February 13, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/92801
Addis admass
በኢትዮጵያ ከሰማኒያ በላይ ብሔረሰቦች እንደሚገኙ ለረጅም ጊዜ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ያሉ ግን ለይተን ያላወቅናቸው ብሔረሰቦች ይኖራሉ ብለው የጠረጠሩትና ወደ ጥናቱ የገቡት ዶ/ር ባይለኝ፤ ይህን ቁጥር ወደ ሁለት መቶ ከፍ አድርገውታል፡፡ ለይተን ያላወቅናቸውን ለይተን በማወቃችን፣ “ሕዝቦች” እያልን ስንጨፈልቃቸው የቆዩትን፣ ከዚህ ሳጥን አውጥተን ብሔር ብለን ለማክበር በመብቃታችን፣ ለእኔ ትልቅ የምሥራች ነው። ኢትዮጵያን የሁለት መቶ ብሔረሰብ አገር አድርገን እንድናውቃትም አስችለውናል፤ አጥኚውን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

አሁን አንድ መቶ ሚሊየን የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የእነዚህ ብሔረሰቦች ድምር ያስገኘው ነው ማለት ነው፡፡ የእነዚህን ብሔረሰቦችና የሕዝባቸውን የወደፊት ሕይወት የተቃና ለማድረግ የተሰለፉ የብሔረሰብና በአገር አቀፍ ደረጃ የተደራጁ ከአንድ መቶ በላይ ክልላዊና አገር አቀፍ ፓርቲዎች፣ ሰሞኑን በኢሲኤ አዳራሽ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ እንደ አንድ ሰው፣ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ የተሳተፉበት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ እራሳቸውን ዶክተር ዐቢይን ጨምሮ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ዶ/ር መረራ ጉዲና የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡
የአቅራቢዎችን የዘር ግንድ ያሰሉ፣ ከእነሱ የዘር ግንድ ወገን የሆነ በአወያይነትም በጥናት አቅራቢነትም አለመሳተፉ ቅሬታ የፈጠረባቸው “የእኛ ሰው የት አለ” የሚል ጥያቄ ሲያነሱ አጋጥመውኛል፡፡ በእውነት “የእኛ ሰው የት አለ” ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡እኛም ከእነ እከሌ እኩል (አሁን ያነሰ ሰው አላቸው እያልኩ አይደለም) ጐልቶ የማይታይ ሰው አናውጣ፣ ኢትዮጵያን ሰው በሰው እናድርጋት የሚል ፉክክር ከሆነ እሰየው የሚባል ሃሳብ ነው፡፡ ሰው ስል ያወቀ የበቃ ማለቴ እንጂ በተፈጥሮ የሰው ትንሽ እንደሌለ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡እያንዳንዱ
