አሜሪካኖቹ የወያኔ አገዛዝ ችግር ላይ እንደወደቀ ከተገነዘቡ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኦሮሞ መንግሥት ለማስቀመጥ እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸውን ከተገነበዘብን ቆይተናል፡፡
ወያኔም ከአሜሪካ ጋር የተባባለውን እንጃ ከዓመታት በፊት ጀምሮ “ለጋላ ሰጥቸልህ ነው የምሔደው!” እያለ ሲዝትብን ነበር፡፡
አሜሪካኖች ይሄንን ዓላማቸውን ለማሳለጥም ዞን ዘጠኝ የሚል የጽንፈኛ ኦሮሞ ንቅናቄ ደጋፊ የሆኑ የወጣቶች ንቅናቄን ፈጥረው ሲያንቀሳቅሷቸው ቆይተዋል፡፡
አሁን ነገርየውን መስመር ያስያዙት ይመስላል፡፡ አሜሪካኖች ከወያኔ ጋር ተደራድረው ሕወሓት ሥልጣኑን ለኦሕዴድ እንዲያስረክብና ተደጋግፈው እንዲሠሩ፣ ኦሕዴድም እነ ኦነግንና ሌሎች የኦሮሞ ጽንፈኛ የኦሮሞ ድርጅቶችን ይዞ አካቶ ወይም ተዋሕዶ እንዲሠራ አስማምተዋቸው በዚህ መሠረት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡
በዚህ መሠረትም መጭውን ምርጫ በሚፈልጉት መልኩ ለማጭበርበር እንዲመች በዘር ፖለቲካ ተጠልፋ የወደቀችውንና በአሜሪካኖች አብራ እንድትሠራ ተነግሯት ለተቀባይነቷ የቀደመ ስሟን በመጠቀም የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበርነት ወ/ሮ ብርቱካን ሚዴቅሳን ሾሙ፡፡
ታስታውሱ እንደሆነ ወ/ሮ ብርቱካን ሚዴቅሳ በሊቀመንበርነት የተሾመች ዕለት ከሹመት ሥነሥርዓቱ እንደወጣች ከዞን ዘጠኟና የጃዋር ቀንደኛ ደጋፊ ከሆነችዋ ሶልያና ሽመልስ ጋር ደስታቸውን ለመግለጥ ተቃቅፈው የተነሡትን ፎቶ ለጥፌ ይህች የዞን ዘጠኟ ሶልያና ሽመልስ የጃዋር ቀንደኛ ደጋፊ መሆኗን ገልጨ “ብርቱካን ሚዴቅሳ ይችን ልጅ የቅርብና የልብ ጓደኛ አድርጋ መያዟ በዘር ፖለቲካ በመጠለፏ ምክንያት ሊሆን ይችላልና ብርቱካን ተሾመችልን እያላቹህ መፈንጠዛቹህን በልክ ብታደርጉት መልካም ነው!” ብየ ነበረ፡፡
ይሄው አሁን ደግሞ ይህችውን የዞን ዘጠኟን የጃዋር ቀንደኛ ደጋፊ ሶልያና ሽመልስን አሜሪካኖች የብርቱካን አማካሪ አድርገው ሾመዋታል፡፡ መጭው ምርጫም በሚገባ የኦነግ ቅርጫ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ያያያዝኩት ፎቶ የዞን ዘጠኝ አባላት ሶልያና እና ናትናኤል ከአሜሪካ ፕሬዘዳንትና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጋር የተነሡትን ፎቶ ነው፡፡
እነኝህ ብቻ እንዳይመስሏቹህ እነ ዐቢይ “ይቀየራሉ!” የተባሉት ቀደም ሲል የተደረጉትን ምርጫዎች ሲያጭበረብሩ የቆዩ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በሙሉ በራሳቸው ሰዎች ለመቀየር አዘጋጅተው አስቀምጠዋል፡፡ “ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል!” አለ ያገሬ ሰው!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በባዶ ወሬ እየተደለለ በዓይኑ የሚያየውንና እየሆነ ያለውን ማስተዋል፣ መረዳት፣ መገንዘብ ጨርሶ አልቻለም!!! በተለይ የአማራው መጃጃልና እንቅልፍ እጅግ እጅግ እጅግ ይገርመኛል!!! አማራ እንዳይነቃ ቅጥረኛው ብአዴን ማዘናጊያ አብንን ፈጥሮ በደንብ አድርጎ ሠርቶለታል!!!
እኔም እላለሁ “ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!” እንደተባለው የራስህ ጉዳይ!!! ስትፈልግ ለምን አራት እግርህን አትነቅልም!!!!…… ሳይመሽ እንድትነቃ እሪሪ….ሪ! እያልኩ ደጋግሜ ጮኼያለሁ ነግሬሀለሁ!!!
አምሳሉ