ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
መስፍን ዓለማየሁ ማን ነው?

መስፍን ዓለማየሁ ከአባቱ ከ ብ/ጀኔራል ዓለማየሁ አድነውና ከእናቱ ከ ወ/ሮ ዘለቃ አለሙ ሓምሌ 8/1951 ዓ.ም ተወለደ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አዲስ አበባ ይገኝ በነበረውና ቅዱስ ዮሴፍ በመባል በሚታወቀው ት/ቤት ካጠናቀቀ በኋላ፤ በቀድሞው ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶም ይከታተል ነበር።
መስፍን ዓለማየሁ በኢሕአፓነት በመጠርጠር ሚያዝያ 24 /1970 ዓ.ም ወደ ቤቱ በመጓዝ ላይ ሳለ ፤ መኪናውን በማስቆም በደርግ ታጣቂ ሃይሎች በግፍ ከተገደለ በኋላ አስክከሬኑ መንገድ ላይ እንዲጣል ተደርጓል። በመጨረሻም ወላጆቹ ከብዙ ፍለጋ በኋላ አስከሬኑን ከብዙ ሬሳዎች መካከል ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በማውጣት የቀብር ስነ ስርአቱን ሊያስፈፅሙለት በቅተዋል።
ይሄንን አረመኔ ፋሺስት ደርግ ነው ያሁኖቹ የድል አጥቢያ አርበኞችና የወያኔ አጋፋሪዎች አገርወዳድ የሚሉን!!
መስፍን ዓለማየሁ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!