February 16, 2019 |

Source: https://mereja.com/amharic/v2/93514

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ዓመታዊ በጀታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊጠይቁ መሆኑ ተነገረ። ፍርድ ቤቶች እስካሁን እንደሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሁሉ በጀት የሚመደብላቸው በገንዘብ እና ኤኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ነዉ።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ግን ፍርድ ቤቶች የሚተዳደሩበትን በጀት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል በማለት ይደነግጋል ሲል ይደነግጋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የእስካሁኑን አሰራር “ፈር የለቀቀ” ሲሉ ተችተዋል።
አቶ ሰለሞን አረዳ “መንግስት የዳኝነት አካልን የሚያስተዳደርበትን በጀት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጥታ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ” መሆኑን መናገራቸውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮምዩንኬሽን ዳይሬክቶሬት በፌስቡክ ገፁ ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል።