February 20, 2019t

የለውጥ አራማጅ፣ የምስራቅ አፍሪካ መሐንዲስ፣ ከእግዚያብሔር ለኢትዮጵያ የተላከ ነቢይ ምንትሴ እየተባለ ሲሞካሽ የከረመው ዐቢይ አሕመድ በዛሬ እለት ሲያጭበረብርበት የነበረውን ጭንብሉን አውልቆ ራቁቱን ተከስቷል። ሲምሉበት የሰነበቱት ምዕመኖቹ ግን ስለእውነት አሳዝነውኛል። የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብላ አንጋጣ ስትከተል እንደዋለችው ሞኟ ቀበሮ መስለው ታዩኝ። አጭበርባሪው ዐቢይ እንደዚህ ባጭሩ ጊዜ ውስጥ ተገጥሎ ኩም ያደርጋቸዋል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።
ዐቢይ አሕመድ የአኖሌ ሐውልት እንዲቆም ዋናው ሐሳብ አመንጪውና የሐውልቱ አስገንቢ ኮሚቴ ሰብባሳቢ እንደነብርና ባለፈው ዓመት በቴሌቭዥን የቀረበውን እጅግ ዘግናኝ የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ረቅቅ አዋጅ ያዘጋጀው እሱ ራሱ መሆኑን ስንነግራቸው ያልሰሙ ወገኖቻችን በአፉ የሚደሰኩረው ሁሉ የልቡን መስሏቸው በአጭበርባሪው ነጋዴ ሲታለሉ ከርመዋል፤ ገንዘባቸውን ጭምር ተበልተዋል።
ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የዘር ድርጅት ኦሕዴድ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫው የጎሳ ፌዴራሊዝሙ የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ነው ብሏል።
ኦሕዴድን የለውጥ ኃይል አድርገው ሕወሓትን ሲያወግዙ የከረሙ ሰዎች ዛሬ ላይ በሁለቱ ድርጅቶች አላማ መካከል ምንም ልዩነት እንደሌለ ካልተገለጸላቸ “በምንሊክ ዘመን የደነቆረ ሁሌም ጎበና ይሙት ይላል!” እንደተባለው ደንቁረዋል ማለት ነው።
ሁለቱ የዘር ድርጅቶችን አንድነት ለማሳየት በዚህ ትናንትና ሁለቱም ድርጅቶች ካወጡ መግለጫ አስረጂ ላቅርብ፤
የርዕዮት ዓለም ወንድሙ ሕወሓት ትናንትና ባወጣው መግለጫው፤
«ሕገ መንግስቱንና ፌዴራላዊ ስርአቱን ለመናድ የሚደረገውን ሽለላና ተንኮል ፍፁም ተቀባይነት የለዉም ብቻ ሳይሆን፣ የትግራይ ህዝብና ህወሓት በዚህ ጉዳይ ፍፁም እንደማይደራደሩ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።» ሲል ተናግሯል።
የዐቢይ አሕመድ ፓርቲ የሆነው ኦሕዴድ ደግሞ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫው፤
«በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ እናስታውቃለን፤ . . . የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ ጉዳይ ነው።» ብሏል።
ሁለቱ ድርጅቶች ለስሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው። ፖለቲካ ድርድር፤ ሰጥቶ መቀበል ይጠይቃል። የኛዎቹ የቀድሞውና የአሁኑ ገዢዎቻችን ግን ከአፈጣጠራቸው ጀመሮ ዲሞክራሲን፣ ፖለቲካንና ሀሳብን ለመቅበር የተፈጠሩ ፋሽስታዊ አምባገነኖች ስለሆኑ ድርድር ብሎ ነገር በመቃብራችን ላይ ነው ይሉናል። ድርድር በመቃብሬ ላይ ነው የሚለው ዐቢይ አሕመድ ነው እንግዲህ ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲ ያሸጋግራል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት!
ሲጀመር ጀምሮ እንዳልነው በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለው የመግለጫ ልዩነት አንዱ የኦሮሞ ሌላኛው የትግሬ ድርጅቶች መሆናቸው ብቻ ነው። ይህን እያዩ ሕወሓትን አውግዞ ኦሕዴድን ለማሞገስ መሞከር ግብዝነት ብቻ ነው። ሁለቱም ጸረ ሰብ፣ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ዲሞክራሲ የሆኑ ዘንዶዎች ናቸው።
ወጥር አማራ! ያለህ አማራጭ ሁለት ብቻ ነው! አንድም በከሰሩና ራሳቸውን የአንድነት ኃይል ብለው በሚጠሩ ግን ባልሆኑ ደላሎች እየደነዘዝህ በዘንዶዎች እየተበላህ ማለቅ አልያም አምርረህ በመወጠር ኅልውናህን በተባበረ ተጋድልህ ማረጋገጥ! በዘንዶዎቹ እየተበሉ ላለማለቅ ደግሞ ያለህ የመዳኛ መንገድ ማርቲ ሉተር ኪንግ እንዳለው መብረር ካልቻልክ ሩጥ። መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፤ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ፤ ብቻ ምንም ቢሆን በያዝከው መንገድ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ! አበቃ!275SHARES
