February 16, 2019

ወሓት ግን መቼ ነው የምትለወጠው፥ የምትማረው?

ከነገሠ ጉተማ

የህወሐት ገንዳ ፎቶ
“ያረጀን ውሻ አዲስ ዘይቤ ማስለመድ/ማስተማር አይቻልም”

ሁላችንም ህወሐት በለውጡ አምና ያለፈውን ጥፋትዋን ተቀብላ እንደ አንድ ቤተሰብ ወደፊት ብንራመድ እንመኛለን። እንደዚያ ቢሆን ኖሮ አንድ ትልቅ ችግር ተቃሎ ሌሎች ችግሮችን በአንድነት መፍታቱ ላይ ማተኮር በቻልን ነበር። የህወሐት “አሻፈረኝ” ማለት መታየት ያለበት ከቀየሰችው ጎዳና እና ለመተግበር ከምትፈልገው ራዕይ አንፃር ነው።

******

ህወሐት እንደ ድርጅት መቼም አትለወጥም – ምክንያቱም ለመተግበር የምትሞክረው ራዕይ የምትጓዝበትን መሥመር እንድትለወጥ አይፈቅድላትም። የሕወሐት መንገድ ለአንድ አቅጣጫ ጉዞ ብቻ የተሠራ ጠባብ መሥመር ነው። ከመስመሩም መውጣት አይቻልም። መሥመሯን የቀየሰችው ገና ስትፀነስ ነው። ሌሎች አማራጮችን የማየት ችሎታ ቢኖራትማ ኖሮ በ1966 ሕዝባዊ አብዮት ሲጀመር ጥያቄዎቿን ከሌላው ሕዝብ ጥያቄዎች ጋር አብራ መፍታት ይቻል ይሆናል ሳትል ለአብዮቱ ጀርባዋን ሰጥታ ወደ ደደቢት ተራራ ባላቀናች ነበር። አሁን ሌላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ርዕዮቷን እንደተለወጠች አስመስላ ለመቅረብ ብትሞክርም ከፅንሷ ከጀመረችውና ደደቢት ከገባችበት ዓላማዋ ንቅንቅ አላለችም። ይህም ዓላማ በኢትዮጵያውያን ላብና ደም የታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ መመሥረት ነው። ራዕይዋንም በ1968ቱ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት መግለጫ (TPLF Manifesto) ተንትና ከትባልናለች። ይህንንም መሥመሯን ስትቀይስ መጥፊያዋንም አብራው አዘጋጅታለች።

First TPLF Manifesto 1968 EC In amharic & tigrigna-1.pdf

 First TPLF Manifesto 1968 EC First TPLF Manifesto 1968EC In amharic & tigrigna-1.pdf  

ህወሐት መቼም አትማርም፡፡ ምክንያቱም የተዋቀረችው አዲስ ዕውቀት ለመማር ወይም አዲስ ዕውቀት ለመፍጠር ሳይሆን ከውስጡ በፊውዳላዊ ቂምና ቁርሾ የተለወሰ ከላይ ደግሞ በዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት የተለበጠ ርዕዮተ ዓለም ለማስፋፋት ነው። የዕውቀቷ መጠን ፈጣሪዎቿ ተብትበው የሰጧትን ዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት እንደመዝሙረ ዳዊት መሸምደድ ነው። ከዚያ ውጭ እንድታውቅ አይፈቀድላትም። አዲስ ዕውቀት መቅሰም ዓይኖቿ እውነታን እንዲያዩና ጆሮቿ እውነትን እንዲሰሙ ስለሚያደርግና ይህም ደግሞ በተራው በመተግበር ላይ ያለችውን የተሳሳተ ርዕዮት የትም እንደማያደርሳት ስለሚያሳያት እንደ ዓላማዋ እንቅፋት ታየዋለች። ለምሳሌ ሕዝቡን የሚያስቀድም እና መብታቸውን የሚያከብር እውነተኛ ዴሞክራሲ ሲነሳባት ያቅለሸልሻታል።

በተምሳሌት ስናየው ህወሐት ገንዳ ውስጥ እንደሚኖር ዓሳ ናት። ዓሳ ከገንዳው ውስጥ ቢወጣ መተንፈስ እንደማይችል ሁሉ ሕወሐትም ከገንዳዋ ብትወጣ መኖር አትችልም። የምታውቀው እዚያው ገንዳዋ ውስጥ በራሷ የቆሸሸ ፍሳሽ በተጨማለቀው ውኃና በተበከለው አየር መተራመስን ብቻ ነው። አዲስ ውኃና ንፅህ አየር አይስማማትም። ከሚከረፋው ገንዳዋ ውስጥ ሊያወጧት የሚሞክሩትን ሁሉ ጠላቶቿ ታደርጋቸዋለች። እንዲያውም ውኃውን ለመቀየርና አየሩንም ለማስተካከል ቢሞከር ታኮርፋለች፣ እንዳበደ ውሻ መናከስ ትጀምራለች፣ የፈሪ በትሯን ታምዘገዝጋለች። ያለችበት የከረፋ የገንዳ ሥርዓት ስለተዋሃዳትና ባሕሏም ስላደረገችው ክርፋቱም ተስማምቷታል። ሁለመናዋ ለበሰበሰው ውኃና ለከረፋው አየር ተስተካክሏል። አንዳንዴ ገንዳው በጣም ሲደፈርስና ሲጨልምባት “ተሐድሶ” በማለት ድፍርሱን ያጠራች እየመሰላት ባስመሳይ እርምጃዎች ትውገረገራለች። “ውኃ ቢወቅጡት እምቦጭ” እንዲሉ ከማይፀዳ የበሰበሰ ገንዳ ውስጥ ተሰብስባ መታደስ ያለፈውን መድገም እንጂ አዲስ ነገር እንደማያመጣ ማወቅ ተስኗት ነው የኖረቸው። ከዚያ ገንዳ ለመውጣት ከፈለገች የትም የማያደርሳትን የጠባቦች ራዕዮቷን መተውና አእምሮዋን ለአዲስ አውነታዎች መክፈት ይኖርባታል። ነገር ግን የራሷን የገንዳ ባሕል የፈጠረች የመንደርተኛ ጥርቅም ስለሆነች አዲስ ለውጥ ከመቀበል ይልቅ መጥፋቷን ትመርጣለች። መለወጥ ብትፈልግ ኖሮ ገንዳዋን ከነወጀለኞቿ ጠቅልላ እንደልማዷ ወደመንደሯ ባልሸሸችና አሁን በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ ባልተፍጨረጨረች ነበር።

REPORT THIS AD

ለህወሐት የተበከለው ውኃ ሕገመንግሥቷ፤ ቅርሻቷና ምናምንቴዋ ማኒፌስቶዋ፤ ገንዳዋ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነቷ ነው። ማኒፌስቶዋንም በሕገመንግሥት አብኩታ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ ለመወትፍ ስትሞክርና ሕዝቡ እምቢ ብሎ ሲያምፅ ወይም ህገ መንግስት ተብዬው በተሟላ መልኩ ይተግበር ስትባል፤ ግንፍል ትልና መገሰጫ ዱላዋ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት ይሆናል።

አሸባሪዎቹ የህወሓት መሪዎች በከረፋው ዴምክራሲያዊ ማዕከላዊ አምባገነንነት ገንዳቸው ውስጥ ተለውሰው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሙዋቸው ፋሺስታዊና ትዕቢታዊ ግፎች በታሪክ ተመዝግበው የሚኖሩ ጥቁር ነጥቦች ናቸው። ሕዝቡን ሳያማክሩት በራቸውን ዘግተው በአፓርታይድ ፖሊሲ ከፋፍለውት በድንበርና በሌሎች ዘረኛ ምክንያቶች እርስ በርስ አንዲጫረስ አድርገዋል፣ እያደረጉም ናቸው። ሕዝቡንም መከፋፈላቸው የሐገሪቷን ሃብቶች ያላንዳች ሐፍረት ለመዝረፍ አስችሏቸዋል። የኢትዮጵያውያንን ሰብዓዊ መብቶች ያላንዳች ቅሬታ ጥሰዋል። በጅምላ ገድለው በጅምላ ቀብረዋል። መግደል ያልቻሉትን ወንዶች አኮላሽተዋል፤ ሴቶችች ደፍረዋል፤ ግብረ ሰዶም ፈፀመዋል፣ እስረኞች ላይ ሽንታቸውን ሸንተዋል፤ ጥፍሮች ነቅለዋል፤ በኤሌክትሪክ አቃጥለዋል፤ የተቃዋሚ እስረኞችን ገላ እንደ ሲጋራ መተርኮሻ ተጠቅመውበታል፤ እግሮችና እጆች ቆርጠዋል፤ ዘቅዝቀው ገርፈዋል። በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቃቸውን ሰቆቃ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ፈፅመዋል። በገሐድ የተሠሩት እሥር ቤቶች አልበቃ ብሏቸው በድብቅ እሥር ቤቶች ውስጥ ብዙውን አሰቃይተዋል። ሜዳ ተወልደው ሜዳ አድገው የአንድን ሕዝብ አንድ ክፍል ብቻ “ነፃ ለማውጣት” የተዋጉና ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደጠላት ወይም እንደ መጠቀሚያ እንጂ እንደሐገራቸው አይተውት የማያውቁ የጫካ ልጆች ስለኢትዮጵያ ደሕነንትና ብልፅግና የማሰብ ውስጣዊ ልቦና የላቸውም። ስለዚህም የወረሩን ለኛ ለኢትዮጵያውያን አስበው አይደለም፤ የወረሩን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ነው። ይህን ሁሉ ነውር እና አሰቃቂ የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ፤ ሰብዓዊ መብትን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ሲጥሱ፤ ራሳቸው የፈተሉትን ሕገ መንግሥት አንቀጾች 18-24ን እየጣሱ ነው። ከሁሉም በላይ የሚያሰቅቀውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ስሜት እንደሌላቸው የሚያሳየው፤ ይህ ሁሉ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፋ ሲወጣና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያዝን፤ እነሱና ደጋፊዎቻቸው ግን ኢሰብዓዊ የግፍ ስቃይ የደረሰባቸውን ወገኖች “እሰይ! እንኳን ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት አገኙ” በማለት አረመኔነትን ሲደግፉ በሚዲያ አዘውትረው ተሰምተዋል፡ የትምክህተኛና የገዳይ ባህርያቸውን እያጋነኑ ደረት መንፋቱ የሕዝቡን ሰቆቃ ከመገንዘብ በልጦባቸው።

እነዚህ አረመኔዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት ግፍ የጀርመን ናዚዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በይሁዶችና በሌሎች ሕዝቦች ላይ ከፈፀሙት ግፍ የማያንስ ነው። ለምሳሌ በጀርመን አገር ውስጥ ቫይማር ሪፐብሊክ በሚባል ክፍል ቡከንቫልድ በሚባል ትልቁ ኮንሰንትሬሽን ካምፕ ውስጥ የታጨቁት ከአሥር ሺህ የማያንሱ ይሁዶችን፣ የጦር ምርከኞችን፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ የሐይማኖት ሰዎችን፣ ተራ ወንጀለኞችን፣ ሌሎችንም በመርዝ ጋዝ ከመፍጀታቸውም አልፎ በሕይወት እያሉ አካላታቸውን በመቆራረጥ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን (ኤክስፐሪመንቶችን) ካደረጉባቸው በኋላ በእሳት አጋይተዋቸዋል። ብዙዎቹንም በተለያዩ አረመኔያዊ ዘይቤዎች በመጠቀም ጥፍሮቻቸውን መንቀል፣ የአካላቸውን ክፍሎች መቁረጥ፣ ቆዳቸውን በሕይወት እያሉ መግፈፍ ዕለታዊ ተግባራቸው አድርገውት ነበር። እነዚህኑ ግፎች በሌሎች የኮንሰንትሬሽን ካምፖችም የሚሊዮን ሕዝብ ሕይወትን አጥፍቷል። ናዚዎች ይህን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈፀሙ የአርያን ዘር በላይነት መብት እንዳላቸው በማመነን ያን መብት የማስከበር ግዴታ እንዳለብቸው በማሰብም ጭምር ነው።

እነዚህ አረመኔዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት ግፍ የጀርመን ናዚዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በይሁዶችና በሌሎች ሕዝቦች ላይ ከፈፀሙት ግፍ የማያንስ ነው። ለምሳሌ በጀርመን አገር ውስጥ ቫይማር ሪፐብሊክ በሚባል ክፍል ቡከንቫልድ በሚባል ትልቁ ኮንሰንትሬሽን ካምፕ ውስጥ የታጨቁት ከአሥር ሺህ የማያንሱ ይሁዶችን፣ የጦር ምርከኞችን፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ የሐይማኖት ሰዎችን፣ ተራ ወንጀለኞችን፣ ሌሎችንም በመርዝ ጋዝ ከመፍጀታቸውም አልፎ በሕይወት እያሉ አካላታቸውን በመቆራረጥ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን (ኤክስፐሪመንቶችን) ካደረጉባቸው በኋላ በእሳት አጋይተዋቸዋል። ብዙዎቹንም በተለያዩ አረመኔያዊ ዘይቤዎች በመጠቀም ጥፍሮቻቸውን መንቀል፣ የአካላቸውን ክፍሎች መቁረጥ፣ ቆዳቸውን በሕይወት እያሉ መግፈፍ ዕለታዊ ተግባራቸው አድርገውት ነበር። እነዚህኑ ግፎች በሌሎች የኮንሰንትሬሽን ካምፖችም የሚሊዮን ሕዝብ ሕይወትን አጥፍቷል። ናዚዎች ይህን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈፀሙ የአርያን ዘር በላይነት መብት እንዳላቸው በማመነን ያን መብት የማስከበር ግዴታ እንዳለብቸው በማሰብም ጭምር ነው።

የህወሐት-ገንዳ-ፎቶ2

ታዲያ የኛው ሐገር አረመኔና ቀማኛ የሆነችው ህወሐት ከናዚዎች በምን ተለየች?

ወደፊት ለመራመድ መፍትሄው ፀሐይዋ የጠለቀችባትን ህወሐት ከነበሰበሰ ገንዳዋ ከትግራይ አገዛዝ አስወግዶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ነው። ለዚህም ከፍተኛ ሚና መጫወት ያለባቸው ትግራይ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሕዝብ፣ በተለይም ወጣቱ ናቸው።