የሶሊያና ሽመልስ የአቛም መግለጫ!

በርግጥ ሶልያና ዛሬም ከእንዲህ ያለው አቛማ ጋር ከሆነ የገለልተኛው ተቛም የምርጫ ቦርዱ ዋና አማካሪ ተደርጋ የተሾመችው ለምንገኝበት የተወሳሰበ ፖለቲካ የተጨማሪ ምስቅልቅል መንስዔ እንዳትሆን በሚል እፈራለሁ።
ተስፋ የማደርገው በ 2013 የተንፀባረቀውና ለተጨማሪ ለድርድርም ሆነ ውይይት በሩን የጠረቀመው እንዲህ ያለው የሶሊ አቛም ዛሬ ላይ ተስተካክሎ ሊሆን ይችላል የሚለውን በሳይንሳዊ አመክኖ ድርቅ የተመታውን የየዋህነት እምነቴን ነው።

ብርቱካም ሚዴቅሳ እና ሶልያና ሽመልስ
ጀዋር መጀመሪያ ኦሮሞነቴ! ማለቱ ችግር የለውም በማለት አቛሟን ፍርጥ አድርጋ የገለጠችው ሶሊ ለአቛሟ ምክንያታዊ ማረጋገጫነት ማወራረጃ ብላ ከኢትዮጵያዊነታቸው ይልቅ “”መጀመሪያ ጎጃሜነቴን — መጀመሪያ ጎንደሬነቴን ብለው የሚያስቀድሙ ወገኖች ባሉበት ሃገር ጀዋር መጀመሪያ ኦሮሞነቴን ቢል ምንድንነው ችግሩ”” ስትል ያቀረበችው ንፅፅር ግን rubbish ከሚለው አገላለፅ ውጭ ሌላ ሊከስተው የሚችል ቃል ፈልጌ አጥቸለታለሁ።
ጎጃም ወይንም ጎንደር የሚባል የቦታ ስም እንጅ የነገድ ስም እንደሌለ የማታውቅ ከሆነ እውነትም ሶሊ ምርጫ ቦርዱን የሚመጥን የማማከር ብቃት አላት ማለት ነው።
ጀዋር ተወልዶ ዕትብቱ የተቀበረበትን ባሌን ሊያወድስ ፈልጎ መጀመሪያ ባሌነቴን ብሎ በነበር እንዃ የሶሊን ማወራረጃ እሽ ይሁን በማለት መቀበል ይቻል ነበር። ጀዋር ግን ያለው መጀመሪያ ኦሮሞነቴን ነው።
ለነገሩ — ጀዋር መጀመሪያ ኦሮሞነቴን ማለቱን እኔም አልቃወም። እንዲያውም አመሰግነዋለሁ። መጀመሪያ አማራነቴን ለሚል እሳት ትውልድ መፈጠር ትንሽም ብትሆን አስተዋፅኦ አድጓል ብየ ስለማስብ። የሶሊ ጉዳይ ግን ይሄው እንደተፈራው ማወዛገቡን ጀመረ ማለት ነው።
ምንአልባት ጠቅላይ ሚንስትሩ “” እዝች አገር ላይ ሃያ የሚሆኑ ጠቃሚ ሴቶች ነበሩን። አስሩን ሚንስትር አደረግናቸው የተቀሩትን አስር ሴቶች ደግሞ የሰላምና እርቅ ኮሚሽን ውስጥ ከተትናቸው፡ ከነዚህ ሌላ ማግኘት አልቻልንም። ከአገኛችሁ እናተው ጨምሯቸው”” ብለው የተናገሩት ነገር እውነት ይሆን እንዴ?
እንደዛ ከሆነ የሶሊን አሿሿም ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ በሚለው ብሂላችን ሸብ አድጌው ባልፍ ደግ ነው ብየ አሰብኩ።
ሶሊያና ሽመልስ ወገንትኛ መሆኗን ከአሁን በፊት ነፌስ ቡክ ገጿ ስትለቃቸው የነበሩትን ጹፎች ከዚህ በታች ይመልከቱ!!



