!

31 Jan 2019, 08:45

Top Masud Member+ Posts:5415Joined: 18 Jun 2013, 09:06

በ1984 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ካርታ ሲዘጋጅ ህወሓት የተከዜን ወሰን በመጣስ አልፎ ሲቲት ሁመራን፣ወልቃይትን፣ጠገዴንና ጸለምትን ወደ ትግራይ ሲጠቀልላቸው የጉልማ (የጎንደር ልማት ማህበር) ሀላፊ የነበሩት ዳኘው ወልደ ሥላሴ ቀይ መስመር እንዳለፉ ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለአቶ ታምራት ላይኔ ይሄን ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር። ክቡር ዳኘው ወልደ ሥላሴ ውሳኔው ሁለት ወንድማማቾን የሚያፋጅ ታሪካዊ ስህተት ለወደፊቱም አይበጅም ብለው ነበር።ደብዳቤው እጅግ የሚደንቅ አሁን እየተከሰተ ያለውን ነባራዊ ሁናቴ አስቀድሞ የተነበዬ ነበር።የተቋቋመው የማንነት የወሰን ኮሚሽን እንዲህ ያሉ ታሪካዊ ሰነዶችን መመርመር ይኖርበታል።እኛም መረጃዎችን ቆፍረን እናወጣቸዋለን!!
የሱፍ ለጋስ