February 19, 2019
ሕብር ሬዲዮ
ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅት የሚያደርገው ሕወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል በኮረም በዛሬው እለት ተጨማሪ ሰባት ሺህ ልዩ ሀይሎችን አምጥቶ ማስፈሩን የራያ የማንነት ተከታታይ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ደጀኔ አሰፋ Dejene Assefa መንግስት ይስማ ሲል ጥሪ አቀረበ።

የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር(ትህነግ) ከዚህ ቀደም በኮረም ወረዳ ስንደዶ በር አካባቢ ካምፕ እያዘጋጀ እንደነበር ሲገልጽ መቆየቱን ያስታወሰው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ በማሰብ መንግስት ይስማው ሲል መረጃውን ይፋ አድርጉዋል።
የትግራይ ነጻ አውጭ ዛሬ የካቲት 12 ቀን።2011 ዓ.ም. 7000 ተጨማሪ ልዩ ሃይል ሰንደዶ በር አካባቢ ባዘጋጀው የድሮው አውራ ጎዳና ካምፕ ውስጥ ማስፈሩን ጠቅሱዋል።
“…ነገሮች ወደ ፍፃሜያቸው እየተቃረቡ ይመስላል” ሲል አስተያየቱን የሰጠው አቶ ደጀኔ አሰፋ የሕወሓትን የጦርነት ዝግጅት መቃረብን እግረ መንገዱን ጠቁሟል።
በሕብር ሬዲዮ በዜና ዘገባችን ትላንት የሕወሓት የጦርነት ዝግጅት እየተጠናከር መጥቱዋል በራያ ወይ በወልቃይት በኩል ሰበብ ፈጥሮ ግጭት ሊያስነሳ ይችላል የሚል ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
የሕወሓት ባለፈው ሳምንት የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ አስተዳስደር በይፋ ተቃውሞውን ከማጠናከር አልፎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኔ ይቁም ሲል የክተት ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም።
ሕወሓት የተመሰረተበትን 44ተኛ ዓመት ሽፋን አድርጎ የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶችን ሲያቀርብ ወጣቶችና ህጻናትን ጭምር መሳሪያ አሳቅፎ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ ሰንብቱዋል።በክልሉ የመከላከያ።እንቅስቃሴ።በተቃውሞ መገታታቱ አይዘነጋም።
