* በፕራይቬታይዜሽን (ወደግል ይዞታ በማዞር) ስም ታላላቅ የመንግሥት ድርጅቶች የነጻ ያህል እጅግ በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ ያለ ጨረታ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ተሸጠውለት፡፡ ተሰጥጦቶት ቢባል ይሻላል ያውም በራሱ ብር መሰላቹህ በባንክ ብድር ወይም በሕዝብ ገንዘብ ነው ልብ በሉ በሕዝብ ገንዘብ፡፡ ይሄንንም የሕዝብ ገንዘብም ሳይመልስ ነው የቀረው፡፡

* ከሕግ በላይ ሆኖ ያለ አንዳች ተጠያቂነት ጥቅም ሲያግበሰብስ መኖሩ፡፡ ከሕግ በላይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዜጋ ባለሀብቶች ሕጉና ቢሮክራሲው በገመድ ላይ የመራመድ ያህል ሆኖባቸው ሲዋከቡና እንዳይሠሩ ሲደረጉ እሱ ግን ከሕግ በላይ ከመሆኑም በላይ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እየተደረገለት በብቸኝነት እንዲፏልል ተደርጎ፡፡

* የውጭ ዜግነት ላለው የተከለከለ በሆነ ወይም ሊሠማራበት በማይቻልበት የኢንቨስትመንት (የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት) ዘርፎች ሕግ ተጥሶ እንዲሠራ ተደርጎ፡፡

* ወደ ውጭ የሚልካቸውን የወርቅና ሌሎች የማይገለጡ መዓድናትን ጉምሩክ ሳያውቀው ወይም በጉምሩክ በኩል ሳያልፍ በሕገወጥ ዝውውር ግብርና ቀረጥ ሳይከፍል እንደፈለገ እንዲያጉዝ ተደርጎ፡፡

በመሳሰሉት ሕገወጥና ውንብድና በተሞሉ መንገዶች ተሠማርቶ ነው ሀገሪቱን ሙልጭ አድርጎ የዘረፋት!!!

ታዲያ ወዶ መሰላቹህ እንዴ ወይም ደግሞ ሰውየው በአባቱ ዓረብ ቢሆንም በእናቱ ግን ትግሬ ስለሆነ ብቻ መሰላቹህ እንዴ ለሕወሓት ነፍሴንም እንኳ ቢሆን እሰጣለሁ!” ሲል የተናገረው???

እርግጥ በአንድ መድረክ ላይ ተናገረ እንደሚባለው በሀገሪቱ ውስጥ በእሱ ስም ከሚንቀሳቀሰው ሀብት የሱ ሀብት የሆነው ሃያ በመቶው ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ብሎ መናገሩ የአንድ ሰሞን የወሬ ርእስ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የተቀረው እንግዲህ ሰውየውን እንዲህ በሕገወጥ መንገድ እንደፈለገ እንዲሠራ የፈቀደለትና ታላላቅ የመንግሥት ንብረቶችን በመናኛ ዋጋ እንዲዛወርለት ያደረገው የወያኔ መሆኑ ነው፡፡

ይሄንን ወንበዴ ነው እንግዲህ የምለቃቅመው ፍርፋሪ ካላሳጣኝ የፈለገውን ቢያደርግ ምን ገዶኝ!” በማለት እነሆድ አምላኩ ሕሊናቢስ ኩሊዎች አላሙዲንን ጭራሽ እንደ የሀገር ባለውለታና ሀገር አልሚ አድርገው ጥቂትም እንኳ ሳያፍሩ ሲያወድሱትና ሲያመሰግኑት የሚታዩት፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር በዚህ መንገድ ውልቃችንን አስቀርቶ ዘርፎ ያካበተውን ሀብት ሳውዲዎች ከነሱ ያጭበረበረውን አንድ ቢሊየን (ብልፍ) ዶላር ከዚህ ውስጥም የተወሰነውን ለሳውዲ ስታር የሩዝ እርሻ አውሎታል ይሁንና እነሱ ግን ይሄንን ለእርሻ ተብሎ የወጣውን ገንዘብ አጭበርብረህ በልተሀል!” ብለው አሳበው አስረው ሲያበቁ ትንሽ ሲተውለት በስተቀር ያካበተውን ሀብት እንዳለ ተረክበው እንደፈቱት እየተነገረ ነው፡፡

እንግዲህ መረጃው ትክክል ከሆነ የጠገበው ጅብ አላሙዲን ቀርቶ የተራበው ጅብ አላሙዲን እንደገና ሊበላህ፣ ሊግጥህ፣ ሊዘርፍህ፣ ሊያራቁትህ እንደሚመጣብህ እወቅ እሽ ምድረ ጅል???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com