February 16, 2019 t

ህብለ ሰረሰር በሌላቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኦዴፓ/ኢህአዴግ ተከቦል፣ የተጠመጠሙበት የፖለቲካ ፓርቲዎ አንዳችም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ ማቅረብ እስካሁን አልቻሉም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ተጠምደዋል፡፡ በየክልላዊ መንግሥቶች የህዝብ መፈናቀል፣ ሰላም ማጣት፣ ፍትህ መጎደል ቁብም አልሰጣቸው፡፡ በመላ ሀገሪቱ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ የመሣሪያ ዝውውር፣ የውጭ ምንዝሪ ገንዘብ ሽሽትን ከጉዳያቸው አልጣፉትም፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማዝገም፣ የግብር አለመሰብሰብ መቀነስ፣ የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆልን ኬሬዳሽ ብለውታል፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ ላሉ 30 ሚሊዮን ስራ አጥ ወጣቶች ሥራ የመፍጠር ፕሮጀክቶች ውጥን የለም፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ የመለመላቸው 7 ሚሊዮን መጅገሮች ካድሬዎች ሳይነቀሉ የኢኮኖሚ ለውጥ አይመጣም እንላለን፡፡ ሃገሪቱ ህወሓት/ኢህአዴግ በነደፈው የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም አሁንም እየተሰራበት ይገኛል፡፡ የቪዝን ኢትዮጵያ ምሁራን ያቀረቡት ጥናት ተቀባይነት አላገኘም፡፡
የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ፋይናንስ ዘርፍ፣{በአጠቃላይ ለሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ማስፈፃሚ በአምስት አመት ፕሮግራም ውስጥ 2.4 ትሪሊዩን ብር ይጠይቃል፡፡} {2.4 ትሪሊዩን ብር ወጪ ለመሸፈን በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የሚኖረው የአገር ውስጥ የገቢ አቅም 2.03 ትሪሊዩን ብር ነው፡፡ በመሆኑም የበጀት ጉድለቱ ዕርዳታን ጨምሮ 341.2 ቢሊዩን ብር ይሆናል የሚል ታሳቢ በረቂቅ እቅዱ ተይዞል፡፡} {}ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪ 119.5 ቢሊዩን ዶላር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 30 በመቶ ማለትም (35.85 ቢሊዩን ዶላር)፣ የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 41.7 በመቶ ማለትም (49.8315 ቢሊዩን ዶላር) ለሌሎች ዘርፎች ቀሪው (33.8185 ቢሊዩን ዶላር) እንደሆነ ይገመታል፡፡ የመንግስታዊ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ወጪ ዕቅድ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት መሠረት አስፈላጊ፣ የካፒታል ወጪ ሃገሪቱን ለማሳደግ ያስፈልጋል፤ ከሚያካትታቸው ውስጥ የተፈጥሮ መሰረተ-ልማት ግንባታ ለሰው ኃይል፣ለእቃዎችና ለአገልግሎት ዘርፍ መጎጎዣነትና ለገበያ ኢኮኖሚ የሚያስፈልጉ መንገዶች፣ባቡር መስመር መዘርጋት፣የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ኤሌትሪክ መስመርና ኤሌትሪክ ቆት ማከፋፈያ መዘርጋት፣ የውኃና የፍሳሽ አገልግሎት ወዘተ የመሳሰሉት ይካተታሉ፡፡ የአንደኛውና ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም ስኬቱና ድክመቱ ሳይጠና በይደር ቀጥሎል፡፡
የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግዳሮቶች፣ በተከሰተው የህዝብ አልገዛም ባይነትና ህዝባዊ አመጽና ተጋድሎ እቅዱ ሊጨናገፍ ችሎል፡፡ የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ችግሮች መኃል የሚከተሉት በጥናት ቀርበው ሰሚ ጆሮ አጥተዋል፡፡
{1} ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት (Foreign Direct Investment Inflows) በየክልሎቹ የተፈናቀሉ 3 ሚሊዮን ህዝቦች በአሉባት ሀገር በሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ መዋለ-ንዋያቸውን የሚያፈሱ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ማለትም ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ሰላም በሌለበት ሃገር የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም፣ እንዲያውም ያፈሰሱትን ምዋለንዋይ ሸጠው ለመውጣት ይገደዳሉ፡፡ በሃገራችን የኢኮኖሚ ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡ አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡
በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2008እኤአ (109 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2009እኤአ (211 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2010እኤአ (288 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2011እኤአ (627 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2012እኤአ (279 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2013እኤአ (1281 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2014እኤአ (2132 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2015እኤአ (2168 ቢሊዮን ዶላር)፣2016እኤአ (አልተገለጸም)፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ነበር፡፡በሃገሪቱ በተፈጠረው የሰላም መጣጣትና የህዝብ መፈናቀል ምክንያት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት በጣም ቀንሶል፣የግንባታ ሥራዎች ቀዝቅዘዋል፡፡
{2} ካፒታል ኩብለላ፣ ከሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚወጣ የውጪ ምንዛሪ ካፒታል ኩብለላ Capital flight ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር በአመት እንደሚደርስ የአፍሪካው ልጅ ታቡ ኢንቤኪ አጋልጠዋል፡፡ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ሪፖርት ከኢትዮጵያ በአስር አመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር መኮብለሉን ተጋልጦል፡፡ በአጠቃላይ በህወኃት/ኢህአዲግ መንግስት የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዝ ዕዳ 27 ቢሊዩን ዶላር በላይ ብድር እንዳለባቸው ዝርዝር ጥናቱ ያሳያል፣ ከዚህ ውስጥ 7 ቢሊዮን ዶላር እዳቸውን ከፍለዋል ብንል እንኮ ከ15 አስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባቸው፣ መንግስት ከ30 እስከ 35 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲደመር ሃገሪቱ በትንሹ 50 ቢሊዮን ዶላር እዳ አለባት እንላለን፡፡ አሁንም ከመቼውም ጊዜ በላይ የውጭ ምንዛሪ ኩብለላ እንዳለ በመንግሥታዊ መገናኛ ብዙሃን እየተስተጋባ ይገኛል፡፡ ዋና ተዋናዬቹ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህኢድን እና አጋሮቻቸው የተቀናበረ ፀረ ህዝብ ሥራ ነው እንላለን፡፡
{3} ብድርና የዕዳ ጫና፣ አይ ኤም ኤፍ በኢትዮጵያ የሚገኙ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ያለባቸውን እዳና የዕዳ ጫና ምን ያህል እንደሆነ ከመግለፅ ታቅቦል፡፡ በአጠቃላይ መንግሥትና ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ከባህር ማዶ ብድር እንዳይወስዱና ሃገሪቱ ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ Ethiopia were changed from moderate to “high risk of debt distress.” የኢትዮጵያ የዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶል መድረሱንና የዕዳ ጫናው ለከፍተኛ አደጋና ስጋት ሃገሪቱን ይዳርጋታል፣ ወደፊት እዳዋንም ለመክፈልም ከፍተኛ ዋጋ ይስከፍላታል ሪፖርቱ ብሎል፡፡ ከተለያዩ መረጃዎች በጥናት በተገኘው መሠረት ግን ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ያለባቸውን እዳ {3.1}የኢትዬጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ ከ 2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000, 000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር፣ {3.2}ኢትዬ ቴሌኮም፣በአጠቃላይ፣ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ጋር የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም ከኢትዩጵያ የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ እንደሚወራረድ ይታወቃል፡፡ {3.3} የኢትዬጵያ መብራት ኃይል ባለሥልጣን(5 ቢሊዩን 490 ሚሊዬን ዶላር ብድር እንዳለበት ጥናቱ ያሳያል፡፡) {3.4} የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን አጠቃላይ የግንባታ ስራ ወጭ 100 ቢሊዩን ብር (3.5) ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር) እንደሚሆን ሲገመት ማሽነሪዎች ለመግዛት ግማሹ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይሻል፡፡የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን 500 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከቻይና ልማታ ባንክ (China Development Bank Corp.) ጋር ተፈራረመ፡፡ {3.5} የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያለበት በአጠቃላይ ብድር 5 ቢሊዩን 4 ሚሊዩን ዶላር ብድር ሥራው ተጠናቆል፡፡ {3.6} የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ ግንባታ በአራት አቅጣጫዎች እየተገነባ ሲሆን፤በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡ ለግንባታው ወጭ 475 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን፣ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በብድር የተገኘ ሲሆን 15 በመቶው በኢትዩጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ በዚህም የዕዳ ጫና የተነሳ በ2010ዓ/ም ሁሉም የመንግሥት ተቆማት በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትዮቴሎኮም የመሳሰሉት የልማት ድርጅቶች የአጭር ጊዜ ብድሮችን ከመበደር እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ተስጥቶቸዋል፡፡ በዚህም የአገሪቱ የብድር ዕዳ ጫና ቀስ በቀስ እያደገ በመምጣቱ ሳቢያ፣ እንዲሁም አበዳሪዎችን እምነትም ላለማጣት ጭምር መንግሥት በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ብድሮችን በማቆረጥ በብድር ዕዳ ክፍያ ላይ ማተኮሩን መርጦል፡፡ በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ ከቻይና መንግሥት ከሚገኝ ጥቅል ኮንሴሽናል ብድር ውስጥ የዕርዳታ ምጣኔው ከፍ ተደረገላት፡፡ የቻይና መንግስት ከዚህ ቀደም የምትሰጠው ኮንሴሽናል የብድር ድጋፍ ሥሌት 27 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ሥሌት የኮንሴሽናል ብድር የድጋፍ ሥሌት 35 በመቶ ተደርጎል፡፡ ኮንሴሽናል ብድር ቀለል ያለ ወለድ የሚከፈልበት መሆኑን፣ በተራዘመ ጊዜ ተከፍሎ የሚያልቅና መጠነኛ ጫና ያለው የብድር ዓይነት ቢመስልም እስካልተከፈለ ነፃ ምሳ የለም፡፡
{4} የባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) የዶክተር አብይ መንግስት ዴሞክራሲን መብት እንዲያብብ በማድረግ፣ ስብዓዊ መብቶችን በማክበር፣የፕሬስ ነጻነት ሥራ ላይ በማዋል፣ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች አዲስ የሚያሰራ ህግ በማውጣት፣ የፖለቲካ እስረኞች በመፍታትና ከጎረቤት አገሮች ጋር የሰላም በመፍጠር መመሪያቸው ከአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥታት የልማት እርዳታ እንደሚያገኝ ተስፋ ተሰጥቶታል፣በመጠኑም ከተለያዮ አገራቶች ድጋፍ አግኝተዋል፡፡
ከ1991 እኤአ እስከ 2012 እኤአ ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በአመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ ከ2008 እስከ 2015እኤአ ያለውን ብቻ ብናይ ከ3 እስከ4 ቢሊዩን ዶላር ሃገራችን የልማት እርዳታ አግጥታለች፡፡ በኦዲኤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ አድራጊ መንግስቶችና ተቆማት አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኢንስቲቲዉሽኖች፣ ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስና ግሎባል ፈንድ ናቸው፡፡
{5} በኢትዮጵያ ከውጭ የተላከ ገንዘብ/ የውጭ ሐዋላ፣ ከአንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ የተዋጣው ከ1 እስ 2 ቢሊዮን ዶላር እያደር እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡ ዲያስፖራው ለወገኖቹ ደራሽ እንደሆኑ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ከ2000 እስከ 2015እኤአ በ2000 እኤአ 53 ሚሊዩን ዶለር የነበረው እያደገ መሄዱን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይፋ አድርረው ነበር፡፡ በግምት አንድ ሚሊዩን ከሚሆኑት ባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኛች በ2012 እኤአ 2.4 ቢሊዩን ዶለር ከውጭ ሐዋላ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ የብሄራዊ ባንክ ገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት ከባህር ማዶ ከሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወደ ሃገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ፣ ከሠንጠረዡ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ዝቅተኛ ከውጭ ሐዋላ የተገኘው ገቢ በ2001 እኤአ 18 ሚሊዩን ዶለር የነበረ ሲሆን ከፍተኛ 3 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር በ2013እኤአ እድረት እንዳሳየ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በ2015 እኤአ 4 ቢሊዩን ዶላር ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ ልከዋል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወገናቸውን በመርዳትና በማስተዳደር የሲሶ መንግስትነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ ሰለዚህም በሀገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ሊያገባቸውና ድምፃቸውም ሊሰማ ይገባል እንላለን፡፡
የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ መንደርደሪያ ሃሳብ
በሃገሪቱ የሠፈነው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የፓርቲዎች የንግድ የሞኖፖሊ ኢንፓየር የግሉ ዘርፍ ባለኃብት ስራን በመንጠቅ ኢኮኖሚውን በፓርቲዎች እዝ ኢኮኖሚ ጠርንፎ የያዘና የመሬት ኃብትን፣ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍና የኢፈርትና ሜቴክ፣ብአዴን ጥረት፣ኦህዴድ ዲንሾ እና ደህኢድን ወንዶየመሳሰሉ ልዮ ልዮ ንግዶች ወደ ግሉ ዘርፍ በአክሲዮን መሸጥ ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ በመቀጠል የህወሓት/ኢህአዴግ ስርአተ አገዛዝ ዘመን የተነደፈው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አፈፃፀም ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ውድቀት በአጭሩ እንቃኛለን፡፡ የብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር፣ የኦዴፓ/ኢህአዴግ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የክልል የፖለቲካ ፖሊሲዎች ተግዳራቶች በዋናነት የሚያጠነጥኑትና ከነሰንኮፋቸው ነቀላና ተከላ የሚሻቸው መሰረታዊ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦች ውስጥ፡-
{0} ለፋይናንስና የባንክ ዘርፍ፣ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፖሊስ በአፋጣኝ ማውጣት፣ ያሉት ባንኮች ከሙስና ወንጀለኞች ጋር ተባብረው እንደሰሩ በተለይ ከሜቴክ ጋር አብረው እንዳሴሩ እየታወቀ አሁንም በዘው ስራ ላይ መቆየታቸው ለሚሰተዋለው ጥገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያማይታይ እጃቸው አንድ ቀን ይታያችሆል እንላለን፡፡ በዘር የተዋቀሩ በባንክና የፋይናንሻል ዘርፍች ባንኮችና ኢንሹራንሶች መለኪያቸው በሙያ ክህሎትና የትምህርት ዕውቀት ላይ ብቻ በውድድርና በፈተና ስራ የሚገባባቸው ህብረ- ብሄር ተቆማት እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
{1} አንደኛ፣ ቌንቌ፣ ተኮር /ዘውግ ተኮር ፖለቲካዊ የክልል ፖሊሲ በብሔራዊ ኢኮኖሚያዊና መልከ-ምድራዊ /ጂኦግራፋያዊ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲን መተካት ይኖርበታል፡፡
{2} ሁለተኛ፣ የክልል ያልተማከለ የኢኮኖሚ እቅድ ስርአት መዘርጋት (Decentralized Planning Systems) በተማከለ ብሔራዊ የኢኮኖሚ እቅድ ሥርዓት (Centralized Planning Systems) ማስተሳሰርና ማቀናጀት ያስፈልጋል፡፡
{3} ሦስተኛ፣ በክልሎች ውስጥ የኃብት ክፍፍል ስርጭት አመዳደብ (Inter-Regional Allocation of Resources) ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ተቆጣጣሪነት፣ በግልፅነት፣ ፍትሃዊና ሚዛናዊ ማድረግ፡፡
{4} አራተኛ፣ ብሔራዊና ክልላዊ የመዋለ ንዋይ /ኢንቨስመንት ፖሊሲዎች በመንደፍ፣ ትስስርና ቅንጅት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
{5} አምስተኛ፣ የብሄራዊና ክልላዊ የስልጠናና እውቀት ክህሎቶች በመንደፍ አስፈላጊውን የሰው ኃይል ልማት ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ የትምህርት ፖሊሲውን ከዚህ አኮያ መቅረፅ፣ ትውልድ ገዳይ እውቀት አምካኝ የሆነውን የወያኔ የትምህርት ፖሊሲ በአፋጣኝ መቀየር፡፡ ለተገቢው የስልጣን እርከን የተማሩ ምሁራን መመደብ ያሻል፡፡
{6} ስድስተኛ አህጉራዊ፣ ብሔራዊና ክልላዊ የውሃ ተፋስስ ልማትና የግብርና እርሻ መስኖ ልማት እቅድ መንደፍ አስፈላጊ ነው፡፡
{7} ሰባተኛ፣ የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች (ቡና፣ ሠሊጥ፣ የቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ) አምራች ለሆኑ ክልሎች አስፈላጊውን የብሔራዊ መሠረተ-ልማቶች ግንባታ የመንገድ፣ የባቡር መሠመርና የዓየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች በቅድሚያ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች አምራች አካባቢዎች በማድረግና ምርቶቹን ወደ ወደቦችና ኤርፖርቶች በማጎጎዝ፣ በዓለም አቀፍ የውጭ ንግድ በመሸጥ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ) ገቢ ማግኘት የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘለቄታዊና ቀጣይነት የውጭ ምንዛሪ ገቢን አስፈላጊ ለሆኑ የምርት መገልገያ እቃዎች የካፒታል ጉድስ (ማሽነሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ትራክተሮች፣ ነዳጅ፣ ማዳበሪ ወዘተ)ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ብሄራዊ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መገንባት አማራጭ የለውም፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በማቆቆም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የኢኮኖሚ እቅድ በጋራ መንደፍ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡
{8} ስምንተኛ ለ30 ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ አጥነት ጥያቄዎች፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና ወገንን መታደግ ብቻ ነው ያለው አማራጭ፡፡ ይሄን በማድረግ ሃገራችንን ከውድቀት ማዳን እንችላለን፡፡ የፖለቲካ ብዱን ድጋፍ፣ ተሳትፎ በአድሎና በዘመድ ሥራ፣ በካድሬና ኮሚሳር በዘርና በፖለቲካ ድርጅቶች በአጋር ድርጅቶች እውቀት አልባ ምላስ አደሮች የተዋቀረው የኢትዮጵያን ቢሮክራሲ ለዘለቄታው መለወጥና ዘመናዊ አስተዳደር በኢትዮጵያ ካልተጀመረ ሃገሪቱ ልትወጣ በማትችለው ችግር በተለይ የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ከአመት አመት መጨመር ምክንያት አብዩት መፈንዳቱ አይቀሬ ነው፡፡ በዘመናዊ መንገድ የተዋቀረው በመልካም አስተዳዳር የዘመነው ቢሮክራሲ ማሽነሪና ዮኒቨርሲቲዎች በጥናትና የቢዝነስ ፕሮፖዛል በማቅረብ ዋነኛ ሥራዎች በትንሹ በዓመት ከሦስት እሰከ አምስት ሚሊዩን ወጣቶች ሥራ የሚያስገኝ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በማድረግ ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠርና የገቢ ምንጫቸውን በማሳደግ፣ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ሃገራቸውን የሚወዱ ሙስና የተጠየፉ በሥራ ባህል ብቻ ማደግ እንደሚቻል ለቀጣዮ ትውልድ የሚያስተምሩ ዜጎች መፍጠር መቻል ይኖርብናል እንላለን፡፡
{9} የሙያ ማህበራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተፅዕኖ ተላቀው በነፃ የመደራጀት መብታቸውን እውን ማድረግ ለህዝባዊ ድጋፍና ለአሳታፊ ዴሞክራሲ ህያውነት ፈረ ቀዳጅ በመሆኑ የመምህራን ማህበር፣ የሠራተኛ ማህበር፣ የሴቶች ማህበር፣ የወጣቶች ማህበር፣ የዮኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር፣ የጋዜጠኞች ማህበር፣ ወዘተ በዚህ አስር ወራት ውስጥ መደራጀት አለመቻላቸው አሳታፊ ዲሞክሲን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡ የኢሠመጉ የተወረሰ ገንዘብ እንዲመለስና በነፃነት በመላ አገሪቱ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡ የፕሬስ ነፃነት እንዲያብብም የመፅሄት፣ የጋዜጣ፣የመፅሃፍ የህትመት ዋጋ እንዲቀንስ መንንግስት አስፈላጊውን ድጎማ ማድረግ ይገባዋል፣ እንዲሁም የመንግስታዊ የፓርቲ የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጣቢያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ ማዛወር ለዴሞክራሲ ማበብና ለመሠረታዊ ለውጥ አንድ እርምጃ በር ከፋች ነው እንላለን፡፡ ከሚዛናዊ ሂስ ይለመድ፣ሃሳቡን በሃሳብነት ለሞመገት ለሚሹ ለአገራችን ጋዜጦችና ሚዲያዎች ፁሑፉን ለህዝብ የማካፈል የሙያ ግዴታችሁን ዛሬ እንኮ ተወጡ፣ ጭፍን ድጋፍና ጭፍን ጥላቻ የሃሳብ ልዕልና ፀር ነውና!!!
ሚዛናዊ ሂስ ያብብ!!