February 16, 2019 | Posted by: Zehabesha r
ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን ለቀቁ:: ሌሎችም እየተከተሉ ነው::
በራያ ሕዝብ ላይ ሕወሓት እየፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ፣ የራያ ማንነት እንዲከበር ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው ጥያቄ እንዲመለስ የሚደግፉ፣ በፓርቲው ውስጥ የራያ ተወላጆች መገፋትና አለመታመንን የተቃወሙ ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን መልቀቃቸው ታወቀ::
በሳዑዲ አረቢያ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው ሚስባህ ማህመድ እና በካይሮ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው አሊ መሀመድ ሕወሓትን ከለቀቁት መካከል ይገኙበታል::
የራያ ተወላጆች እየወሰዱት ባለው አቋም በሕወሓት ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥንና መፈረካከስን ፈጥሯል::
ተከታታይ መረጃዎችን ከዘ-ሐበሻ ይጠብቁ::
Sponsored by Revcontent

