February 19, 2019392SHARESShareTweet

የኢትዮጵያ ህገ-መንግስትና የፌደራል ስርዓት የኢትዮጵያ ህዝብ የመከረበትና ይጠቅመኛል ብሎ ያጸደቀው አይደለም፡፡ ህወሓት ሀገሪቱን በወረሃ ግንቦት1983ዓ.ም እንደተቆጣጠረ ቀደም ሲል ደረግ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር ሲዋጋ ዳናው ተሰምቶ የማይታወቀው ኦነግ ከኤርትራ ተስፈንጥሮ አዲስ አበባ ገባ፡፡ በዚህም ኢትተጵያም በሶስት ክፉ ጠላቶች ስር ወደቀች፡- ህወሓት፣ ሻእቢያና ኦነግ፡፡ በዚህ ወቅት ኢትየጵያን ወደ ሞት ከሚወስዷት አውሬዎች የሚከላከል ሌላ ሃይል አልነበራትም፡፡ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያንም እንደተለመደው አዲስ ኃይል ሲመጣ መጨብጨቡን ቀጠሉበት፡፡

ሦስቱ አውሬዎች ኢትዮጰያን ለማጥፋት የነደፉት የጥፋት ስልት በዘር ላይ የተመሠረት የፌደራል ሥርዓት መመሠረትና ለዚህም ግብዓት የሚሆን ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ ህገ-መንግስት መቅረጽ ነበር፡፡ የጸረ-ኢትዮጵያው ህገ መንግስት ዋና ግቡ ለኢትዮጵያ ህልውና መሠረት የሆኑ ነገሮችን በሙሉ መደምሰስ ነበር/ነውም፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያን ከስር መሠረቷ ለማናጋት ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ተቀመሙ፡፡ ብሄረን ከብሄር በቋሚነት የሚያጋጭ የጎጥ አስተዳደር፣ ሁለተኛ ለኢትዮጵያ አንድነት ከፍተኛ አስተዋፆ አለው የሚሉትን ቡድን በሁሉም መስክ ማዳከምና ሶስተኛው ለኢትዮጵያ አንድነት አስተዋጾ የሚያደርጉ እሳቤዎችን/እምነቶችን ማጥፋት ናቸው፡፡

የቋንቋ/ዘር-ፌደራሊዝም፡-ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ብሄር ሳይገድባቸው እጅግ የተደበላለቁ በመሆኑ የዘር-ፌደራሊዝም የሚመጥናቸው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ተገደው በቋንቋ እንደ ዳቦ ተከፋፈሉ፡፡ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ዋና ግባቸው ኢትዮጵያዊነትንና ለኢትዮጳያ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል የሚሉትን ኃይል መግደል በመሆኑ ቋንቋን እንደመስፈርት እዚህ ላይ አይጠቀሙም፤ የተጠቀሙትና የሚጠቀሙት ኃይል ነው፡፡ የወልቃይት፤የራያና የሸዋ አማራን ጉዳይ በምሳሌት መውሰድ ይቻላል፡፡

በዚህ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ከ1984ዓ.ም ከበደኖና አርባ ጉጉ የአማሮች ጭፋጨፋ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድርስ ለሩብ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ እየተገዳደሉ ይገኛሉ፡፡ ብሄረን መሠረት ያደርገ ከቀየ መፈናቀል፤ መገድል ንብረትና ሀብትን መዘረፍ የኢትዮጵያውያን የሩብ ክብለ ዘመን ቋሚ ክስተት ሆኗል፡፡ የቋንቋ ፌደራዝም እስካለ ድርስ ይህ ክፉ ድርጊት ይቀጥላል ምን አልባትም ለኢትዮጵያ ህልውና ማክተም ዋና ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ሁለተኛው ኢትዮጵያን የመግደያ ስልት ለኢትዮጵያ ደህንነት አስተዋፆ የሚያደርጉ እሳቤዎችን/እምነቶችን ማደከም ነበር/ነው፡፡ በዚህ በኩል ለጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ዋና ጠላት ሆና የተገኘችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ናት፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት ኦርቶዶክስን እንደ ኳስ ሲጫወትባት የኖረው፡፡ አሁንም እንዚህ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች የቤተ ክርስቲያን መዋቅሩንና ኃይማቱን ከማናጋት አልፈው ቤተክርስቲያናትን እያቃጠሉ የሚገኙት፡፡

ሦስተኛው ለኢትዮጵያ አንድነት ከፍተኛ አስተዋፆ አለው የሚሉተን ቡድን በጭክነት ማጥቃት ነው፡፡ በዚህ በኩል ዋና ኢላማ የሆነው አማራ ነው፡፡ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች አማራን አቅም አልባ/ሽባ ለማድረግ የተጠቀሙበትና የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ብዙ ናቸው፡፡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳይሆን የህዝብ ቁጥር መቀነስ፤ ጸረ-አማራ የሆኑ ቡድኖች ክልሉን እንዲመሩ መመደብ፤ በተለያዩ የፈደራል መስሪያቤቶች ተገቢውን ውክልና እንዳያገኝ መከልከልና በዋናት የአማራን ታሪካዊ ረዕስቶች መከፋፈል ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የአማራን ታሪካዊ ርዕስቶች ያልተከፋፈለ ክልል አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በዋናነት ግን የአማራ ዕርስቶች የተከፋፈሉት ህወሃትና ኦነግ ናቸው፡፡ህወሓት ከትግራይ የራቀውን የአማራ ዕርስት ለሌሎች ያከፋፈለበት ትልቁ ምክንያት የአማራን ጠላቶች በማብዛት አማራ በወልቃይትና ራያ ላይ የሚኖረውን ትኩረት ለማሳጣት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ሥለሆነም የአመራን ታሪካዊ ዕርስቶች ያለ አማራ ውክልና የተከፋፈሉ ኃይሎች (ህወሓትና ኦነግ/ኦዴፓ) የፌደራል ስርዓቱን አንደ አይነ ብሌን እንጠብቀዋለን ቢሉ አይፈረድባቸውም ምክንያቱም ይሕ የዘር ፌደራዝም ለህወሓትና ኦነግ ቀደም ሲል ያልነበራቸውን መሬቶች እንዲዘርፉ እድል የሰጣቸው በመሆኑ፡፡ለዚህም ነው ኦዴፓ/አነግ በዛሬው እለት (Feb.19/02/2019) “የፌደራሊዝም ስርአት ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም” በማላት በትዕቢት መግለጫ ያወጣው፡፡

አስመሳዩና ሸንጋዩ ኦዴፓ ስልጣን በደንብ እስኪቆናጠጥ ድረስ ኢትዮጵያ ሱስ ናት፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞትም ኢትዮጵያ ነን በማለት የዋሕ ኢትዮጵያንን አስጨፈረ፤ ሁሉም የእነረሱን ፎቶ በመኪናውና በቤቱ ለጠፈ፡፡ ኦዴፓ/ኦነግ ግን ስልጣን በያዘ ማግስት ወሳኝ የሆኑ የፌደራል ስልጣኖችን ያለምንም ይሉኝታ ለብቻው ተቆጣጠረ፤ አዲስ አበባ የእኛ ናት አለ፤ በአጽሟ የቆመቸው ኢትዮጵያ በኦነግ ስትዘረፍ አይቶ እንዳላየ ዝም አለ፤ በአሸዋ ሜዳ ዘራፊ ቄሮዎች ህዝብ ሲገድሉ፤ ህፃናትን አስገድደው ሲደፍሩ፤ ንብረት ሲያወድሙ አካባቢው ለጸጥታ ጥበቃ ስለማያመች ነው ብሎ ተሳለቀ፡፡ ግፍ የደረሰባቸው ወገኖች ብሶታቸውን ሊያሰሙ ሰልፍ ሲወጡ በግፍ ተገደሉ፤ ወንጀለኛውን ቄሮን ትቶ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጀምላ በማሰር ኦዴፓ የወደፊቱ ከህወሓት የበለጠ ህወሓት እንደሚሆን በተግባር አሳየ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና አድሎ የሚከናወነው ኦዴፓ ስልጣን ከያዝ በስምንት ወራት ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ፍጥነትም ይሕ ድርጅት ሱሴናት ያላትን ኢትዮጵያ ለማፍረስ ሁሉት ዓመት የሚወስድበት አይመስለኝም፡፡

ኦዴፓም ሆነ ህወሓት ያልተገነዘቡት አንድ ትልቅ ነገር ቢኖር በ21ኛ ክፍለ ዘመን የሌላወን ታሪካዊ እርስት በጉልበት ቀምቶ መሄድ የማይቻል መሆኑን ነው፡፡ እንገነጠላለን ካሉ መገንጠል የሚችሉት የአማራን ርእስቶች በመነጠቅ ሳይሆን የራሳቸውን ዕርስት በመያዝ ነው፡፡ ይህ አካሄድ ግን ለኦዴፓ እጅግ አደገኛ ነው ምክንያቱም የእኔ ነው የሚለው ታሪካዊ እርስት ስሌለለው፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነውና ዛሬ ኦዴፓና ህወሓት አለን የሚሉት ጉልበት አማራው እንደሚኖረው መጠራጠር አይኖርባቸውም፡፡ እነርሱ በጉልበት የአማራን መሬት ሲነጥቁ አማራ ለዕርስቱ መሰዋት የማይክፍልበት ምክንያት አይኖርም፡፡
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባርነትንና ውርደትን የሚያስተናግድ አካል አይኖርም! 392SHARESShareTweetAds by RevcontentMen, You Don’t Need the Blue Pill if You Do ThisMenhealthcluesxCanada Casinos Hate This Trick Because It Pays Millions to Ottawa PlayersJackpot SecretsxFat And Slim PeopleWeight LossxInterested In Forex In Canada? Read This Article Before Openning An AccountTrading ReviewsxSome of These Snapshots Are Worth Millions!InspiredotxHere’s What New Dental Implants Should Cost You in Ottawa. Don’t OverpaySponsored linksxሳተናው

6 COMMENTS

  1. Gamadaa February 19, 2019 at 7:00 pm Do you think that the Oromo people have fought the TPLF for 27 years to bring you back to the throne of Menilk, the Hitler of Africa? Just to is futile attempt. No more business as usual!Those mentally retarded and culturally corrupted individuals like the rude Berhanu Nega, the racist Eskinder Nega and co. cannot understand true democracy. They cannot adjust their mentalities with the principles of win win approaches. They are just human INBOCH and parasites like tapeworms! But the Qeerroos will never let them do whatever not acceptable in Oromia including Finfinne. Watch out!The Ethiopian peoples have been exploited  its natural and human resources in the last 150 years because of such cheap and self centered politics and policies. The social, political, cultural and economic developments of the people are extremely retarded by such backward and inhuman mentalities. Such individuals and their ruling systems  are parasites like a tapeworm which dehydrates its host continuously. The ultra nationalists have been suffering from the mentality of racism like some of the former white south Africans who grew up in the culture of Apartheid. They write always here and their  an anti-Oromo thesis in order to justify their hatred regarding the Oromo nation and their anti-Oromo sentiments. But it cannot help them. Their “golden” time of discriminating, discrediting and uprooting the Oromo is up. Besides that they also try to promote the political ideologies of the organizations with anti-multinationality programs in order to sustain old thinking and backward political ideologies. They are not ready to accept unity in diversity. They try to preach against the multinational politics by labeling it as “clan politics”  in order to promote their hegemony in Oromia and elsewhere. But the current Ethiopian multinational politics hat nothing to do with a clan politics. None of the Oromo political organization had been promoting about clan politics. They have been promoting the political and human rights of the great Oromo nation.  De-Amharanisation of the whole Ethiopian politics is indispensable and absolutely necessary in order to reform and reshape Ethiopia as a country of multinational state. The politics of one language, one culture  and a single nation is dangerous and cannot be accepted. Don’t forget you lost your war with Eritrea. If you try against the Oromo people, you have no chance. But now temporally you can make noise. That is all what you can do right now.Every small and big ethnic groups in Ethiopia have been still demanding their own self rule against such backward and ever uncivilized mentalities.  The  persistent stubbornness of the ultra nationalists will help even more as a fuel in strengthening and speeding up the de-Amaharaization of the whole Ethiopian politics in order to substitute it with the politics of a true multinationalism. Watch out! We will have at least the following additional federal languages soon: afaan Oromoo, afaan Sidamaa , afaan Somalee,  afaan Afar and Tigren
  2. Enqoqo February 19, 2019 at 7:48 pm True, True, True. Hope now the blind Abiy supporters and so called non ethnic centered Ethiopians as they call themselves will wake up and align themselves with the truly
    ethiopian Amharas and some southern groups who are still pro-ethiopia. I also hope the shameful act by those supporters of Abiy to withdraw their support and they will stop lying to themselves now and refocus on the reality. This is a clear message to the money men like Tamagen to return the money they collected back to the diaspora since it is collected under false pretense and mis-representation by the existing oromo junta. I also ask the so called Amhara enclave party in the eprdf to re-asses its position and make a decision that is in alignment with its constituency. Always believed those opposition groups that returned to Ethiopia like G7, ESAT etc. with out anything concrete in front of them were sell outs and was I ever right. Will all these groups leave as they should immediately? Will we here sorry we goofed? Oh Ethiopia, My Ethiopia, Our Ethiopia You are Crying so are We. It is time to rise against the scrooge of marxism lenninism maoism and the student movement cohorts now for planting the seeds of division, tribalism, tribal nationalism and hate among the Ethiopian people. It is astounding to see the Haile Selassie system of government was and is superior to marxim lenninism, maoism, the proof is in front of us. Time to say we goofed children of the 60’s university students. I say we goofed as a group Now it is time to set our error right by bring Democracy to Ethiopia the western way and kick out marxism lenninism maoism for good. Ehtiopia has one people with differing cultures,belief systems, languages etc. who lived together for many centuries and can and will do so if we can kick out the cancer of marxism lenninism maoism for good. The day we cut out the cancer will be the day we cut out all its sales men too. That day will be celebrated as the second Ethiopian Independence Day.
    Enqoqo from Canada
  3. እውነቱ February 19, 2019 at 8:33 pm መከራና እልቂት ከመመኘት አማራ ከሆንክ በአማራነት ተደራጅተህ ስለ እኩልነትና ዲሞክራሲ ታገል:: እኛ ብቻ እናውቃላችሗለን በዚህ ወቅት በኢትዮጵይ አይሰራም:: ሌሎችን በመዝለፍ የሚመጣ ለውጥ አይኖርም::
  4. Degone Moretew February 19, 2019 at 8:36 pm እባብን ያየ በልጥ በረየ ይላል” ምሳሌው:: ጤናማ የፈደራል ሲስተም በሀገራችን ስላላየን በዘር ላይ የተመሰረተ ፌድራሊዝም ጣጣ ስላመጣ የፌደራሊዝም ምልከታችን አሉታዊ ሆኗል::በናጀሪያ ብዙ ተመሳስይ ችግሮች የፈቱት በጤናማ ፌደራል ሲስተም ሲሆን ደቡብ አፍርካና ጎረቤት ኬንያ ይህን ይጠቀማሉ:: በኬንያ የጎሳ ጫና እንዳይከሰት ማስተካከያ ሲያረጉ ፌደራል ክልሎች በጎሳ አልተዋቀሩም የኩኩዩ የካላንጂኒ የሶማሌ የኦሮሞ ክልል/ ግዛት የላቸውም:: ጥናቱ የተደረገው በ2012 ሲሆን በአፍሪካ በብቸኝነት ፌደራሊስምን በጎሳ የደረገችና በፌደራዝም መገንጠልን የፈቀደችው ብቸና ሃገራችን የደረሱባትን የፌደራል ችግሮች በመቅረፍ ሁሉ የሚሳተፍባት ዲሞክራቲክ ፌደራሊስት ኢትዮጲያ በመግባባት ከባህላችን ጋር በሚሄድ መልኩ ልትገነባ ትችላላቸ::ከአጼ ምኒሊክ በፊት የነበሩት ግዛቶች ፌደራል ሂደት የነበራቸው በአካባቢ ንጉሶች የሚገዙ ነበር::ንጉሰነግስት በሚል ገናናነት ሌሎቹን በማስገበር በእነሱ ቋንቋ”ሃገር ማቅናት” በትክክለኛው ግን ወረራ ተካሂዶ ቁርሾው ዛሬ ድረስ ጉዳቱ ስለሚታይ ያለፈውን ለትምህርት በመውሰድ መከባበር መቀባበል ያለበትን ፌድራላዊ ሃገር መግንባት አማራጭ የሌለው ነው የሚለው የኦዴፓ መግለጫ ተገቢ ነው::ለኢትዮጲያችን ከጤናማ የፌደራል አወቃቀር ውጭ ማእከላዊ (አሃዳዊ) አገዛዝ ለተጀመረው ለውጥና የህዝቦች ማንነት ጥያቄ እንቅፋት ነው::ዮናታን የተባሉ ምሁር የዘገቡት ትንታኔ በሚገባ ያስተምራልና ይህ ውይይት በቀና መንገድ በሁሉ ይስፋፋ ዘንድ መክራለሁ::
  5. Degone Moretew February 19, 2019 at 8:42 pm እባብን ያየ በልጥ በረየ ይላል” ምሳሌው ጤናማ የፈደራል ሲስተም በሀገራችን ስላላየን በዘር ላይ የተመሰረተ ፌድራሊዝም ጣጣ ስላመጣ የፌደራሊዝም ምልከታችን አሉታዊ ሆኗል::በናጀሪያ ብዙ ተመሳስይ ችግሮች የፈቱት በጤናማ ፌደራል ሲስተም ሲሆን ደቡብ አፍርካና ጎረቤት ኬንያ ይህን ይጠቀማሉ:: በኬንያ የጎሳ ጫና እንዳይከሰት ማስተካከያ ሲያረጉ ፌደራል ክልሎች በጎሳ አልተዋቀሩም የኩኩዩ የካላንጂኒ የሶማሌ የኦሮሞ ክልል/ ግዛት የላቸውም:: ጥናቱ የተደረገው በ2012 ሲሆን በአፍሪካ በብቸኝነት ፌደራሊስምን በጎሳ የደረገችና በፌደራዝም መገንጠልን የፈቀደችው ብቸና ሃገራችን የደረሱባትን የፌደራል ችግሮች በመቅረፍ ሁሉ የሚሳተፍባት ዲሞክራቲክ ፌደራሊስት ኢትዮጲያ በመግባባት ከባህላችን ጋር በሚሄድ መልኩ ልትገነባ ትችላላቸ::ከአጼ ምኒሊክ በፊት የነበሩት ግዛቶች ፌደራል ሂደት የነበራቸው በአካባቢ ንጉሶች የሚገዙ ነበር::ንጉሰነግስት በሚል ገናናነት ሌሎቹን በማስገበር በእነሱ ቋንቋ”ሃገር ማቅናት” በትክክለኛው ግን ወረራ ተካሂዶ ቁርሾው ዛሬ ድረስ ጉዳቱ ስለሚታይ ያለፈውን ለትምህርት በመውሰድ መከባበር መቀባበል ያለበትን ፌድራላዊ ሃገር መግንባት አማራጭ የሌለው ነው የሚለው የኦዴፓ መግለጫ ተገቢ ነው::ለኢትዮጲያችን ከጤናማ የፌደራል አወቃቀር ውጭ ማእከላዊ (አሃዳዊ) አገዛዝ ለተጀመረው ለውጥና የህዝቦች ማንነት ጥያቄ እንቅፋት ነው::ዮናታን የተባሉ ምሁር የዘገቡት ትንታኔ በሚገባ ያስተምራልና ይህ ውይይት በቀና መንገድ በሁሉ ይስፋፋ ዘንድ መክራለሁ::
  6. Abba Caala February 19, 2019 at 10:39 pm Fallacy #1: “ኢትተጵያም በሶስት ክፉ ጠላቶች ስር ወደቀች፡- ህወሓት፣ ሻእቢያና ኦነግ፡፡ በዚህ ወቅት ኢትየጵያን ወደ ሞት ከሚወስዷት አውሬዎች የሚከላከል ሌላ ሃይል አልነበራትም፡፡ ” ባንተ ቤት ህወሓት፣ ሻእቢያና ኦነግ ባህር ተሻግረው የመጡ የዉጪ ጠላቶች፣ ኢትዮጲያ ደግሞ የሚከላከልላት መንግስት/መንግስቱ ሃ ማ እንዳልነበራት፣ ወይም ፋሺስታዊዉ ደርግ ፕሪስተር ጆን (Priester John) የነበረ አስመሰልከው!
    Fallacy #2: ” የጸረ-ኢትዮጵያው ህገ መንግስት ዋና ግቡ ለኢትዮጵያ ህልውና መሠረት የሆኑ ነገሮችን በሙሉ መደምሰስ ነበር/ነውም ” ባንተ ቤት “የኢትዮጵያ ህልውና መሠረት” አንድ ህዝብ፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል በሚለው አባዜ የአምሃራን የበላይነት ማስጠበቂያ የደርግ መፈክር ነው?? ወይስ ኢትዮጲያ ማለት አማሃራ ማለት ሆኖ የተቀሩት እንደ አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ አምሃራን እንዲያመልኩ የነበረው (አሁንም የአብን ማኒፈስቶ) መቀጠል አለበት??
    Fallacy #3: “ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ብሄር ሳይገድባቸው እጅግ የተደበላለቁ በመሆኑ …” በአእምሮህ ዉስጥ ብቻ ነው የተደበላለቁብህ! እንኳን ጋምበላ፣ ሙርሲ ወይም ክፍቾ ቀርቶ አ አ ዙርያ አሉትን ኦሮሞዉንም በቅጡ አታዉቅም። እርግጠኛ ነኝ፣ ከአማርኛ ሌላ የሃገሪቱ ቋንቋ አትችልም! ስለኢትዮጲያዉያን አንድ መሆን ግን ካንተ በላይ የሚያዉቅ የለም!
    Fallacy #4: “ብሄረን መሠረት ያደርገ ከቀየ መፈናቀል፤ መገድል ንብረትና ሀብትን መዘረፍ የኢትዮጵያውያን የሩብ ክብለ ዘመን ቋሚ ክስተት ሆኗል፡፡” ለአንተ ዘመን መቆጠር የተጀመረው ከሩብ ክፍለዘመን ወዲህ ነው?! ሚኒሊክ ከነጭፍሮቹ ወደ ምስራቅ፣ ደቡብና ምእራብ ሲዘምት ብስኩት እና ከረሜላ እያደለ ነበር የሄደው?? የኦሮሞ ህዝብ በግማሽ፣ ወላይታ እና ካፍቾ ሁለት/ሶስተኛው ያለቀው ራሱን ገድሎ ነበር? የተቀሩት በገዛ ቀዬአቸው ለነፍጠኞች ገባር የተደረጉት “የኢትዮጵያ ህዝብ” ሁሉ አንድ ስለሆነ ነዋ!Fallacy #5: “ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በዋናነት የአማራን ታሪካዊ ረዕስቶች መከፋፈል ናቸው” ስትል በሚኒሊክ ጊዜ በምርኮ ስም የተከፋፈለላቸውን የሌሎች ህዝቦችን መሬት ማለትህ ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ነው እያልክ ደግሞ ለአምሃራ ብቻ ምን አስጨነቀህ ታዲያ?? የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ነው ብለህ ስትሟገት ከርመህ “አምሃራ እንዲህ ሆነ፣ እንደዚያ ተደረገ” ስትል Fallacy #2 ማረጋገጥህ ነው > ያንተ ኢትዮጵያ = አምሃራ !!ስለዚህ አሁን ያለው ፈደራሊዝም የአምሃራን “ታሪካዊ ረዕስቶች” (ያባቶችህን ጋሻ መሬቶች) ስለሚያሳጣህ “አምሃራ መስዋዕት መክፈል አለበት”!!
    የነፍጠኛ “ዲሞክራቶች” ፍልስፍና እንዲህ ነው !! በ21ኛው ክፍለ ዘመንም እንኳ እንደ 13ኛው ክዘ ነው የሚያስቡት! Brain dead dinosaurs!