February 20, 2019 eet

ድንቄም ከንቲባ?! ~~~
*************************
የለገጣፎ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በያዝነው ሳምንት ሶስት ሺህ ቤቶች እየፈረሱ እንዳሉና በቀጣይ 12 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ለOMN አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በአካባቢው ባለስልጣናት ፈቃድ ተሰጥቷቸው፣ ግብር እየከፈሉና የቤቶቻቸው ካርታ ሳይቀር ያላቸው ናቸው። ታድያ የነዋሪዎቹ ቤት እየፈረሰ ፈቃዱን የሰጡት የአካባቢው ባለስልጣናት የማይጠየቁበት ምክኒያት ምንድነው???
……………………………………….
ፈቃዱን የሰጡት ባለስልጣናት ይህን ሁሉ ህዝብ ሜዳ ላይ በመጣልና ቤተሰብን በመበተን ነዋሪዎቹ ላይ ለፈጸሙት ወንጀል በህግ ሊጠየቁ ይገባል። የከተማው ከንቲባ ፈቃድ የሰጡትን ባለስልጣናት ከስራ ማገድ ይኖርባቸዋል። አቃቤ ህግም በእነዚህ ባለስልጣናት ላይ ክስ መመስረት ይኖርበታል። ከንቲባዋ ግን ገና 12 ሺህ ቤቶች ይፈርሳሉ ብለው ሲናገሩ ትንሽ ጉድጓድ እንድትቆፈር ትህዛዝ የሰጡ ይመስል ያለምንም ዓይነት የሀዘን ስሜት ረገ ብለው ማውራታቸው እጅግ በጣም አስገርሞኛል። እንደ ሴት ርህራሄ እንኳን አይታይባትም?!
© ይልማ ኪዳኔ


749
