ወይ ሞት! ወይ መደፈር! ወይ መዋረድ! ወይ መታመም! ወይ በቁም መቀበር!!!

በቀደም እሮብ ዕለት ምሽት የአማራ ቴሌቪዥን በአረመኔዎቹ በግፈኞቹ ወያኔ/ኢሕአዴጎች አረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ (ቶርቸር) የተፈጸመባቸውን ወገኖች አቅርቦ ነበር፡፡ ሊንኩ (ይዙ) ከታች ተቀምጧል፡፡

ዓለም ላይ በአረመኔዎች በግፈኞች ከተፈጸሙ የሰቆቃና (የቶርቸርና) የግፍ ዓይነቶች በአማራ ላይ ያልተፈጸመ የሰቆቃና የግፍ ዓይነት አንድ እንኳ አለ ወይ??? ይልቁንም በእኛ ላይ የተፈጸመ በሌላ ላይ ያልተፈጸመ ሰቆቃ (ቶርቸር) እና ግፍ ሊኖር ካልቻለ በስተቀር!!!

እነኝህ ትናንት በአማራ ቴሌቪዥን (ምርዓየ ሁነት) የቀረቡት አሰቃቂ ግፍና ሰቆቃ የተፈጸመባቸው ጥቂቶችና ከሞት ተርፈው ለምስክርነት የበቁ ወገኖች ናቸው፡፡ ወያኔ የአማራን ዘር ለማጥፋት ባለው ሰይጣናዊ ዓላማ ምክንያት በዚህ 27/28 ዓመት ውስጥ አማራ ታስቦበት በአቅድ በመመራት ከመላ ሀገሪቱ በሚሊዮኖች (በአእላፋት) የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በየስፍራው በየጫካው እንደ በግ እየታረዱ ተጥለው፣ ከነነፍሳቸው ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ተወርውረው፣ ጎጇቸው ተዘግቶባቸው እላያቸው ላይ እሳት ተለቆባቸው ተቃጥለው አመድ እንዲሆኑ ተደርጎ፣ በመርዝ እየተመረዙ ተሰቃይተው እንዲያልቁ ተደርጎ፣ ትግራይ ውስጥ ባዶ ስድስት በሚባሉ የማሰቃያ እስር ቤቶች ታጉረው ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው፣ እንዲደኸዩ እንዲቆረቁዙ ያጡ የነጡ ድሀ ሆነው በችጋር ተጠብሰው እንዲያልቁ ተደርጎእና በመሰል አረመኔያዊ ዘር የማጥፊያ ጥቃቶች አማራው እንዲያልቅ ተደርጓል!!!

እነኝህ ግፈኞች ከወያኔ ጋር አብረው ይሄንን ሁሉ ግፍ መፈጸማቸውና እንዲፈጸምብን ማድረጋቸው ሳያንስ ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ምርዓየ ሁነት) እንዳያቹህት ትናንትናም በአማራ ቴሌቪዥን በተላለፈውም እንዳያቹህት እነኝህ አረመኔዎች አንደበት ሊገልጸው የማይችለውን አረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ እስኪበቃቸው የፈጸሙባቸውን ወገኖቻችንን አሁን እንደገና ደግሞ እነኝህን የግፍ ሰለባዎችን ይቅር ብያለሁ በል! ቂም አልያዝኩም በል!” እያሉ በተጎዳ፣ በቆሰለ፣ ስንት ነገር ችሎ በተቀመጠ ጭንቅላታቸው ላይ ሌላ ተጨማሪ የሥነልቡና ጉዳት እያደረሱባቸውና በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደዱባቸው ይገኛሉ፡፡ እንኳን እነሡ የአረመኔያዊ የግፍና ሰቆቃ ሰለባዎቹ እኔ እንኳ የፈለገ ነገር ቢመጣ በምንም ተአምር ቢሆን ወያኔንና ቅጥረኞቹን ይቅር አልልም!!!!!!!…..

እነኝህ ግፈኞቹ ብቻ አይደሉም የግፍ ሰለባውን ሕዝብ ይቅር ብያለሁ ቂም አልያዝኩም በል!” እያሉ እያስጨነቁ ያሉት፡፡ አድር ባይ ቅጥረኛ ሆኖ አብሮ ሲያገበግብ የኖረው ምኑም ያልተነካ ሕሊናቢስ አጋሰሱ ሁሉ ነው በየመድረኩ ለአንደበቱ እንኳ ጥቂትም ሳይከብደው የተሰደበን ሰው ይቅር በል!” የሚሉትን ያህል እንኳ ለነገሩ ክብደት ሳይሰጡ እየተነሡ ይቅር ብያለሁ በሉ፣ ቂም አልያዝኩም በሉ!” እያሉ የሚገኙት፡፡

አማራ ሆይ! ይሄንን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ያደረሱብህን ወያኔንም ሆነ ቅጥረኞቹን ይቅር ብያለሁ በሉ፣ ቂም አልያዝኩም በሉ!” እያሉ በነፍስ በሥጋህ ሊቀልዱብህ የሚፈልጉትን ምናቸውም ተነክቶ የማያውቅ የአድርባይ፣ የቅጥረኛና የአስመሳይ መንጋ ቢመጣብህ ቀንደኛ ጠላትህ ነውና ድፋው!!!

ሁሉም ነገር ሥርዓት አለው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ፍትሕ መፈጸም አለበት፣ የሕግ የበላይነት መረጋገጥ አለበት!!! ይሄ ሳይፈጸምና በዳይ ግፍ ፈጻሚ አረመኔ ይቅር በሉኝ?” ሳይል፣ የበደለውን ሳይክስ፣ የቀማውን ሳይመልስ፣ ሳይጸጸት፣ ሳይታረም ጭራሽ እንዲያውም አሁንም በዚያው በግፍ ተግባሩ ላይ ባለበት ሁኔታ ይቅር በሉ! ቂም አትያዙ!” ብሎ ማለት በግፍ ሰለባዎች ላይ ከባድ የሥነልቡና ጥቃት መፈጸም ነው፣ በግፍ ላይ ግፍ ማድረስ ነው ይሄም እራሱን የቻለ ሌላ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ደረጃ እየተቀለደም ዕርቅ ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከላይ የገለጽኩት ቅድመ ሁኔታ ሳይፈጸም ዕርቅና ይቅር ማለት ሊኖር አይችልም፡፡ በደቡብ አፍሪካም ሆነ በሩዋንዳ ዕርቅ የተፈጸመውና ይቅር የተባባሉት ፍትሕ ከተፈጸመና የሕግ የበላይነት ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ገዥ ሕጎች በሰብእና ላይ ወንጀል የፈጸመ (Crime against humanity) እና የሰብአዊ መብት ጥሰትን (human rights violation) የፈጸሙ ይቅር ሊባሉና ምሕረት ሊደረግላቸው አይችሉም!” ይላልና በደቡብ አፍሪካም ሆነ በሩዋንዳ ዕርቅና ይቅር መባባሉ የተፈጸመው በዚህ ማዕቀፍ ነው፡፡ እዚህ ሀገራችንም በዚሁ መልክ ነው መፈጸም ያለበት፡፡ የራሱ የወያኔ ሕገመንግሥትም ከላይ የጠቀስኩትን ወንጀል የፈጸመ ሰው ይቅርታና ምሕረት እንደማይደረግለት ደንግጓልና፡፡

ምን ይገርመኛል መሰላቹህ ወያኔ/ኢሕአዴግን የውሸትም ቢሆን አጥፍቻለሁ ተለውጫለሁ!” እንዲል ያደረገው የሕዝቡ ማምረርና በቃኝ ብሎ ፍርሐቱን ገድሎና ሞትን መፍራት ትቶ በመውጣት እየሞተ ሰቆቃ እየተፈጸመበትም ጨክኖ መነሣቱ ሆኖ ሳለ እነሱ ግን ልክ ከፊሎቹ ወያኔ/ኢሕአዴጎች በሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍና ሰቆቃ አንገሽግሿቸው በተቀሩት ወያኔ/ኢሕአዴጎች ላይ ተነሥተው በመገልበጥ የሥርዓት ለውጥ ያመጡ ይመስል የተፈጸመውን ግፍ በጥቂቱም ቢሆን ማሳየታቸው ይገርመኛል፡፡ ለነገሩ ይሄንን ካላደረጉ እንዴት ብለው ተለወጥን የሚሉትን እየተወኑ ያስመስሉ ታዲያ???

ሕዝቡ የመጨረሻ ባያመር ኖሮ እንደአሁኑ ተገደው በማስመሰል በመሸንገል የማጃጃልን አዲስ ዘይቤን መያዝ ትተው ሁሉንም ነገር በኃይል ለማረቅ ለመጨረስ የሚጥሩበትን የቀደመውን ዘይቤያቸውን እንደያዙ አረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ እየፈጸሙ መቀጠላቸው ይቀር ነበር ወይ???

አሁንም ቢሆን ሕዝብ ነቅቶ እምብኝ አልጃጃልም!” የማለት አዝማሚያ እያሳየ በመሆኑ እምብኝ አልጃጃልም ካልክ ይሄንን የሰቆቃ ዘመን እንመልስብሀለን!” ብለው ለማስፈራራት እነኝህን የአረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ ሰለባዎችን አሳዩን እንጅ ተጸጽተውና እውነቱ እንዲታወቅ ፈልገው እንዳልሆነ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡

የምር ከልብ ተጸጽተውና እውነቱ እንዲታወቅ ከመፈለግ ቢሆን ኖሮ፦

1. በአባሪ ተባባሪነት ይሄንን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ለዘመናት ከፈጸሙ በኋላ አሁንም በሥልጣን ላይ ለመቀጠል ሕሊናቸው ባልፈቀደላቸው፣ የሞራል ዝግጅቱም ባልኖራቸው ነበር፡፡

2. የአረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ ሰለባዎች ተገቢውን ፍትሕና ካሳ እንዲያገኙ ባደረጉ ነበር፡፡

3. ሕዝቡ አሁንም በየስፍራው ሌላ ግፍ ሲፈጸምበት በቸልተኝነት ባልተመለከቱ ነበር፡፡

4. ለውጥ የሚሉት ነገር ተጨባጭና መሬት የያዘ ይሆን ነበር፡፡

5. ወገን በየቦታው ግፍ ተፈጽሞበት ተፈናቅሎ ከሞት ተርፎ ሲመጣና አቤት ሲል በወገናዊ የተቆርቋሪነት ስሜት ተቀብለው ለመርዳትና ችግራቸውን ለመቅረፍ ሲረባረቡ ይታዩ ነበር እንጅ እያባረሩ መልሰው ወደሞት ባልላኳቸው ነበር፡፡

6. የአረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ ሰለባ ወገኖቻችንን ይቅር በል! ቂም አትያዝ!” እያሉ ከደረሰበት ጥቃት በላይ እንደገና ደግሞ ሰብእናውን ከውስጡ ለመግገል፣ ወንድነቱን ለመስለብ፣ አእምሮውን ለማኮላሸት ለማፍዘዝ ለማደንዘዝ ጥረት ባላደረጉ ነበር፡፡

7. ይሄንን ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በአባሪ ተባባሪነት ከወያኔ ጋር የፈጸሙ በየደረጃው ያሉ የኢሕአዴግ አመራሮች አሁንም በሥልጣን ላይ እንዲገኙ ባልተደረገ ነበር፡፡

እናም እነኝህ ነጥቦች የሚያረጋግጡት ሀቅ ቢኖር ነገሩ ሁሉ ጨዋታ ቀልድ ድራማ (ትውንተ ሁነት) መሆኑን ነውና ወገን ሆይ ቶሎ ነቅተህ ወያኔ/ኢሕአዴግ የማጃጃያ ዘዴው ሁሉ አልቆበት፣ አንተም በመሀሉ ነቅተህበት ወደቀደመው የግፍ ዘመን ሳይመለስብህ በፊት ቅደመውና ቅበረው!!!

ወያኔ/ኢሕአዴግ እስካለ ጊዜ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ ሰላም፣ ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነት፣ ነጻነት፣ ዕኩልነት፣ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ይኖራል ብለህ ተስፋ እንዳታደርግ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ቅዠት ነው፡፡ እነኝህ ነገሮች ሊመጡ የሚችሉት በወያኔ/ኢሕአዴግ መቃብር ላይ ብቻ ነው!!!

https://youtu.be/NkUJr3x3mMQ

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com