣ ባልተቀረፈበት ሁኔታ ነው ፖፕ ፍራንሲስን ሀገራችንን በማስረገጥ በቁማችን ሊቀብረን፣ ታሪካዊ ውርደት ሊያከናንበን፣ ሁለተኛ ሊገድለን፣ በንጹሐን የግፍ ሰለባ ወገኖቻችን ደም ሊሳለቅብን የሚፈልገው!!!
እኛ ኢትዮጵያውያን አሁን ላይ ስንታይ ደሀ እንሆን ይሆናል ነንም፡፡ ይሁንና ድህነታችን የቱንም ያህል ቢጠናብን ብሔራዊ ክብራችንንና ኩራታችንን ለገንዘብ ወይም ለዳቦ እንድንሸጥ እንዲያስገድደን መቸም ፈቅደን አናውቅምና ወደፊትም ፈጽሞ አንፈቅድምና ይሄንን የብሔራዊ ክብርንና ኩራትን ምንነትና ዋጋ ጨርሶ የማያውቀውን የማይገባውንም እዩኝ እዩኝ ባይ ወያላ ዐቢይ አሕመድን እረፍ በሉት!!!
አይ! የሚል ከሆነና ያሰበውን በማድረግ ፖፑን ሀገራችንን የሚያስረግጥ ከሆነም እኛ ሳናልቅ ይሄንን ሊያደርግ እንደማይችል ከወዲሁ ይወቀው!!!
ፋሽስት ጣሊያን በአምስት ዓመቱ የወረራ ቆይታው ባደረሰውና በፈጸመው ጭፍጨፋ ያልተጠቃ ያልተጨፈጨፈ የየትኛውም ጎሳ ብሔረሰብና የእምነት ተቋም ተከታይ የለምና ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉም ሰለባ ነውና ዛሬም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ይሄንን የፖፕ ፍራንሲስን ጉብኝት አጥብቆ እንዲቃወምና እንዲያወግዝ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥሪየን አቀርባለሁ!!!
እንደ አንድ ክርስቲያንም ያ የፋሺስት (አረመኔ) ጣሊያን ወረራ ጥቃት በዋናነት ክፉኛ ተጠቂና ተጎጅ ያደረጋት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስም ይሄንን የፖፕ ፍራንሲስን ጉብኝት አጥብቆ እንዲቃወም ጥሪየን አቀርባለሁ!!! ሲኖዶሱ ይሄንን ማድረግ ሳይችል ቢቀርና ጭራሽም ተባባሪ ሆኖ ቢገኝ እኛ ሕዝበ ክርስቲያን በእናንተ ጳጳሳት ተብየ ምንደኞች ላይ የምንነሣ መሆኑን እወቁት!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
