February 15, 2019
“ታላቁ ተቃርኖ” በሚል ርዕስ ሀብታሙ አለባቸው የተባለ ኢትዮጵያዊ የጻፈውን ግሩም ጥናት-አከል መጽሐፍ እያነበብኩ ሳለ የልጅ ኢያሱ ታሪካዊ ስህተት የተጠቆመበት ቦታ ላይ ስደርስ አላስችልህ አለኝና ወደራሴው ጭሮሽ ገባሁ – እንደለመደብኝ ልብሰከሰክ፡፡
ልጅ ኢያሱ ከነዚያ ውክቢያ ከበዛባቸው ጥቂት የሥልጣን ጊዜያቱ በኋላ በባላንጣዎቹ እጅ ሲወድቅ ምን አለ – “ልጅነትን ‹እግዚአብሔር ይማርሽ‹ በሏት”፡፡ ወርቅ አበባባል ነው፡፡ የሠራው ስህተት ገብቶታል ማለት ነው፡፡ ለዚያ ያደረሰው ልጅነቱ – አለመብሰሉ – እንደሆነ በመጨረሻው ተከስቶለታል ማለት ነው – እንደኔ አረዳድ፡፡ ልጅነት እኮ ግን ከልጅነት ቦታው ውጭ ከዋለ መጥፎ ነው፡፡ አሁን ማን ይሙት የ16 ዓመት ታዳጊ አገር እንዲያስተዳድር ሥልጣን ይሰጣል? ምን ዓይነት ሀገር ውስጥ ነው እኖር የነረው ግን? አሁንስ ቢሆን? “በስምንተኛው ሺ ውርጋጥ አገር ይገዛል፤ልጆች የሽምብራ ዛፍ ሥር ተቀምጠው (ጠማማ) ፍርድ ይሰጣሉ፡፡” ይባል ነበር ዱሮ፡፡ ወይ ይቺ ጉደኛ ስምንተኛው ሽህ! ሳንጠራትና ሳንፈልጋት ከች አለች’ኮ፡፡
በሥልጣን አያያዝ ረገድም ሆነ በማንኛውም ማኅበራዊና ግላዊ የነገሮች አካሄድና ክስተት ላይ ዕድሜ ትልቅ ግብኣት ነው፡፡ ዕድሜ ከስሜት ጋር ያለው ቁርኝት ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ዕድሜ ከወቅት ንፋስ ጋር ያለው ዝምድና ሊረሳ አይገባም፡፡ ዕድሜ ለጥፋትም ለልማትም ወሳኝ ነው፡፡
እኔ ለምሣሌ አሁን 55 ዓመቴ ነው፡፡ መሪየን በ12 ዓመት ገደማ እበልጠዋለሁ – ፊታውራሪ መሸሻንና ባለቤታቸውን ወ/ሮ ጥሩዓይነትን እንዳታስታውሱብኝ እንጂ የትዳር አጋሬንም ጭምር ይቺኑ ታክል እበልጣታለሁ – ጉድ የሚፈላው ትንሽ ቆየት ስንል ነው – ሊያውስ ከቆየንና ካቆዩን አይደል – በወቅተኞች የተያዘው ዜማና ቀረርቶ እኮ ሌላ ነው – ሆ! “አዲስ እረኛ በግ አያስተኛ” አሉ?…
መሪየና እኔ ያለን ዕድሜ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከመረዳት አኳያ እንድንለያይ ያደርገናል፡፡ በዚያ ላይ በግል ባለኝና በነበረኝም የንባብም ይሁን የማኅበራዊ ተራክቦ ዶሴ ምክንያት የኔ ዕድሜ ከኋለኞች እንጂ መሪየ ከሚጋራቸው ከፊተኞች ባለመሆኑ በትንሹ አሥር ምናባዊ ዓመታትን ጨምሩበትና 65 አድርጉልኝ፡፡ በተቃራኒው መሪየ ከፊተኞች እንጂ ከኋለኞች ጋር እምብዝም ተጣጥሞሽ ይኖረዋል ብዬ ስለማልገምት ከርሱ ዕድሜ ላይ በትንሹ 10 ቀንሱና አሁን የ32 ዓመት ጎረልማሳ አድርጉት – አማርኛውም ጠፋኝ፡፡ ምን እያልኩና ወዴየትም እያመራሁ እንደሆነ እኔ ራሴም አልገባኝምና ዛሬ እስኪሰክን ሁላችንም በትግስት እንጠብቅ፡፡ ወይ ቅኔ! ቅኔ እንዲህ ይርከስ?
ኢሕአዴግ የተባለው ጭራቅ – ጭራቅ ብቻ? – የማፊያዎች ቡድን – የሂትለሮችና ሙሶሊኒዎች ጥርቅም – የዘረኞች በረት – የሆዳሞች ጋጣ – የወጣቶቻችንን አእምሮና የአስተሳሰብ አድማስ ክፉኛ ሲኮደኩድ ከርሞ ከእርሱው ጓዳ ወጡ የተባሉ ወጣች አሁን ሀገሪቱን ይዘዋል፡፡ ከዚህ የዐውሬዎች ዋሻ የወጡ ልጆች ምን እንዲሠሩልን እንጠብቃለን? እንዴት እንደተጸነሱና እንደተወለዱ እያወቅን፣ በምን አንቀልባና እንዴት ታዝለው እንዳደጉ እያወቅን፣ ምን ወተትና ምን ዓይነት ሴሪፋም እየተመገቡ እያወቅን፣ ምን ዓይነት የዕንቅልፍ ማስያዣ ተረቶችና ጨዋታዎችን እየኮመኮሙ እንዳደጉ እያወቅን… አሁን እነዚህን ወጣቶች ከሚያውቁት ዘፈን ውጪ ምን አዲስ ዘፈንና እንዴትስ እንዲዘፍኑልን እንጠብቃለን? የተማሩት ዘረኝነትን፣የቀሰሙት ማሰር መግደልን፣ ያዩት መቀማት መዝረፍን፣ ያደጉበት በአቋራጭ ከብሮ መገኘትን፣ ያዩት ፍትህን ማንሻፈፍን… እነዚህ ጮርቃዎች ጥቂት ትያትሮችን በመተወን ከመምህሮቻቸው በልጠው ለመገኘት ከመሞከር ባለፈ የት የተማሩትን ይተግብሩት? በዚህ መልክ ከእባብ ዕንቁላል ዕርግብ እንዲፈለፈል ከጠበቅን ችግሩ ከእባቦቹ ወይም ከዕርግቦቹ ሳይሆን ከኛ ከተስፈኞቹ ነው፡፡ ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን እኮ – ኢዝወዝን በቅጡ ሳይለዩ በጌቶቻቸው ቅያስ ተጉዘው በሀሰት መረጃና በለብለብ የይድረስ ይድረስ የተልእኮ ትምህርት የዶከተሩ (ብዙዎቹን ማለቴን ነው) እነዚህ የወያኔ አሳዛኝ ፍጡራን ልጆች ምን እንዲያደርጉ እንጠብቃለን? የት ያገኙትንና ማን የሰጣቸውን ይስጡን? ለሹመትስ ቢሆን ከለመዱት የዘር አሹዋሹዋምና ከሚያውቋቸው የዘር ሐረግ ትምህርት ቤት መለሳዊ ምልምሎችና ምሩቃን ውጪ ማንን አምነው እንዴት ይሹሙ? በአፍ ጤፍ መቁላትና በተግባር እንጀራ አስፍቶ ወጪትንም ጥዶ ማባያ በመሥራት 100 ሚሊዮን ሕዝብ መመገብ ለዬቅል ናቸው፡፡ አታናግረኝ እንጂ ወንድማለም! የሚነገረውና የሚሠራው አንድ ቢሆንማ ኖሮ የዓለማችን ቅርጽ የአሁኑን አስጠሊታ ቅርጽ ባልያዘ ነበር፡፡ ፖለቲካ ቀልድ መሰለህ? “ዚኣከ ለዚኣየ” የሚሏትን ማለፊያ የቆሎ ተማሪ ቤት ብሂል መርምሩልኝ፡፡ እንጂ ከተሾሙት ወጣቶችና ጎልማሣዎች መሀል ስንትና ስንት ወንጀል የፈጸሙና ስንትና ስንት የኢኮኖሚ ምዝበራ ያካሄዱ እንዳሉ ይነገር የለም እንዴ? የሚወዱት ሌባና የሚጠሉት ሌባ ላይ ሰዎች ያላቸው አመለካከት እንደሚለያይ የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ሁኔታ በማየት በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ዘርና የዓላማ መቀራረብ እንዲህ ናቸው፡፡ ዓላማና ጥቅም ሁለመናን ያሳውራሉ፤ አስተዋይነትን ያጠፋሉ፤ ባጭሩ ከከትብም ያሳንሳሉ፡፡ …አሁን አነሳሴ ገባኝ!
አንድ ወሬ በአእምሮየ ብቅ ጥልቅ እያለ እያስቸገረኝ ነውና ላስቀድመው መሰለኝ፡፡
በሥነ ልቦና ትምህርት በስፋት የሚጠቀስ ሂፕኖሲስ (hypnosis) የሚባል ቃል ወይም ጽንሰ ሃሳብ አለ፡፡ ግሱ hypnotize ነው፡፡ ባማርኛ እንደነገሩ ብንመልሰው ማነሁለል፣ አእምሮን መግዛት፣ ማቂያቂያል… ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህን “ጥበብ” በዋናነት የሚጠቀሙበት ሳይኪያትሪስቶች ናቸው፡፡ አንድን ጥበብ ደግሞ ለበጎ ዓላማም ለመጥፎ ዓላማም መጠቀም እንደሚቻል ይታወቃል፡፡
ባደጉ ሀገሮች በዚህ ጥበብ ወንጀለኞችን እየመረመሩ የተደበቁ የወንጀል ድርጊቶችን ሰውዬው ራሱ እየዘከዘከ ያወጣዋል – አእምሮ ወደነፈዝነት ስለሚለወጥ ያልተፈለገ መልእክትም መጻፍ ይቻላል፡፡ ይህን “ጥበብ” የሚገለገል ሰው ዐዋቂውን የአንጎል ክፍል (conscious) ሥራውን እንዲያቆም አድርጎ subconscious ወደሚባለው የአእምሮ ጓዳ ሰተት ብሎ ይገባና ያለውን ምሥጢር ሁሉ ይቦጠቡጣል፡፡ በዚህ ጥበብ ተጠቅመው ሴትን ምናልባትም … የሚደፍሩ የ“ሙያ”ው ባለጌዎች እንዳሉም በስፋት ይነገራል፡፡
ይህ የሂፕኖሰሲ ጥበብ በዶ/ር አቢይ ጥቅም ላይ ውሏል፤ እየዋለም ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በመጀመሪያ አካባቢ እውነት ይመስለኝ ነበር፡፡ የአቢይ ጅማሮ ሂፕኖሲስ ቢጤ መሆኑን ብረዳም ለበጎ ዓላማ የሚያውለው መስሎኝ እኔም በተወሰነ ደረጃ hypnotized ሆኛለሁ – የከፋ ነገር እንዳልደረሰብኝ ግን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ በምናነበውና በምንሰማው መልክ የምንጓዝ ከሆነ ግን ወደፊት እጅግ በጣም ያስፈራኛል፡፡ እናም ከምፈራው የአዲሱ መንግሥት የሂፕኖሲ መጥፎ ገጽታ እድን ዘንድ ፈጣሪየ በቶሎ እንዲወስደኝ እለምነዋለሁ – እነአባጫላና ገመዳ በዚች ጸሎት እንደሚተባበሩኝም ተስፋ አለኝ – ወይ ኢትዮጵያ፡፡ በዘመን መጨረሻ እንዲህ ትሆኝ? “ሲያልቅ አያምር” የሚባለው ለካንስ ለዚህ ኖሯል፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮማ ከ800 የሚበልጡ ንጹሓን ዜጎችን ወደው ባልተፈጠሩበት የዘር ሐረጋቸው ምክንያት ብቻ ከሥራ ባልተወገዱና በምትካቸውም በትምህርትም ሆነ በችሎታ ከነሱ ያነሱ በነገዳቸው ብቻ የተመረጡ ዜጎች ባልተመደቡ ነበር – ሂትለር ከዚህ በላይ ምን አደረገ? ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት የአርያን ዘር ነው ያለው? እያንዳንዱ የአስተሳሰብ ድኩም በፈረቃ እየመጣ ሳይወከል ተወክየለታለሁ የሚለውን ነገድ ስም እያንጠለጠለ ግፍና በደል የሚፈጽምብን እስከመቼ ነው? ለአንባቢም ለፈጣሪም የምሰነዝረው ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ሰውን በዘሩ ምክንያት የማንጓለል ክስተት ብቻውን ምፅዓትን ይጠራል – ደም አለመፍሰሱ አይደለም ዋናው ነገር፡፡ ፍትህ መጓደሉና የእግዚአብሔርን እኩል ፍጡራን አንዱን ወርቅ ሌላውን ኩበት ማድረጉ እንጂ፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡ ማንም ቢሆን ከዚህ አስቀያሚ ማዕቀፍ ካልወጣ ስንዝር ሊራመድ እንደማይችል ጊዜ ራሱ በቅርብ የማይረሳ ትምህርት ይሰጠናል፡፡ በትግስት ጠበቅ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም፡፡
ሀገርህ አልታደለችም፡፡ አንተም ተናጋሪ እንስሳ ሆንክና ግፋ ቢል ማንጋጠጥ እንጂ ወደ ጎንህ ዘወር ብለህ እንኳን ከመሰሎችህ ጋር “ኧረ ምን ይሻለናል? ምን እናድርግ?…” ብለህ አትጠይቅም፡፡ እንደአጋሰስ የመጣው ሁሉ ግሳንግሱን ሲጭንብህ ዝም ብለህ ትጫናለህ፡፡ አፍዝ አደንግዙን ለመፍታት አትጥርም፡፡
ይህን ዜና አንብብ፡፡ (በመጨረሻ ላይ አስቀምጨዋለሁ፡፡)
አሁን ያለው አካሄድ በፍጥነት ካልተለወጠ በቅርቡ እንዲህ ይሆናል፡፡
1. በወያኔ ዘመን ይደረጉ የነበሩና አሁን የቀሩ የሚመስሉ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰው ይቀጥላሉ፡፡ ምክንያቱም እውነትና ምክንያት ጠፍተው ዘረኝነትና ሆዳምነት መድረኩን ከያዙት ጥቅምንና ሥልጣንን ለማስጠበቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ ጨካኝና ዐውሬ መሆን ነው፡፡ መጻፍ፣ መናገር፣ ማተም ፣ መሣተም፣ መሰብሰብ፣ ወዘተ. በአሸባሪነት የሚያስከስሱ ይሆናሉ፡፡ አልበጃቸውም እንጂ ወያኔዎች እንደዚያ ዐረመኔ የሆኑት ወደው አልነበረም፡፡ “አታሞ በሰው እጅ ታምር” ነው ነገሩ፡፡
2. አሁን የተለቀቀው ኢንተርኔት ቀስ በቀስ መታፈንና በሂደት ልክ እንደሰሜን ኮሪያ የለየልን እንስሳት እንሆናለን፡፡ ሁሉም ይዝጋጋና እንዱሮው በፕሮክሲ ሳይቶች መጠቀም እንምራለን፡፡ የአሁኑ ሆይ ሆይታና የደስታ ቡረቃ ሁሉ እንደህልም ይሆንና ይበናል፡፡ ሂፕኖሲሱ እውነት መሷቸው ከሩቅም ከቅርብም የመጡ ተቀናቃኞችም በሏቸው ተቃዋሚዎች ከነአቢይ ጋር ያላቸውን የወረት ፍቅርና የጫጉላ ሽርሽር ጨርሰው ወደየመጡበት ይመለሳሉ፡፡ አሁን ይህን ሁሉ የአሠራር ግድፈትና ዘረኝነት ባይናቸው በብረቱ እያዩ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ጭጭ ያሉበት ምክንያት ባይገባኝም ጊዜው መድረሱ አይቀርምና ያኔ በዕድላቸውና አሁን በሚሠሩት ስህተት ይጸጸታሉ – መጸጸትን ካወቁ፡፡ ነገሩ “ቂጣም ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል” እንዲሉ ነውና ሁኔታዎች እየከረሩ ሲመጡ አርጩሜው ወደነሱ ሜዳም መግባቱ አይቀርም – እያዋዛ፡፡ ግን ህልም እልም፡፡
3. ወያኔ በ27 ዓመታት ሊሠራው ያልቻለውን ኢትዮጵያን በአንድ ነገድ ቁጥጥር ሥር የማዋል ተግባር በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ እውን ሆኖ እናያለን፡፡ ስለዚህ የሸገርን ወደ ፊንፊኔ መለወጥ ተወውና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለመንቀሳቀስ አፋን ኦሮሞ መናገር ይጠበቅብሃል፡፡ አለበለዚያ በአሁኑ ወቅት በነታከለ ኡማ መሠሪነት በሂፕኖታዜሩ የበላይ ጠባቂነትና ቡራኬ ከየኦሮሞ አካባቢዎች በነጃዋር እየተመለመሉ ወደ ፊንፊኔ ማነው ወደ አዲስ አበባ በሚላኩና የኗሪነት መታወቂያ በገፍ እየተሰጣቸው እንደሆነ በሚነገርላቸው፣ በዘር ቅኝት ተኮትኩተው ባደጉ ነበልባል የኦሮሞ ወጣቶች አማካይነት በፓንጋ(ቆንጮራ) አንገትህን ትቀነጠሳለህ፡፡
4. በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመንግሥት መ/ቤቶች አንድም ኢ-ኦሮሞ ዜጋ አይኖርም፡፡ “በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም” ብለዋል እመት ዘርፌ፡፡ አዎ፣ ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ አሁን እንሳቅ፡፡ አሁን እንሞጋገስ፡፡ በጀርባሽ ምን እየተሠራ እንደሆነ ግን ከሰይጣን በስተቀር ፈጣሪም አያውቀውም፡፡ ኢትዮጵያ ካልጠፋች ዕንቅልፍ የማይወስደው አካል የአሠራር ሥልቱንና መልኩን እንደየዘመኑ እየቀያየረ ሌት ከቀን ሥራውን እየሠራ ነው፡፡ እኛ ግን ተኝናል፡፡
5. ስለሆነም ከሂፕኖሲስ እንውጣ፡፡ እውነቱን አንጋፈጥ፡፡ በቀላሉ አንታለል፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ማወቅ ለተሰናቸውና ከወያኔ ቅንጣት ላልተማሩ ምሥኪን ወገኖቻችንም እንጸልይላቸው፡፡ ከአንጀቴ ነው የማዝንላቸው – ከማዝንባቸው በተጨማሪ፡፡ ሰው አንጎሉን ትቶ እንዴት በዘር መሥፈርት ያስባል? እንዴ! ኧረ ተው… ተው…ግዴላችሁም? የሚያቀባብር ሥራ እንሥራ እንጂ ጎበዝ!
ቀጥሎ ያለው መረጃ ከዚህ ምንጭ የተወሰደ ነው – https://www.satenaw.com/amharic/archives/63644
በዶር አብይ መንግስት በተሾመው ታከለ ኡማ በኩል በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን አከናውኗል።
1. 76,200 የአዲስ አበባ መታወቂያ ከባሌ፣ከወለጋ ለመጡ ነዋሪ ላልሆኑ ተሰጥተዋል።
2. 8214 ሰራተኞች ያለምንም ውድድር በዝውውር ኦሮሞ የሆኑ ብቻ ተመድበዋል።
3. ከአዲስ አበባ በጀት 2.34 ቢሊዮን ብር ለካሣ ልማት ለኦሮሞ ተከፋፍሏል።
4. ብዙ የቀበሌና ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለኦነግ አባለት ተሰጥተዋል።
5. 613 ሚሊየን ብር ለኦሮሞ ሥራ ዕድል ፈጠራ ሊወሰድ ነው።
6. 8 ሰራተኞች ይህንን በመጠየቃቸው ተባረዋል።
7. ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ 6 ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ኦሮሞዎች መነኩሴ መሥለው አሥተዳደሩ ላይ ተመድበዋል።
8. የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ሁሉንም ኃላፊነቶች ለኦሮሞ ብቻ አድርጓል።
የጨነቀው የታከለ ኡማ ቡድን ለወ/ሮ ሰናይት የፃፈው ደብዳቤ!
ምንጭ – https://www.satenaw.com/amharic/archives/63615
Tweet“የፅ/ቤቱን ደህንነት የሚያጎድፍ የተሳሳተ መረጃ ሆን ብሎ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ለነዋሪነት መታወቂያ አማርኛ መናገር እንደመስፈርት በማጣቀስ ለሚዲያ በተሳሳተ አግባብ መረጃ በመስጠት ከስራ መታገድዎ ይታወቃል።
በመሆኑም ከቀን 04/06/ 2011 ዓም ጀምሮ ወደ ስራ እንዲመለሱ እያሳወቅን መረጃውን ካስተላለፈው ሚዲያ ጋር ትክክለኛውን መረጃ እንዲያስተላልፉ በቀጣይ የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን።”

